በምስራቅ ሐረርጌ ያብዶ ጎጀሌ ወረዳ ከሰላሳ ስድስት ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተገነባው የውሃ ኘሮጀክት የተለያዩ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዋች በተገኙበት ተመርቋል።
የፍትህ ሚኒስቴር አማካሪ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ኡመድ ኡጁሉ በምረቃት ስነ-ስርዓት ላይ የተገኙ ሲሆን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን እንደ ተጠሪ ተቋም የሚመዘግባቸውን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን የመከታተልና የመደገፍ ሃፊነት አለብን በማለት ድርጅቱ የጀመራቸውን ማህበረሰብ ተኮር ስራዎች አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው አንስተው ከመንግስት አስፈለጊ እገዛ ለማድረግ ዝግጁ ነን ሲሉ ገልጸዋል፡፡
የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ ባደረጉት ንግግር ድርጅቱ በሃገሪቱ የተለያዩ አከባቢዋች እያከናወነ ያለው ተግባር አበረታች መሆኑን ገልፀው ዛሬ የተገነባውን የውሃ ኘሮጀክት ቀጣይነቱ እንዲረጋገጥ ማህበረሰቡ በሃላፊነት መጠበቅ አለበት ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
May be an image of 5 people and text
የካቶሊክ ሪሊፍ ሰርቪስ (CRS) ዳይሬክተር አቶ ዘመዴ አበበ ድርጅቱ የሰራቸው ስራዎችን ለመመልከት የተገኙ ባለድርሻ አካላትን አመስግነው ይህ ፕሮጀክት እንዲጠናቀቅ ድርጅቱ ካበረከተው አስተዋጽኦ በተጨማሪ የመንግስት ባለድርሻ አካላት እና የህዝብ ተሳትፎ ከፍተኛ መሆኑን አንስተዋል፡፡ ካቶሊክ ሪሊፍ ሰርቪስ (CRS) በኢትየየጵያ ከ65 ዓመታት በላይ ያስቆጠረ እና በተቀናጀ የልማት ስራዎች ላይ ተሰማርቶ እንደሚገኝ ያነሱት ዳይሬክተሩ የምረቃት ፕሮግራሙም ዓላማ ድርጅቱ የሰራቸው ስራዎችን ማስተዋወቅና ቀጣይነቱን ለማረጋገጥም መሆኑ አብራርተዋል፡፡ ድርጅቱ በመላው ሃገሪቱ በሁሉም ክልልች በውሃ፣በትምህርት፣በሰብዓዊ ድጋፍ ስራዎች፣በውሃ፣በጤናና እና በግብርና ስራዎች ላይ በመሰማራት በባለፉት ዓመታት በርካታ የማህበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ አድርጓል፡፡
በምስራቅ ሐረርጌ ያብዶ ጎጀሌ ወረዳ የተመረቀው የውሃ ፕሮጀክት ከሰባት ሺህ ዘጠኝ መቶ በላይ የማህበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ያደረገ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ ለትምህርት ቤት መስመር በመዘርጋትና ለእንስሳት አገልግሎት እንዲውል ገንዳዎችን የመገንባት ስራ ሰርቷል፡፡
ተጠቃሚዎች በሰጡት አስተያየትም ከዚህ ቀደም በውሃ እጦት ምክንያት በርካታ የቀበሌው ነዋሪዎች ችግር ላይ መውደቃቸውን ጠቅሰው አሁን ላይ ድርጅቱ ባስገነባው የውሃ ፕሮጀክት ተጠቃሚ መሆናቸውን እና እረፍት ማግኘታቸውን ገልጸዋል፡፡ አያይዘውም ከውሃ በተጨማሪ በኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የቁጠባ እና መነሻ ካፒታልና እንስሳትን በመስጠት የቀበሌው ነዋሪዎች በኢኮኖሚ እራሳቸውን እንዲችሉ የማድረግ ስራ መስራቱን ገልጸው ለዚህም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ ድርጅቱ በምስራቅ እና ምዕራብ ሐረርጌ ብቻ በ12 ቀበሌዎች በላይ የተለያዩ የልማት ስራዎችን መስራቱ ተጠቅሷል፡፡