አገር በቀል ድርጅቶችን የውስጥ አቅማቸውን ለማጎልበት ንቁና ተጠያቂነትን ያለው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ለመፍጠር እንዲሁም በዴሞክራሲያዊ ስርዓት እና በግጭት አፈታት ስርዓት ላይ የራሳቸውን አስተፅኦ እንዲያደርጉ በጀርመን አግሮ አክሽን (GAA)፣) በዴቨሎፕመንት ኤክስፐርቲዝ ሴንተር (DEC) እና በራስ አገዝ ቡድን አሰራር ድርጅቶች ህብረት በኢትጵያ (CoSAP) በጋር ከአውሮፓ ህብረት ባገኙት ድጋፍ የሲ ኤስ ኤፍ ፕላስ መርሀግብር ለ101 አገር በቀል ድርጅቶች የሚውል 3.5 ሚሊዮን ዩሮ አቅም ለማሳዳግ የሚውል ፈንድ ለማስተላለፍ የሚየያስችል መርሀግብር ተካሄደ፡፡ በመርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የባለስልጣኑ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ እንዳሉት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ዘርፍ ሪፎርም ለማድረግ በርካታ ስራዎች ሲሰራ መቆየቱን አንስተው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በሃገረ መንግስት ግንባታው ጠንካራ፣ የበለፀገች፣ ዴሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብቶች የተከበሩባት ልዕልናዋ ከፍ ያለ አገር በመገንባት ሂደት ላይ ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ገልፀዋል፡፡

አያይዘውም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት መረጋገጥ የሚቻልበትን አውድ ለመፍጠር ባለፉት ዓመታት በተከናወኑት የሪፎርም ስራዎች ውስጥ አንዱ የህግ ማሻሻል ተደርጎ ለአምስት ዓመታት እየተተገበረ መሆኑን አንስተው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በርካታ መብቶችን ያጎናፀፈ ትልቅ ሀላፊነት የሰጠ በዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ እና በዘላቂ ልማት ላይ እንዲሁም የህብረተሰቡን የላቀ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
አዳዲስ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በተፈጠረላቸው ምቹ አውድ የሚጠበቅባቸውን ሀላፊነት እና አገር በመገንባት ረገድ እየሰሩ ያለው ስራ መልካም ቢሆንም ያሉባቸውን ችግሮችን ማረም እንደሚጠበቅባቸው ገለፀዋል፡፡
አገር በቀል ድርጅቶችን ማጠናከር የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ዓላማ ማሳካት መሆኑን ያነሱት ሃላፊው ይህ ፕሮግራም አገር በቀል ድርጅቶችን ለማጠናከር ታሳቢ ያደረገ ፕሮጀክት (GAA)፣) በዴቨሎፕመንት ኤክስፐርቲዝ ሴንተር (DEC) እና በራስ አገዝ ቡድን አሰራር ድርጅቶች ህብረት በኢትጵያ (CoSAP) ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጋር በመወያየት ከ36 የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ውስጥ 22 አዲስ የተቋቋሙ ድርጅቶች መሆናቸውን ም/ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡
አገር በቀል ድርጅቶች አቅማቸውን በመገንባት የህዝብን ጥቅም በዘላቂነት ለማረጋገጥ ውጤታማ ስራዎችን ማከናወን እንዳለባቸው በመግለፅ ፕሮግራሙ ውጤታማ እንዲሆን ባለስልጣን መስሪያቤቱ አስፈላጊውን ድጋፍና ቁጥጥር እንደሚያደርግ ም/ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ፋሲካው ሞላ አሳስበዋል፡፡ ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ለድርጅቶቹ በበጀት ድጋፍ ያደረገውን አውሮፓ ህብረት እንዲሁም ያሳተባበሩ ድርጅቶችን አመስግነዋል፡፡ የጀርመን አግሮ አክሽን (GAA) የአገር ውስጥ ተጠሪ ወ/ሮ ሳራ ወርቁ እንደገለፁት WHH በጀርመን አገር ውስት አንጋፋ አለም አቀፍ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት መሆኑን ጠቅሰው ይህ ድርጅት እ.ኤ.አ በ1972 የጀርመን አግሮ አክሽን ስም በኢትዮጰያ ተመዝግቦ እየሰራ ያለ ድርጅት ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡ WHH ከአውሮፓ ህብረት ባገኙት ድጋፍ የሲ ኤስ ኤፍ ፕላስ (CSF+) መርሀግብር ለአገር በቀል ድርጅቶች አዲስ የአቅም ግንባታ ፕሮግራም በመተግበር ላይ እንደሚገኝ አንስተዋል፡፡

