4ኛው ዙር የሚዲያ አካላት የመስክ ጉብኝት በስኬት ተጠናቀቀ፡፡

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የሲቪል ማህበረሰብ ዘርፉን ሚና ለሚዲያ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች በማስተዋወቅ ዘርፉን ከሚዲያ ጋር ለማስተሳሰርና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በሚሰሩት ስራ ማህበረሰቡ ተጠቃሚ አንዲሆን ለማስቻል እንዲሁም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣንን ተግባርና ኃላፊነት ማስተዋወቅን አላማ አድርጎ በየዓመቱ የሚካሄደው የሚዲያ አካላት የመስክ ጉብኝት ተጠናቋል፡፡May be an image of 6 people
በጉብኝቱ በጤና፣ በትምህርት፣ በአቅም ግንባታ፣ በግብርና፣ በውኃ እንዲሁም በተቀናጀ የልማት ስራዎች ላይ የተሰማሩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ስራዎቻቸውን ያስጎበኙ ሲሆን ድርጀቶቹ ከተቋቋሙበት ጊዜ አንስቶ የተቋቋሙባቸውን ዓላማዎች ለማሳካት እና የህብረተሰቡን የላቀ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያደረጉትን ጥረት እና የየድርጅቶቻቸውን ታሪካዊ ዳራ ለተሳታፊዎቹ አብራርተዋል፡፡
ጉብኝቱ ለተከታታይ አምስት ቀናት የተከናወነ ሲሆን በጉብኝቱ ላይ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱን ከፍተኛ ስራ ኃላፊዎችን ጨምሮ ከተለያዩ የሚዲያ ተቋማት የተውጣጡ የሚዲያ ተቋማት ኃላፊዎች እንዲሁም ከድርጅቶቹ ጋር በትብብር የሚሰሩ የመንግስት ቢሮ ኃላፊዎች እና የዞንና የወረዳ ኃላፊዎችና ተወካዮች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
በመጀመሪያው ቀን ጉብኝት በሲዳማ ብሄራዊ ክልል በሀዋሳ ከተማ አዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል ውስጥ በጤናው ዘርፍ MSH የተባለው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ከቲቪ ጋር በተያያዘ ያከናወናቸውን ጉልህ ስራዎችን በሚመለከት ገለጻ አድርገዋል፡፡ ድርጅቱ ለቲቢ ህሙማን በቂ ክትትል እንዲያገኙና የቲቢ ስርጭት እንዲቀንስ ከፍተኛ ጥረት ከማድረጉም ባለፈ ለጤና ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በመስጠትና የህክምና ቁሳቁሶችን በማሟላት ማህበረሰቡ ተጠቃሚ እንዲሆን ትልቅ አስተዋጽዖ አበርክቷል፡፡
በዚያው ሀዋሳ ላይ በተደረገው ጉብኝት FH Ethiopia በተለይ በትምህርት ላይ ያከናወናቸውን ዋና ዋና ተግባራት ፕሮጀክቶቹ በሚገኙበት ሸበዲኖ ወረዳ በትምህርት መሰረተ ልማትና በቅድመ መደበኛ ትምህርት እንዲሁም በጤና አጠባበቅ ሰርቶ ማሳያ ማዕከል ለጎብኝዎች አሳይተዋል፡፡
May be an image of 11 peopleበሁለተኛው ቀን በተደረገው ጉብኝት በዎላይታ ሶዶ ዙሪያ ሄሊቪታስ (Heli Vitas) እና አግሪቴራ (Agri tera) የተባሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በድልድይ መሰረተ ልማት እና በኢኮኖሚ አቅም ግንባታ ላይ የሰሯቸውን ስራዎች አስጎብኝተዋል፡፡ በአርባ ምንጭ ከተማ በተደረገው ጉብኝትም በተለይ በህጻናት ቃጠሎ ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራው ችልድረን በርን ኤንድ ውንድድ ኬር ፋውንዴሽን(children burn and wounded care foundation) እና በግብርና እና ስራ እድል ፈጠራ ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራው ኤስ ኤን ቪ ስዊዝ ኮርፖሬት SNV Swiss corporate) የሰሯቸውን ስራዎቻቸውን አስጎብኝተዋል፡፡ በኮንሶ ዞን ካራት ከተማ ዙሪያ እና ኬና ወረዳዎች የእናቶችና ህጻናት ዘርፈ ብዙ ልማት ድርጅት የተባለው ሀገር በቀል ድርጅት በውኃ እና በግብርና ላይ የሰራቸውን ስራዎች ያስጎበኘ ሲሆን በእለቱም በኬና ወረዳ ለማህበረሰቡ አገልግሎት ክፍት ያደረጋቸውን የውኃ ቦኖዎች በምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ መስፍን ሙሉነህና በዞኑ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች አስመርቋል፡፡
በተለይም በኮንሶ እና በቦረና ዞኖች ከድርቅ ጋር በተያያዘ ያጋጠመውን የውኃ እጥረት ለመቅረፍ የእናቶችና ህጻናት ዘርፈ ብዙ ልማት ድርጅት፣ እስላሚክ ሪሊፍ፣ ጀርመን አግሮ አክሽን እና ኬር ኢትዮጵያ የውኃ ማስፋፊያዎችን በመገንባት፣ የሶላር ኃይልን በመጠቀም ውኃን ለማህበረሰቡ በማዳረስ እንዲሁም የአየር ንብረቱን የሚቋቋሙ የሰብል ምርቶችን በማስተዋወቅና ምርታማነትን በማሳደግ ረገድ ያከናወኗቸው ተግባራት በጉብኝቱ ወቅት ትኩረት የተሰጣቸው ናቸው፡፡
ጉብኝቱ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የማህበረሰቡን የላቀ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሚያደርገው ጥረት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምን ያህል አስተዋጽዖ እያደረጉ እንደሚገኙ ያስተዋወቀ እና ከመገናኛ ብዙኃንም ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል መንገድ የጠረገ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡

 


የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በየዓመቱ የሚያዘጋጀው የሚዲያ ኃላፊዎች የመስክ ምልከታ ሚዲያ ቱር ፕሮግራም እየተካሄደ ይገኛል፡፡

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የተቋሙን ተግባርና ሃላፊነት ማስተዋወቅንና የድርጅቶቹን አንቅስቃሴ በአካል ለሚዲያዎች በማሳየት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ለማህበረሰቡ ብሎም ለባለድርሻ አካላት ስራዎቻቸውን በመገናኛ ብዙኃን አማካኝነት እንዲያስተዋውቁ በማድረግ የዘርፉ ሚና የማጎልበት እና የማህበረሰቡን የላቀ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ዓላማ አድርጎ የተጀመረው የሚዲያ አካላት የመስክ ጉብኝት ለ4ኛ ጊዜ ከተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ኃላፊዎች በተገኙበት መካሄድ ጀምሯል፡፡ በፕሮግራሙ ላይ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ እና ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ መስፍን ሙሉነህን ጨምሮ ከተለያዩ የሚዲያ ተቋማት የተውጣጡ የሚዲያ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
May be an image of 9 people and textበጉብኝቱ ላይ የተገኙት የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ ባደረጉት ንግግር አዲሱ አዋጅ ከወጣበት 2011 ዓ.ም ወዲህ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ህግን መሰረት አድርገው በነጻነት መንቀሳቀስ እንዲችሉ ሰፊ እድል የሰጠ መሆኑን ጠቅሰው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ፤ ሚዲያና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች መቀናጀታቸው ህዝብ ተጠቃሚ እንዲሆን የሚያስችል በመሆኑ ይህ ቅንጅት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አንስተዋል፡፡ በመጀመሪያው ቀን ጉብኝት MSH እና FH Ethiopia የተባሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በሀዋሳ ከተማ በጤናና በትምህርት ዘርፎች ላይ በሀዋሳ ከተማ የሰሯቸውን ስራዎች ያስጎበኙ ሲሆን ድርጅቶቹ የሚሰሩበትን ዓላማ እንዲሁም ድርጅቶቹ ከተቋቋሙበት ጊዜ አንስቶ ከመንግስትና ከማህበረሰቡ ጋር በመቀናጀት በትምህርትና በጤና እንዲሁም በአቅም ግንባታና መሰል ተግባራት ላይ ያከናወኗቸውን ተግባራት አቅርበዋል፡፡ በሁለተኛው የጉብኝቱ ቀን በዎላይታ ሶዶ በውኃ፣ ምግብና አየር ንብረት፤ በስራ እድል ፈጠራና አሳታፊነት ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራው ሄልቪታስ የተባለው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት የሰራውን የባንበላ በዴሳ ተንጠልጣይ ድልድይ በመስክ የታየ ሲሆን ድርጅቱ በተቋቋመባቸው ዓላማዎች መሰረት ያከናወናቸውን ዋና ዋና ተግባራት አስተዋውቋል፡፡
በተጨማሪም በዚሁ በዎላይታ ሶዶ ዞን በኢኮኖሚ አቅም ግንባታ ላይ ትኩረቱን አድርጎ የሚሰራው አግሪ ቴራ የተባለው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት በዞኑ ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ በሄምቤቾ ገበሬዎች ሁለገብ መሰረታዊ የህብረት ስራ ማህበር ያደረጋቸውን የአቅም ግንባታ ስራዎችን በመስክ ጉብኝት የታዪ ሲሆን ድርጅቱን የስራ እንቅስቃሴ በተመለከተ የድርጅቱ የስራ ኃላፊዎች ገለጻ አድርርዋል፡፡ ጉብኝቱ በአርባ ምንጭ ከተማ የሚቀጥል ሲሆን በግብርና በጤና መሰረተ ልማት ላይ የተሰሩ ስራዎች በጉብኝቱ የሚዳሰሱ ይሆናል፡፡

 


ሀገር በቀል የፋይናንስ ተስፋ ሰጪ ምንጮች ለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በሚል የፓናል ውይይት ተካሄደ፡:

May be an image of 1 person, dais and text that says 'វ MSI REPRODUCTIVE CHOICES MECHANISMS OF A PANEL DISCUSSION ΟΝ PROMISING SUSTAINABILITY DOMESTIC FINANCING FOR THE OF CIVIC SOCIETY ORGANIZATIONS ሀገር በቀል የፋይናንስ ተስፋ ሰጪ の円 ለሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች ቀጣይ ፋይዳ -የዉይይት መ MAY20,20 MAY 20 203 ADDIS መስበስት'የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ 1113/2011 ለሀገር በቀል ድርጅቶች የገቢ ማስገኛ ስራዎችን እንዲሰሩ ፍቃድ የሰጠ በመሆኑ በርካታ ድርጅቶች በገቢ ማስገኛ ስራ ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ፡፡ በውይይቱ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ም/ ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ እንዳሉት አዲሱ አዋጅ ለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ከፍተኛ የሆነ የስራ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ ሰፊ ምዕዳር የፈጠረ መሆኑን በማንሳት ሀገር በቀል ድርጅቶች ከውጭ እርዳታ ጥገኝነት ተላቀው በሀገር ሀብት መንቀሳቀስ እንዳለባቸው ገልፀዋል፡፡ አያይዘውም በባለስልጣኑ ተመዝግበው ከሚገኙ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ውስጥ ከ3000 በላይ አዲስ የተመዘገቡ ድርጅቶች መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
ሌላው ያነሱት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ታይቶ መጥፋት ሳይሆን ንቁ፣ ዓላማውን ያወቀ፣ በማህበረሰቡ ተቀባይነት ያለው፣ ለሀገር የሚጠቅሙ መሆን አለባቸው ያሉት ም/ዋና ዳይሬክተሩ አገር የሚጠቅም ትልልቅ ስራዎችን ማለትም በሰብዓዊ ድጋፍ፣በልማት እና በዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ላይ መስራታቸውን አንስተዋል፡፡ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ያላቸውን ጥሩ ተሞክሮዎችን በመለዋወጥ በአገር ላይ ጉልህ አሻራ ማሳረፍ እንዳለባቸውም/ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡ የማሪስቶፐስ ኢንተርናሽናል ካንትሪ ዳይሬክተር ዶ/ር አበበ ሽብሩ ባደረጉት ንግግር የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ትልቁ ሚናቸው የሀገራችንን እድገትና ኢኮኖሚ መደገፍ ነው ሲሉ በተለይ መንግስት በማይሸፍናቸው የልማት ስራዎችን በመስራት በህብረተሰቡ ዘንድ ዘለቄታ ያለው ስራ መስራት እንዳለባቸው አንስተዋል፡፡
ሌላው ያነሱት አዲሱ አዋጅ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በገቢ ማስገኛ ስራ ላይ እንዲሰማሩ የሚፈቅድ መሆኑን በመግለፅ በደንብ ከተተገበረ በሀገር ደረጃ ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር አንስተዋል፡፡ በመድረኩ ላይ በገቢ ማስገኛ ስራ ላይ ከተሰማሩ ድርጅቶች ሜሪስቶፐስ ኢንተርናሽናል እና ተስፋ ድርጅት ተሞክሯቸውን አቅርበዋል፡፡ የባለስልጣኑ ድጋፍና አገልግሎት መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ብርሀኑ አባተ የገቢ ማስገኛ መመሪያ ቁጥር 937/2015 ገለፃ አድርገዋል፡፡

ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን: ከአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ እና ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክርቤት የተውጣጣ ኮሚቴ ባከናወናቸው ተግባራት ዙሪያ ውይይት አድርገዋል::

May be an image of 7 people and textከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን: ከአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ እና ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክርቤት የተውጣጣ ኮሚቴ ባከናወናቸው ተግባራት ዙሪያ ውይይት አድርገዋል:: ቀደም ሲል በባለስልጣኑ: በአመራር ልህቀት አካዳሚው እና በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን መካከል በሲቪል ማህበረሰብ አመራር ልማት ፕሮግራም: በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ዘርፍ ጥናትና ምርምር: በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሽልማት ፕሮግራም እና በአፍሪካ ሲቪል ማህበረሰብ የልህቀት ማዕከል ለማቋቋም የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ በአፍሪካ የአመራር ልህቀት አካዳሚ መፈረሙ የሚታወስ ነው:: ይህንኑ የመግባቢያ ሰነድ ወደተግባር ለመለወጥ የሚያስችል ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ተወካዮችም የተካተቱበት ኮሚቴ ተቋቁሞ ሲሰራ የቆየ ሲሆን የስምምነት ሰነዱን ወደተግባር ለመለወጥ የሚያስችል ስትራቴጂ ነድፎ አቅርቧል:: በተጨማሪም ኮሚቴው ከተዋቀረበት ጊዜ ጀምሮ ያከናወናቸውን ዋና ዋና ተግባራት ያቀረበ ሲሆን በቀጣይ ስለሚከናወኑ ተግባራትም ገለፃ ተደርጓል:: በእለቱ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች አቶ ፋሲካው ሞላ እና አቶ መስፍን ሙሉነህ እንዲሁም የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዛዲግ አብርሃ እና የኮሚቴው አባላት የተገኙ ሲሆን በቀጣይ የስምምነት ሰነዱን ለባለድርሻ አካላት በሰፊው እንዲተዋወቅና በፋይናንስ እንዲጠናከር አቅጣጫ አስቀምጠዋል::

 


ባለስልጣን መስሪያቤቱ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ጋር በ9 ወር የእቅድ አፈፃፀም እንዲሁም በአካታች አገራዊ ምክክር ላይ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሚና በተመለከተ ተወያየ።

ባለስልጣን መስሪያቤቱ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ጋር በ9 ወር የእቅድ አፈፃፀም እንዲሁም በአካታች አገራዊ ምክክር ላይ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሚና በተመለከተ ተወያየ።
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ጋር የ2016 በጀት ዓመት የ9 ወራት እቅድ አፈፃፀም ዙሪያ ዝርዝር ውይይት አድርጓል፡፡ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የ2016 በጀት ዓመት የ9 ወር አፈፃፀም በምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ የቀረበ ሲሆን በቋሚ ኮሚቴው በኩል የተለያዩ ጥያቄዎች ተነስተው በባለስልጣኑ አመራሮች በኩል ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
May be an image of 12 people and text
የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ ቋሚ ኮሚቴው ከዚህ ቀደም ለባለስልጣኑ የሰጠው የአፈጻጸም ግብረ መልስ በማኔጅመንት ደረጃ የተገመገመ መሆኑን በማውሳት ከተከበረው ቋሚ ኮሚቴ የሚሰጠው አስተያየትና አቅጣጫ አፈፃፀምን ለማሻሻል ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያለው በመሆኑ የተቀመጡ አቅጣጫዎችን በትኩረት እንደሚተገብሩ ገልፀዋል፡፡ በውይይቱ ባለስልጣኑ አዳጊ በሆነ መልኩ መልካም አፈፃፀሞችን እያስመዘገበ እንደሚገኝ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ በተከበሩ ወ/ሮ እፀገነት መንግስቴ እና በቋሚ ኮሚቴው አባላት የተጠቀሰ ሲሆን የተጀመሩ ውጤታማ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ እንዲሁም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በተጨባጭ የህዝብን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ስራዎችን እንዲያከናውኑ የበለጠ የክትትልና ድጋፍ ስራዎች መከናዎን ያለባቸው መሆኑን አፅንኦት በመስጠት ተገልፆል፡፡ የአካታች አገራዊ ምክክርን በተመለከተ የውይይት ፅሁፍ በአቶ አህመድ ሁሴን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ቀርቦ በቋሚ ኮሚቴው አባላት ውይይት የተደረገበት ሲሆን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የአካታች አገራዊ ምክክሩ ውጤታማ መሆን እንዲችል ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማድረግ እንደሚገባቸው የቋሚ ኮሚቴው አባላት አሳስበዋል፡፡

 


ሲቪል ብሪክስ ፎረም /Civil BRICS Forum/ በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን አዘጋጅነት በአዲስ አበባ ተካሄደ፡፡

በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን አዘጋጅነት ከሩስያ የመጡ የሲቪል ብሪክስ ፎረም ሰብሳቢዎች ከባለስልጣኑ ተወካዮችና ከኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ተወካዮች ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን የብሪክስ ሲቪል ፎረም ዓላማና አሰራርን እንዲሁም በኢትዮጵያ ተሳትፎ ዙሪያ ግንዛቤ የሚፈጠሩ ጉዳዮች ዙሪያ ሃሳቦች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
May be an image of 9 people, dais and textበፎረሙ ላይ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ፣ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ዶ/ር ንጉሱ ለገሰ እንዲሁም በጤናና አካባቢ ጥበቃ ላይ የሚሰሩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ተወካዮች የተገኙ ሲሆን ከብሪክስ ሲቪል ፎረም በኩል የፎረሙ ሰብሳቢ ዶ/ር ቪክቶሪያ ፓኖቫ እና ልዑካቸው ተሳታፊ ሆነዋል:: የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል ከመሆኗ ጋር ተያይዞ በሁሉም ዘርፎች የሀገሪቱን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ በንቃት ተሳትፎ እያደረገች መሆኑን ገልፀው በብሪክስ ሲቪል ፎረምም በንቃት ተሳትፎ በማድረግ የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን በማጠናከር የሀገሪቱን ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማሳደግ የሚያስችሉ ስራዎች እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡ አቶ ፋሲካው ሞላ በፎረሙ ላይ በኢትዮጵያ ያለውን የሲቪል ማህበራት አስተዳደር በተመለከተ ዝርዝር ማብራሪያ ለልዑኩ ያቀረቡ ሲሆን ብሪክስ ሲቪል ፎረም ለኢትዮጵያ ሲቪል ማህበራት አዲስና ተደማሪ/ተጨማሪ አጋር እንዲያገኙ በማድረግ፤ በመንግስት፣ በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እና በግሉ ዘርፍ ያለውን ትስስር በማጠናከር፤ የተለያዩ የልምድ ልውውጥ እድሎች በመፍጠር ዘርፉን በማሳደግ፤ የብሪክስ ዋና ዓላማ ውስጥ አንዱ የሆነውን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን በማጎልበት፤ እና ፕሮጀክቶችን በጋራ በመተግበር የአገርና የህዝብን ተጠቃሚነትን ለማሳደግ ጉልህ ጠቀሜታ ያለው መሆኑን በመጠቆም በብሪክስ ማዕቀፍ ውስጥ  በትኩረት መንቀሳቀስ እንደሚገባ አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡
በፎረሙ የብሪክስ ከፍተኛ ባለሙያዎች ካውንስል ሃላፊ እና የብሪከስ ሲቪል ፎረም ሰብሳቢ ዶ/ር ቪክቶሪያ ፓኖቫ ብሪክስን በሚመለከት በሰጡት ማብራሪያ በተለይም ብሪክስ ቅድሚያ በሚሰጣቸው የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ትኩረት ሰጥተው አብራርተዋል፡፡ ዶ/ር ቪክቶሪያ ፓኖቫ ብሪክስ ሲቪል ፎረም በኢትዮጵያና በብሪክስ አባል አገራት መካከል አዲስ የትብብር ምእራፍ የሚከፍት መሆኑን በማንሳት ወፊትም በቅርበት ከኢትዮጵያ ጋር የሚሰሩ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በፎረሙ ተሳታፊ የሆኑ የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበራት አመራሮች ስላከናዎኗቸው ተግባራትና በቀጣይ መኖር ስለሚገባው የትብብር ማዕቀፎች በሚመለከት ገለፆዎችን ያቀረቡ ሲሆን ፎረሙ ከብሪክስ አባል አገራት ድርጅቶችና አጋሮች ጋር ትስስር ለመፍጠር እድል የሚሰጥ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ተጠሪና እና የሰብዓዊ ጉዳዮች አስተባባሪ የሆኑትን ዶ/ር ራሚዝ አላክባሮቭን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ፡፡

May be an image of 7 people, people studying and newsroomየሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ተጠሪና የሰብዓዊ ጉዳዮች አስተባባሪ ዶ/ር ራሚዝ አላክባሮቭ ከተመራ ልዑክ ጋር በጽ/ቤታቸው ውይይት ያደረጉ ሲሆን የባለስልጣን መ/ቤቱ እና የተመድ ኢትዮጵያ ጽ/ቤት በጋራ ሊሰሩባቸው ባሰቧቸው የትብብር ማዕቀፎች ዙሪያ ሰፊ ውይይት አድርገዋል፡፡ በውይይቱ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተቋሙ የተከናወኑ የለውጥ ስራዎችን በሚመለከት ለልዑክ ቡድኑ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን በተለይም የኢትዮጵያ መንግስት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደት ላይ የላቀ ሚና እንዲወጡ የሚያስችል የፖሊሲ፣ የህግና የአሰራር ለውጦችን ያካሄደ በመሆኑ ውጤቶች የተመዘገቡ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አያይዘውም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የአገሪቱን ህግ አክብረው በመንቀሳቀስ የህዝብን የላቀ ተጠቃሚነት እንዲያረጋግጡ የተጀመረው የክትትል፣ ቁጥጥርና ድጋፍ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የገለጹ ሲሆን ባለስልጣን መ/ቤቱ የጀመራቸውን የሪፎርም ስራዎች ለማስቀጠል እና የወጠናቸውን እቅዶች ተግባራዊ ለማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ተጠሪ ጽ/ቤት ጋር በጋራና በትብብር መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ሀሳብ ተነስቶ በትብብርና በአጋርነት ለመስራት የሚያስችል የጋራ መግባባት ላይ ደርሰዋል፡፡ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የሚያከናውኗቸውን የሰብዓዊ ድጋፍ ስራዎች ለማሳለጥ በሚቻሉባቸው ጉዳዮችም ተነስተው በቀጣይም በቅንጅት የሚሰራ መሆኑ በውይይቱ ተጠቁሟል፡፡

በ ዶ/ር ይሽሩን አለማየሁ የተመራ ልዑካን ቡድን የተቋሙን የኢ-ሰርቪስ አገልግሎት ተመለከቱ፡፡

May be an image of 4 people, suit, newsroom and textየኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስቴር ዴኤታ ዶ/ር ይሽሩን አለማየሁ የተመራ ልዑክ ተቋሙ በኢ-ሰርቪስ እየሰጠ ያለውን አገልግሎት በአካል ተመልክተዋል፡፡ ሚኒስትሩ በሰጡት አስተያየት የጉብኙቱ ዓላማ ከሪፖርት በተጨማሪ የኢ-ሰርቪስ አገልግሎት ምን ደረጃ ላይ እንዳለ በመመልከት ድጋፍ ለማድረግ መሆኑን አብራርተዋል፡፡ አያይዘውም ሚኒስትር መስሪያቤታቸው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በኢሰርቪስ አገልግሎት ከመስጠት አንጻር አንደሞዴል እንደሚመለከቱት እና በቀጣይ ወደዚህ አገልግሎት የሚገቡ ተቋማትም ተሞክሮ የሚወስዱበት ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡የተቋሙ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ በበኩላቸው ተቋማቸው ወረቀት አልባ ተቋም ከመገንባት አንጻር ቁርጠኛ አቋም አንዳለው በመግለጽ በሁለተኛው ተቋማዊ የለውጥ ምዕራፍም በቴክኖሎጂ የታገዘ ተቋም መገንባት ትልቅ ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ መሆኑን አንስተዋል፡፡ ተቋሙ 54 አገልግሎቶችን በኦላይን የሚሰጥ ሲሆን የአመራሩ ቁርጠኝነት፣የክትትልና ድጋፍ ስርዓቱ እና በዘርፉ ያለው የቴክ ኖሎጂ ተጠቃሚነት ተቋሙ የኦላይን አገልግሎቱ ሳይቆራረጥ እንዲቀጥል ያስቻለው ጉዳይ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡ በመጨረሻም ከተገልጋይ ደንበኞችና ከሰራተኞች በሲስተሙ ላይ መሻሻል ይኖርባቸዋል ተብለው ለተነሱ ጥያቄዎች ሚኒስትር መስሪያቤቱ ትኩረት አድርጎ ወደ ተሻለ ደረጃ ለማምጣት እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡

 


ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ፈንድ ድጋፍ የተደረገላቸው ድርጅቶች ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጋር የስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የሲቪል ማህበረሰብ ፈንድ በማቋቋም የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችን በፋይናንስ የመደገፍና በዘርፉ ያላቸውን አስተዋጽኦ ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር እየሰራ ይገኛል ። የሲቪል ማኅበረሰብ ፈንድ ትኩረቱ በጎ ፈቃደኝነትን እና የዘርፉን ዕድገት ለማበረታታት ፣ በተለይም ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን የማኅበረሰብ ክፍሎች የሚያገለግሉ ድርጅቶችን ማበረታታት ነው ፡፡ በዚህ ፈንድ ተጠቃሚ የሚሆኑት በባለሥልጣኑ ተመዝጋቢ የሆኑ አገር በቀል ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ብቻ ናቸው:: አንድ ድርጅት የፈንድ ተጠቃሚ ለመሆን ግልፅ የሆነ የውሳኔ አሰጣጥ፣ የፋይናንስ እና ግዢ አስተዳደር የሚከተል ፤ በፕሮፖዛሉ የተጠቀሰውን ፕሮጀክት የሚፈፅምበት ሌላ አስተማማኝ የገቢ ምንጭ የሌለው ፣በባለሥልጣኑም ሆነ በመንግስት የሚወጡ አዋጆችና መመሪያዎች አክብሮ የሚንቀሳቀስ እና ሌሎች መስፈርቶችን ሟሟላት ይገባቸዋል፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ለሁለተኛ ጊዜ ባወጣው ውደድር መሰረት የፈንድ ድጋፉን ያሸነፉ ድርጅቶች ኮንሶ ልማት ማህበር (በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በኮንሶ ዞን)፣ በህዝብ ተሳትፎ የተቀነባበረ ዘላቂ ልማት ድርጅት( በአፋር ክልል)፣ ሄልፒንግ ኢትዮጵያ (በትግራይ ክልል)፣ ሙዳይ በጎ አድራጎት ማህበር( በአማራ ክልል)፤ ቤዛ ፓስቶሪቲ የልማት ማህበር ሲሆኑ ጅረት ፒስ ኤንድ ሪኮንስሌሽን ኦርጋናይዜሽን በመመሪያ ቁጥር 848/2014 መሰረት በልዩ ድጋፍ የተቀመጠውን መስፈርቶች በማሟላት ድጋፍ ተደርጎላቸዋል፡፡ ለድርጅቶቹ መልዕክት ያስተላለፉት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ እንደገለፁት በአሁን ሰዓት በአገራችን ፈተናዎችና ውጣ ውረዶች በበዙበት ወቅት መንግስትም የህብረተሰቡን ህይወት ለመለወጥና የልማት ስራዎችን ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ እንደሚገኝ አንስተው ድርጅቶች የተደረገላቸውን ድጋፍ እንደመነሻ በመውሰድ ለህብረተሰቡ ውጤታማ ስራዎችን መስራት እንዳለባቸው ገልፀዋል፡፡
May be an image of 3 people and text
አያይዘውም ህብረተሰቡን በመርዳት የምናገኘው የውስጥ እርካታን በማስቀደም መስራት እንዳለባቸው አሳስበው አገራችን አሁን ያለውን ውጣ ውረዶች ተሻግራ ወደ ብልፅግና ጎዳና እንደምትሸጋገር አምናለሁ ብለዋል፡፡ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ እንዳሉት ከተመዘገቡት 86 አገር በቀል ድርጅቶች ውስጥ መስፈርቱን አሟልታችሁ ስላሸነፋችሁ እንኳን ደስ አላችሁ በማለት የተሰጣችሁ ድጋፍ አነስተኛ ቢሆንም አስተዳደራዊ ወጪውን ቀንሳችሁ ቀጥታ ለህብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ ላይ ትኩረት ብታደርጉ የተሻለ ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡
አያይዘውም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ፈንድ ለሁለተኛ ዙር ድጋፍ የተደረገ መሆኑን አንስተው በቀጣይ የማህበረሰቡን ችግር የሚፈታ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ፈንድ ማደራጀት ላይ አቅም እንደሚፈጥር ገልፀዋል፡፡ ድጋፍ የተደረገላቸው ድርጅቶች ስራቸውን በማጠናከር መስራት አለባቸው ያሉት ም/ዋና ዳይሬክተሩ በሂደትም ተቋሙ ክትትልና ድጋፍ እንደሚያደረግላቸው ተናግረዋል፡፡ ድጋፍ የተደረገላቸው ድርጅቶች ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ያደረገላቸውን ድጋፍ በማመስገን የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ላይ ትኩረት አድርገው እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ፈንድ ድጋፍ የተደረገላቸው ድርጅቶች ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጋር የስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡

ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ የበጎ ፈቃድና በጎ አድራጊነት ባህልን ለማዳበር ለአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ስልጠና ሰጠ።

ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ የበጎ ፈቃድና በጎ አድራጊነት ባህልን ለማዳበር ለአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ስልጠና ሰጠ።

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በአዋጅ 1113/2011 በተሰጠው ሀላፊነት መሰረት የበጎ ፈቃድና በጎ አድራጊነት ባህልን በህብረተሰቡ ውስጥ ለማስረጽ እና ውጤታማ ለማድረግ ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ጋር በጋራ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል።
በስልጠናው ላይ የተገኙት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ ለሰልጣኞች እንዳሉት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በህብረተሰቡ በእለት እለት ኑሮው ውስጥ ባህል መሆን እንዳለበት በማንሳት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊ እና በፖለቲካዊ ውስጥ በተለይ ደግሞ በስነ ምግባር የታነፀ፣ ህግና ስርዓትን የሚከተል፣ ማህበረሰቡን የሚያከብር፣ አገሩን የሚወድ ለሰዎች መልካም ነገርን በማድረግ የሚረካ ትውልድን የመፍጠር አቅም እንዳለው ገልፀዋል፡፡
በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ የተሰማራ ሰው መጥፎ ነገሮችን ከማድረግ የተቆጠበ ነው ያሉት ም/ዋና ደይሬክተሩ የሀሳብ ልዩነቶች ቢኖሩ እንኳን በንግግርና በውይይት ለመፍታት የሚጥር ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ሌላው እንደምሳሌ ያነሱት በመንግስት የተጀመሩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች እንደአርአያ በመውሰድ ተጠናክረው በህብረተሰቡ እንዲሁም በሲቪል ሶሳይቲው ውስጥ መሰራት እንዳለባቸው ገልፀዋል፡፡
በመጨረሻም ባለስጣን መስሪያ ቤቱ በጎ አድራጊዎች የሚገናኙበት ፕላት ፎርም (VMIS) አዘጋጅቶ ወደስራ መግባቱን እንዲሁም ሌሎች ስራዎችም እየተከናወኑ መሆኑን አንስተው በዩኒቨርስቲው በበጎ ፈቃደኞች እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማድነቅ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱም ከጎናቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በዩኒቨርስቲው በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ዘርፍ 20/25 የተባለ የበጎ አድራጎት ድርጅት እያከናወነ ያላቸውን ስራዎች አቅርቧል፡፡
ከሰሯቸው ስራዎች ውስጥ አዲስ ተማሪዎችን ወደ ዩንቨርስቲው ሲመጡ አቀባበል ማድረጉ እና በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲግባቡ፣ የአረጋውያን መንከባከቢያ ቤቶችን እንዲሁም በአዳማ የሚገኙ ሌሎች ማህበረሰቦችን በመጎብኘት የምክር አገልግሎት በመስጠት የዜግነት ሚናውን እየተወጣ መሆኑን አቅራቢዋ ተናግረዋል።