የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን እና UN-OHCHR በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የትብብር ፍኖተ ካርታ ይፋ አደረጉ፡፡

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን እና UN-OHCHR በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የትብብር ፍኖተ ካርታ ይፋ አደረጉ፡፡

በፕሮግራሙ ላይ የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ፣ Mr. Marcel C. Akpovo, Regional Representative of UN Office of High Commissioner for Human Rights-East African Regional Office እና ሌሎች የተቋሙ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
የፍኖተ ካርታው ስምምነት ዓለማ የህግና የፖሊሲ ማዕቀፎች፣ ቴክኒካል ድጋፍ እና የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በመስጠት በሲቪል ማህበራት ዘርፍ የተሻለ አፈጻጸም እንዲኖር ማስቻል ነው፡፡
FDRE Authority for Civil Society Organizations and UN-OHCHR have officially announced a partnership roadmap that will enable them to collaborate.
******************** ********************
Mr. Samson Biratu, Director-General of ACSO, Mr. Marcel C. Akpovo, Regional Representative of UN Office of High Commissioner for Human Rights-East African Regional Office, and other senior officials of the two Institutions have attended the announcement program. The partnership roadmap which focuses on legal and policy framework, technical assistance and capacity building training aims to realize enhanced performance of the civil society sector in Ethiopia.


የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በአማራ ክልል በሰብዓዊ ድጋፍና በመልሶ ማቋቋም ስራዎች ላይ በስፋት መንቀሳቀስ እንዳለባቸው ተጠቆመ፡:

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ እና ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች በአማራ ክልል ከሚንቀሳቀሱ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር በባህር ዳር ከተማ ምክክር አድርገዋል፡፡ የውይይት መድረኩ በክልሉ የፋይናንስ ቢሮ በኩል የተዘጋጀ ሲሆን የቢሮው ኃላፊ ዶ/ር ጥላሁን መሀሪ እና የክልሉ የተለያዩ የመንግስት ተቋማት አመራሮች እና በክልሉ በሰብዓዊ ድጋፍ እና በልማት ስራዎች ላይ እየተንቀሳቀሱ ያሉ ድርጅቶች ተሳታፊ ሁነዋል፡፡
May be an image of 2 people and dais
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ቀዳሚ ተግባር የህዝብን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ከመሆኑ አንፃር በግጭትና በተለያዩ ምክንያቶች ችግሮች በሚያጋጥሙበት ወቅት ከማንኛውም አካል በመቅደም ሰብዓዊ ድጋፍ ማድረግ እና የመልሶ ግንባታ ስራዎችን ማከናዎን እንደሚኖርባቸው በውይይቱ አጽንኦት ተሰጥቶት ቀርቧል፡፡ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢ ስራዎችን የሚያከናውኑ ሲቪል ማህበራት ችግሮች አጋጥመዋል በሚል ስራቸውን ሳያቆሙ ወይም ሳይቀንሱ ይልቁንም በበለጠ በማጠናከርና በማሳደግ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች በመንቀሳቀስ የአስቸኳይ ጊዜ ምላሾችን እያደረጉ መሆኑን በማንሳት ለዚህም ተንቀሳቀሶ ለመስራት የሚያስችል ሁኔታ ያለ መሆኑን አቅርበዋል፡፡ ሆኖም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አስተዋፅኦ በስፋትም በተደራሽነትም መሻሻል የሚገባው መሆኑ እና ለዚህም ሲቪል ማህበራት ሃብት በማሰባሰብ ማህበረሰቡን ባሳተፈ መልኩ ስራዎችን መስራት እንደሚገባቸው ጥሪ ተላልፏል፡፡
በዚሁም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የሰብዓዊ ድጋፍ በማድረግና በዘላቂ ልማት ስራዎች ላይ በተለይም ትምህርት ቤት እና የጤና ተቋማት አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ በማድረግ ከመቼውም ጊዜ በላይ መስራት እንዳለባቸው የባለስልጣኑ አመራሮችና የክልሉ የስራ ሃላፊዎች አፅንኦት ሰጥተው ገልፀዋል፡፡
የባለስልጣን መ/ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ የመንግስት ቁርጠኛ መሆንን አረጋግጠው ለማህበረሰቡ የሰብዓዊ ድጋፎችን በማድረግ እንዲሁም ዘላቂ ልማትና ሰላምን የሚያረጋግጡ ስራዎችን በማከናዎን ረገድ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በንቃት እንዲንቀሳቀሱ አሳስበዋል፡፡ ባለስልጣን መ/ቤቱም ለዚህ ስኬት አስፈላጊውን የማስተባበር፣ የመደገፍና የመከታተል ሚናውን የሚወጣ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በየወሩ የሚደረገው ተቋማዊ የንባብ ቀን ለ11ኛ ጊዜ በድምቀት ተካሂዷል፡፡

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የተቋሙን ሰራተኞች የንባብ ባህል ለማሳደግ እና የእርስ በእርስ ግንኙነትን ለማጠናከር በሚል የተጀመረው ተቋማዊ የንባብ ቀን ለ11ኛ ጊዜ በድምቀት ተካሂዷል፡፡
በዕለቱ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች እንዲሁም ከፌ.ደ.ራ.ል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
May be an image of 1 person and text
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ ተቋማዊ የንባብ ቀንን የመሰሉ ከተቋማችን አልፎ ለሌሎችም ምሳሌ ሊሆኑ የሚችሉ ስራዎችን አጠናክሮ በመቀጠል አንባቢ ትውልድ መፍጠር እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡ የፍትህ ሚንስቴር ሚንስትር ደዔታ ዶ/ር ኤርሚያስ የማነብርኃን መርሃ ግብሩ ሳይቆራረጥ እዚህ በመድረሱ መደሰታቸውን ገልጸው መርሃ ግብሩ ለተቋሙ ሊጠቀስ የሚችል ትልቅ ተግባር በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ በምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ በኩል መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የሶፎስ አፍሪካ መስራችና ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ደስታ ሃሊሶ በፕሮግራሙ ላይ የተገኙ ሲሆን የተቋሙን ቤተ መጻህፍት ለማጠናከርና የርሳቸውንም ልምድና ተሞክሮ ለማጋራት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ በመርሃ ግብሩ ላይ በፌ.ደ.ራ.ል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን የማረምና ማነጽ ተሃድሶ ልማት ዘርፍ የትምህርትና ስልጠና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ አዝመራው አብደታ በፌደራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ከንባብ ጋር በተያያዘ ያሉ ተሞክሮዎች ያቀረቡ ሲሆን በተለይም ከታራሚዎች ጋር በተያያዘ ከተለያዩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር በመተባበር የእውቀት ማዕከላትንና ቤተመጻህፍትን በማደራጀት ረገድ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ ተጠቁሟል፡፡
ተቋማዊ የንባብ ቀን ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ካለፈው ዓመት ጀምሮ በየወሩ በተከታታይ የተለያዩ ሰዎችን በመጋበዝ የንባብ ተሞክሯቸውን እንዲያቀርቡና የተቋሙ ሰራተኞችም ያላቸውን ተሰጥዖ እንዲያሳድጉና የንባብ ባህላቸውን እንዲያጎለብቱ በማድረግ ረገድ አስተዋጽዖ እያደረገ ያለ ተቋማዊ ፕሮግራም ነው፡፡

አገር በቀል ድርጅቶችን ማጠናከር የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ዓላማ ማሳካት ነው፡፡

አገር በቀል ድርጅቶችን የውስጥ አቅማቸውን ለማጎልበት ንቁና ተጠያቂነትን ያለው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ለመፍጠር እንዲሁም በዴሞክራሲያዊ ስርዓት እና በግጭት አፈታት ስርዓት ላይ የራሳቸውን አስተፅኦ እንዲያደርጉ በጀርመን አግሮ አክሽን (GAA)፣) በዴቨሎፕመንት ኤክስፐርቲዝ ሴንተር (DEC) እና በራስ አገዝ ቡድን አሰራር ድርጅቶች ህብረት በኢትጵያ (CoSAP) በጋር ከአውሮፓ ህብረት ባገኙት ድጋፍ የሲ ኤስ ኤፍ ፕላስ መርሀግብር ለ101 አገር በቀል ድርጅቶች የሚውል 3.5 ሚሊዮን ዩሮ አቅም ለማሳዳግ የሚውል ፈንድ ለማስተላለፍ የሚየያስችል መርሀግብር ተካሄደ፡፡ በመርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የባለስልጣኑ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ እንዳሉት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ዘርፍ ሪፎርም ለማድረግ በርካታ ስራዎች ሲሰራ መቆየቱን አንስተው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በሃገረ መንግስት ግንባታው ጠንካራ፣ የበለፀገች፣ ዴሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብቶች የተከበሩባት ልዕልናዋ ከፍ ያለ አገር በመገንባት ሂደት ላይ ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ገልፀዋል፡፡
May be an image of 5 people, dais and text
አያይዘውም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት መረጋገጥ የሚቻልበትን አውድ ለመፍጠር ባለፉት ዓመታት በተከናወኑት የሪፎርም ስራዎች ውስጥ አንዱ የህግ ማሻሻል ተደርጎ ለአምስት ዓመታት እየተተገበረ መሆኑን አንስተው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በርካታ መብቶችን ያጎናፀፈ ትልቅ ሀላፊነት የሰጠ በዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ እና በዘላቂ ልማት ላይ እንዲሁም የህብረተሰቡን የላቀ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
አዳዲስ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በተፈጠረላቸው ምቹ አውድ የሚጠበቅባቸውን ሀላፊነት እና አገር በመገንባት ረገድ እየሰሩ ያለው ስራ መልካም ቢሆንም ያሉባቸውን ችግሮችን ማረም እንደሚጠበቅባቸው ገለፀዋል፡፡
አገር በቀል ድርጅቶችን ማጠናከር የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ዓላማ ማሳካት መሆኑን ያነሱት ሃላፊው ይህ ፕሮግራም አገር በቀል ድርጅቶችን ለማጠናከር ታሳቢ ያደረገ ፕሮጀክት (GAA)፣) በዴቨሎፕመንት ኤክስፐርቲዝ ሴንተር (DEC) እና በራስ አገዝ ቡድን አሰራር ድርጅቶች ህብረት በኢትጵያ (CoSAP) ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጋር በመወያየት ከ36 የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ውስጥ 22 አዲስ የተቋቋሙ ድርጅቶች መሆናቸውን ም/ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡
አገር በቀል ድርጅቶች አቅማቸውን በመገንባት የህዝብን ጥቅም በዘላቂነት ለማረጋገጥ ውጤታማ ስራዎችን ማከናወን እንዳለባቸው በመግለፅ ፕሮግራሙ ውጤታማ እንዲሆን ባለስልጣን መስሪያቤቱ አስፈላጊውን ድጋፍና ቁጥጥር እንደሚያደርግ ም/ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ፋሲካው ሞላ አሳስበዋል፡፡ ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ለድርጅቶቹ በበጀት ድጋፍ ያደረገውን አውሮፓ ህብረት እንዲሁም ያሳተባበሩ ድርጅቶችን አመስግነዋል፡፡ የጀርመን አግሮ አክሽን (GAA) የአገር ውስጥ ተጠሪ ወ/ሮ ሳራ ወርቁ እንደገለፁት WHH በጀርመን አገር ውስት አንጋፋ አለም አቀፍ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት መሆኑን ጠቅሰው ይህ ድርጅት እ.ኤ.አ በ1972 የጀርመን አግሮ አክሽን ስም በኢትዮጰያ ተመዝግቦ እየሰራ ያለ ድርጅት ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡ WHH ከአውሮፓ ህብረት ባገኙት ድጋፍ የሲ ኤስ ኤፍ ፕላስ (CSF+) መርሀግብር ለአገር በቀል ድርጅቶች አዲስ የአቅም ግንባታ ፕሮግራም በመተግበር ላይ እንደሚገኝ አንስተዋል፡፡

የተቋሙ ሰራተኞች የበጎ ፊቃድ ስራ ላይ ሞዴል መሆን እንደሚገባቸው ተገለፀ::

የተቋሙ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ መስፍን ሙሉነህ በበጎ ፍቃድ ዙሪያ በተዘጋጀ ስልጠና ላይ ባደረጉት ንግግር ተቋሙ ከተቋቋመበት ዓላማ መካከል በህብረተሰቡ ዘንድ የበጎ አድራጎትና በጎ ፍቃደኝነት ባሕል እንዲዳብር ማድረግ የሚገኝበት ሲሆን ይህንን ተፍጻሚ ለማድረግ በርካታ ተግባራት መከናወኑን ገልፀዋል::
አያይዘውም በጎ ፍቃድን ለማስረፅ ሃላፊነት እንደተሰጠው አንድ ተቋም አርዓያ ሆኖ መገኝት አስፍላጊ በመሆኑ የተቋሙ ሰራተኞች በፍላጎት ተሰባስበው እርስ በእርስ የሚረዳዱበት ሰውነት የሚባል በጎ ፍቃደኞች መረዳጃ ማህበር መመስረታቸውን ተናግረዋል። ሰራተኞች የበጎ ፊቃድ ስራ ላይ ሞዴል መሆን ይገባቸዋል ያሉት ሃላፊው እንደ ጅምር ሰውነት ማህበር የሰራቸው ስራዋች አበረታች መሆናቸውን እና በተለይም የተቋሙ ዝቅተኛ ተከፍይ የሆኑና በተለያየ ችግር ውስጥ ለሚገኙ የስራ ባልደረቦቻቸው በገንዘብና በዓይነት ያደረጉት ድጋፍ ተጠቃሽ መሆኑን አንስተዋል።
May be an image of 1 personMay be an image of 1 person
የስልጠና መድረኩም ዓላማ ሰዋች የበጎ ፍቃድ ስራ በልምድ ሳይሆን ፅንሰ ሃሳቡን ተረድተው ቢሰሩ የበለጠ ውጤት እንደሚያመጡ በማመን ለተቋሙ የሰውነት አባላት ስልጠና መዘጋጀቱን አቶ መስፍን ተናግረዋል። በስልጠናው ማጠቃለያ ንግግር ያደረጉት የተቋሙ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፍሲካው ሞላ በበኩላቸው በጎነት እና መልካምነትን የሚኖር ሰው በህይወቱም በስራውም ውጤታማ ነው ያሉት ሃላፊው በተቋም ደረጃም የሚከናወነው በጎ ተግባር ተቋም ላይ አስተዋፅኦ ስለሚያደርግ መደገፍና ከዚህ የተሻለ ስራ እንዲሰራ ማድረግ ይጠይቀናል ብለዋል። የበጎ ፍቃድ ስራ ሰዋች በፍፁም ቅንነት እና ከልብ በመነጨ ፍቃደኝነት የሚከውኑት መሆኑን አንስተው እንደሃገርም ከተጠቀምንበት በርካታ ተግዳሮቶቻችንን የምንጠግንበት ነው ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፍዋል።

ካቶሊክ ሪሊፍ ሰርቪስ (CRS) በጭሮ ከተማ ያብዶ ጎጀሌ ቀበሌ ከሰላሳ ስድስት ሚሊየን ብር በላይ ያስገነባውን የውሃ ፕሮጀክት አስመረቀ።

በምስራቅ ሐረርጌ ያብዶ ጎጀሌ ወረዳ ከሰላሳ ስድስት ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተገነባው የውሃ ኘሮጀክት የተለያዩ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዋች በተገኙበት ተመርቋል።
የፍትህ ሚኒስቴር አማካሪ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ኡመድ ኡጁሉ በምረቃት ስነ-ስርዓት ላይ የተገኙ ሲሆን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን እንደ ተጠሪ ተቋም የሚመዘግባቸውን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን የመከታተልና የመደገፍ ሃፊነት አለብን በማለት ድርጅቱ የጀመራቸውን ማህበረሰብ ተኮር ስራዎች አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው አንስተው ከመንግስት አስፈለጊ እገዛ ለማድረግ ዝግጁ ነን ሲሉ ገልጸዋል፡፡
የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ ባደረጉት ንግግር ድርጅቱ በሃገሪቱ የተለያዩ አከባቢዋች እያከናወነ ያለው ተግባር አበረታች መሆኑን ገልፀው ዛሬ የተገነባውን የውሃ ኘሮጀክት ቀጣይነቱ እንዲረጋገጥ ማህበረሰቡ በሃላፊነት መጠበቅ አለበት ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
May be an image of 5 people and text
የካቶሊክ ሪሊፍ ሰርቪስ (CRS) ዳይሬክተር አቶ ዘመዴ አበበ ድርጅቱ የሰራቸው ስራዎችን ለመመልከት የተገኙ ባለድርሻ አካላትን አመስግነው ይህ ፕሮጀክት እንዲጠናቀቅ ድርጅቱ ካበረከተው አስተዋጽኦ በተጨማሪ የመንግስት ባለድርሻ አካላት እና የህዝብ ተሳትፎ ከፍተኛ መሆኑን አንስተዋል፡፡ ካቶሊክ ሪሊፍ ሰርቪስ (CRS) በኢትየየጵያ ከ65 ዓመታት በላይ ያስቆጠረ እና በተቀናጀ የልማት ስራዎች ላይ ተሰማርቶ እንደሚገኝ ያነሱት ዳይሬክተሩ የምረቃት ፕሮግራሙም ዓላማ ድርጅቱ የሰራቸው ስራዎችን ማስተዋወቅና ቀጣይነቱን ለማረጋገጥም መሆኑ አብራርተዋል፡፡ ድርጅቱ በመላው ሃገሪቱ በሁሉም ክልልች በውሃ፣በትምህርት፣በሰብዓዊ ድጋፍ ስራዎች፣በውሃ፣በጤናና እና በግብርና ስራዎች ላይ በመሰማራት በባለፉት ዓመታት በርካታ የማህበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ አድርጓል፡፡
በምስራቅ ሐረርጌ ያብዶ ጎጀሌ ወረዳ የተመረቀው የውሃ ፕሮጀክት ከሰባት ሺህ ዘጠኝ መቶ በላይ የማህበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ያደረገ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ ለትምህርት ቤት መስመር በመዘርጋትና ለእንስሳት አገልግሎት እንዲውል ገንዳዎችን የመገንባት ስራ ሰርቷል፡፡
ተጠቃሚዎች በሰጡት አስተያየትም ከዚህ ቀደም በውሃ እጦት ምክንያት በርካታ የቀበሌው ነዋሪዎች ችግር ላይ መውደቃቸውን ጠቅሰው አሁን ላይ ድርጅቱ ባስገነባው የውሃ ፕሮጀክት ተጠቃሚ መሆናቸውን እና እረፍት ማግኘታቸውን ገልጸዋል፡፡ አያይዘውም ከውሃ በተጨማሪ በኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የቁጠባ እና መነሻ ካፒታልና እንስሳትን በመስጠት የቀበሌው ነዋሪዎች በኢኮኖሚ እራሳቸውን እንዲችሉ የማድረግ ስራ መስራቱን ገልጸው ለዚህም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ ድርጅቱ በምስራቅ እና ምዕራብ ሐረርጌ ብቻ በ12 ቀበሌዎች በላይ የተለያዩ የልማት ስራዎችን መስራቱ ተጠቅሷል፡፡

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ለተቋሙ የኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ስልጠና ሰጠ፡፡

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በተቋሙ ለሚገኙ የኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጥቷል፡፡
May be an image of 6 people, people studying, table, dais and textስልጠናው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በጀመረው የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እቅድ መሰረት በተደረገ የዳሰሳ ጥናት የተለዩ ከፍተቶችን ለመሙላት ታስቦ የተዘጋጀ ሲሆን በተለይም በNextcloud, eservices, EFMIS እና ኔትዎርኪንግ ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና ነው፡፡
በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ወ/ሮ ፋንታዬ ኩምሳ እንደገለጹት ስልጠናው ሲዘጋጅ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ወጥ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ዘመናዊ የዲጂታል አጠቃቀም ለመዘርጋት ባወጣው የተቋሙ የአይቲ ፖሊሲ መሰረት ውጤታማ አፈጻጸም እንዲኖር የሚያስችል ነው፡፡
ተቋሙ በውስጥ አቅም ያበለጸገውንና ለውሥጥ ተግባቦት ስራ ላይ ያዋለውን የNextcloud እና talk ገጾችን እንዲሁም የተገልጋዮችን ምልልስ እና እንግልት በከፍተኛ ሁኔታ በመቀነስ ረገድ ትልቅ አስተዋጽዖ እያደረገ የሚገኘው የኢሰርቪስ አገልግሎት የበለጠ ውጤታማ እንዲሆን ባለሙያዎቹ በቂ ግንዛቤ እንዲይዙና በስራ ላይ የሚያጋጥማቸውን ክፍተት ለመሙላት የሚያግዝ ስልጠና መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በአገር ደረጃ የተከናወኑ የ100 ቀናት የእቅድ አፈጻጻም ሪፖርት ላይ ተወያዩ፡፡

የ2017 የመጀመሪያ 100 ቀናት የሪፎርም ዋና ዋና የኢኮኖሚ አፈጻጸም ላይ በአራት ክፍሎች ተሰናድቶ በተዘጋጀው ሰነድ ላይ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን አመራሮችና ሰራተኞች ውይይት አካሄዱ፡፡ በውይይቱ ላይ የባለስልጣኑ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ መስፍን ሙልነህ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በንግግራቸውም የ2017 የመጀመሪያ 100 ቀናት የሪፎርም ዋና ዋና የኢኮኖሚ አፈጻጸም በአገር ደረጃ የተገመገመ መሆኑን ገልፀው በተቋማችን ደረጃም በተመሳሳይ ውይይት መደረጉ አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል፡፡
May be an image of 8 people, people studying and crowd
አያይዘውም የመጀመሪያ 100 ቀናት የሪፎርም ዋና ዋና የኢኮኖሚ አፈጻጸም ላይ አመራሩና ሰራተኛው የሚሰጠው አስተያየቶችና ጥያቄዎች ለቀጣይ በአገር ደረጃ ለሚከናወኑ የሪፎርም ስራዎች እንደግብዓትነት ለመጠቀምና የተሻለ ውጤቶችን ለማስመዝገብ ከፍተኛ ሚና እንደለው ጠቅሰዋል፡፡ በውይይቱ ላይም የተለያዩ አስተያየቶችና ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን በተነሱት ላይም ከአወያዮች ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

ባለስልጣኑ አዲስ በወጡ መመሪያዎችና ሂዩማን ራይትስ ቤዝድ አፕሮች ዙሪያ ለተቋሙ ባለሙያዎች ስልጠና ሰጠ::

ባለስልጣኑ የሰራተኛውን እና የአመራሩን አቅም ለመገንባት የተለያዩ የእውቀት የአመለካከትና የክህሎት ስልጠናዎችን እየሰጠ ይገኛል፡፡ በስልጠናው ላይ የተገኙት የባለስልጣኑ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ መስፍን ሙሉነህ እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት መስሪያ ቤቱ የመፈፀምና የማፅፈፀም አቅሙን ለማጠናከር እንዲሁም የአገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል በቅድሚያ የሰራተኛውን አቅም በስልጠና መገንባት ተቀዳሚ ተግባር መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

May be an image of 14 people and text

አያይዘውም የ2017 በጀት አመት ያቀድናቸው እቅዶች ከግብ እንዲደርሱ ሁሉም አመራር ከባለሙያ ጋር በቅንጅት መስራት እንዳለባቸው ገልፀዋል፡፡ ስልጠናው የሰጡት የፕሮጀክት አስተዳደር አጋርነት ቡድን መሪ አቶ እድሪስ የሱፍ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ታሪካዊ ዳራ ያቀርቡ ሲሆን አዲሱን አዋጅ 1113/2011 አስመልክቶ የክትትል ግምገማና ምርመራ መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ተሾመ ወርቁ ለተሳታፊዎች አቀርበዋል፡፡ በመቀጠልም አዲስ በወጡ መመሪያዎች ላይ ገለፃ ያደረጉት ወ/ሮ ፍሬህይወት መኮንን የቦርድ ፀሀፊ ሲሆኑ ስልጠናው ለሶስት ቀናቶች ቆይቶ ዛሬ ተጠናቋል:: ስልጠናው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከኮንሰርቲየም ኦፍ ሰልፍ ሄልፕ ግሩፕ ፕሮሞተር ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው፡፡

"የፍትህ ዘርፍ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ለሚስተዋሉ ችግሮች መፍትሄ በማስቀመጥ መልካም አስተዳደርን ማስፈን ያስፈልጋል" ክቡር ኤርምያስ የማነብርሀን (ዶ/ር)

"የፍትህ ዘርፍ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ለሚስተዋሉ ችግሮች መፍትሄ በማስቀመጥ መልካም አስተዳደርን ማስፈን ያስፈልጋል" ክቡር ኤርምያስ የማነብርሀን (ዶ/ር):: የፍትህ ሚኒስቴር የተቋም ግንባታና ሪፎርም ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር ኤርምያስ የማነብርሃን (ዶ/ር) ይህን ያሉት በዛሬው ዕለት የፍትህ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት የፍትህ ዘርፍ የአገልግሎት አሰጣጥን ማሻሻልን አላማው ያደረገ የፍትህ ዘርፍ የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ፎረም የንቅናቄ መድረክ ላይ በተገኙበት ነበር።

May be an image of 5 people, newsroom, dais and text

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 12 ላይ የመንግስት አሰራር ግልፅና ተጠያቂነት ባለበት መልኩ መሰጠት እንዳለበት ማስቀመጡን የገለፁት ክቡር ሚኒስትር ዲኤታው በዚሁ መሰረት አገልግሎት አሰጣጡን ከመልካም አስተዳደር ፅንሰ ሀሳቦች ጋር የሚቆራኝ በመሆኑ ተጠያቂነት፣ አካታችነት፣ ግልፅና ቀልጣፋ በሆነ መልኩ አገልግሎት መስጠት ያስፈልጋል ሲሉ አክለዋል።
ክቡር ሚኒስትር ዲኤታው ከፍትህ ዘርፍ ልዩ ባህሪያት አንዱ አገልግሎቱ በግል የማይሰራ መሆኑና የሚሰጡ አገልግሎቶችም ከተቋማቱ ብቻ የሚገኙ መሆናቸውን በሚገባ በመገንዘብ የሚስተዋሉ ችግሮችን አውቆ መፍታት በሚያስችል መልኩ ተፈጥሯዊ ሃላፊነትና ከፍተኛ ግዴታ ያለብን መሆኑን በመረዳት መስራት ይገባልም ብለዋል። አያይዘውም መልካም አስተዳደር በሀላፊዎች መልካም ፈቃድ ብቻ የተመሠረተ መሆን የለበትም ፤ ተቋማዊ መሆን አለበት ካሉ በኋላ በፍትህ ዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት ቅንጅታዊ አሰራርን በመፍጠርና በማዳበር ተቋማዊ በሆነ መልኩ አገልግሎት ማግኘት የህዝቡ መብት መሆኑን ግምት ውስጥ በማስገባት መንቀሳቀስ እንደሚገባ አሳስበዋል።
የፍትህ ሚኒስቴር አማካሪ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ኡመድ ኡጁሉ በበኩላቸው ብልሹ አሰራርን የምንከላከለው የተቋማት አገልግሎት አሰጣጥን ፈጣንና ቀልጣፋ በማድረግ ነው ሲሉ በፍትህ ዘርፉ የተለዩ ችግሮችን ለመፍታት ምን መስራት አለብን ለሚለው ጥያቄ መልስ እየሰጡ መሄድና የሰው አስተሳሰብ ላይ መስራት ብሎም በግልም ሆነ በተቋም ለመፍትሄው ቁርጠኛ በመሆን መስራት ያስፈልጋል ካሉ በኋላ ይህ ካልሆነ ግን የህግ የበላይነትን ለማስፈን ተጠያቂነት ተግባራዊ ይደረጋል ብለዋል።
በፍትህ ዘርፍ አገልግሎት አሰጣጥና አሰራር ላይ የሚስተዋሉ ችግሮች ላይ የተዘጋጀውን የዳሰሳ ጥናት ያቀረቡት በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የስነ- ምግባርና ፀረ ሙስና መከታተያ ክፍል ሃላፊ ወ/ሮ ትዕግስት አቡዬ በፍትህ ዘርፍ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ከሚስተዋሉ ችግሮች ውስጥ በዋናነት የሚጠቀሰው ሙስናና ብልሹ አሰራር መሆኑን ተናግረዋል።
አገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል በርካታ የመፍትሄ አቅጣጫዎች የተቀመጡ ሲሆን ተቀባይነት ያለው አገልግሎት መስጠትና ዘላቂ ተጠያቂነት ያለው ስርአት መገንባት ብሎም የተጠናከረ የመልካም ስነ- ምግባር ስርአት እንዲገነባ ማድረግ ከተቀመጡ መፍትሄዎች ውስጥ ተጠቃሽ ናቸው። የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የቀረበው የዳሰሳ ጥናት ትክክለኛውን ችግር ያመላከተ መሆኑን አንስተው የተነሱ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ለመፍታትም እያንዳንዱ ተቋም በሀላፊነት ወስዶ መስራት እንደሚጠበቅት አንስተው በተለይም የፍትህ ዘርፍ አካላት ቅንጅታዊ አሰራራቸውን በማጠናከር በጋራ ሊንቀሳቀሱ እንደሚገባ ገልፀዋል።