የ2017 የመጀመሪያ 100 ቀናት የሪፎርም ዋና ዋና የኢኮኖሚ አፈጻጸም ላይ በአራት ክፍሎች ተሰናድቶ በተዘጋጀው ሰነድ ላይ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን አመራሮችና ሰራተኞች ውይይት አካሄዱ፡፡ በውይይቱ ላይ የባለስልጣኑ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ መስፍን ሙልነህ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በንግግራቸውም የ2017 የመጀመሪያ 100 ቀናት የሪፎርም ዋና ዋና የኢኮኖሚ አፈጻጸም በአገር ደረጃ የተገመገመ መሆኑን ገልፀው በተቋማችን ደረጃም በተመሳሳይ ውይይት መደረጉ አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል፡፡

አያይዘውም የመጀመሪያ 100 ቀናት የሪፎርም ዋና ዋና የኢኮኖሚ አፈጻጸም ላይ አመራሩና ሰራተኛው የሚሰጠው አስተያየቶችና ጥያቄዎች ለቀጣይ በአገር ደረጃ ለሚከናወኑ የሪፎርም ስራዎች እንደግብዓትነት ለመጠቀምና የተሻለ ውጤቶችን ለማስመዝገብ ከፍተኛ ሚና እንደለው ጠቅሰዋል፡፡ በውይይቱ ላይም የተለያዩ አስተያየቶችና ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን በተነሱት ላይም ከአወያዮች ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

