የተቋሙ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ መስፍን ሙሉነህ በበጎ ፍቃድ ዙሪያ በተዘጋጀ ስልጠና ላይ ባደረጉት ንግግር ተቋሙ ከተቋቋመበት ዓላማ መካከል በህብረተሰቡ ዘንድ የበጎ አድራጎትና በጎ ፍቃደኝነት ባሕል እንዲዳብር ማድረግ የሚገኝበት ሲሆን ይህንን ተፍጻሚ ለማድረግ በርካታ ተግባራት መከናወኑን ገልፀዋል::
አያይዘውም በጎ ፍቃድን ለማስረፅ ሃላፊነት እንደተሰጠው አንድ ተቋም አርዓያ ሆኖ መገኝት አስፍላጊ በመሆኑ የተቋሙ ሰራተኞች በፍላጎት ተሰባስበው እርስ በእርስ የሚረዳዱበት ሰውነት የሚባል በጎ ፍቃደኞች መረዳጃ ማህበር መመስረታቸውን ተናግረዋል። ሰራተኞች የበጎ ፊቃድ ስራ ላይ ሞዴል መሆን ይገባቸዋል ያሉት ሃላፊው እንደ ጅምር ሰውነት ማህበር የሰራቸው ስራዋች አበረታች መሆናቸውን እና በተለይም የተቋሙ ዝቅተኛ ተከፍይ የሆኑና በተለያየ ችግር ውስጥ ለሚገኙ የስራ ባልደረቦቻቸው በገንዘብና በዓይነት ያደረጉት ድጋፍ ተጠቃሽ መሆኑን አንስተዋል።


የስልጠና መድረኩም ዓላማ ሰዋች የበጎ ፍቃድ ስራ በልምድ ሳይሆን ፅንሰ ሃሳቡን ተረድተው ቢሰሩ የበለጠ ውጤት እንደሚያመጡ በማመን ለተቋሙ የሰውነት አባላት ስልጠና መዘጋጀቱን አቶ መስፍን ተናግረዋል። በስልጠናው ማጠቃለያ ንግግር ያደረጉት የተቋሙ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፍሲካው ሞላ በበኩላቸው በጎነት እና መልካምነትን የሚኖር ሰው በህይወቱም በስራውም ውጤታማ ነው ያሉት ሃላፊው በተቋም ደረጃም የሚከናወነው በጎ ተግባር ተቋም ላይ አስተዋፅኦ ስለሚያደርግ መደገፍና ከዚህ የተሻለ ስራ እንዲሰራ ማድረግ ይጠይቀናል ብለዋል። የበጎ ፍቃድ ስራ ሰዋች በፍፁም ቅንነት እና ከልብ በመነጨ ፍቃደኝነት የሚከውኑት መሆኑን አንስተው እንደሃገርም ከተጠቀምንበት በርካታ ተግዳሮቶቻችንን የምንጠግንበት ነው ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፍዋል።

