የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከKVO INTERNATIONAL ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ፡፡

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከKVO INTERNATIONAL ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ፡፡

በጎ ፈቃድ አብሮነትና ሀገራዊ አንድነት እንዲጎለብት፣ ማኅበራዊ መስተጋብር እንዲጠናከር፣ ሰላምና ሀገራዊ መግባባት እንዲፈጠር፣ የልማት ዓላማ ግቡን እንዲመታ፣ የበጎ ፈቃድ ተግባር ለሀገር ካለው ጥቅም አንፃር ባህል እንዲሆን፣ በጎ ፈቃደኞች ለሀገር እና ለወገን ያላቸውን ፍቅር በተግባር እንዲገልጹ ለማስቻል ዋንኛ መሳሪያ ነው፡፡
ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በአዋጅ 1113/2011 ከተሰጡት ስልጣንና ተግባር መካከል አንዱ የበጎ ፈቃደኝነትን ባህልና እንቅስቃሴ ማበረታታት፣ የበጎ ፈቃደኝነትን በተመለከተ የስርጸት ስራ መስራት አንዱ ሲሆን የተሰጠውን ሀላፊነት በአግባቡ ለመወጣት እና በጎ ፈቃደኝነት በማህበረሰቡ ውስጥ ባህል ለማድረግ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡
ይህንንም ተግባር ወደፊት ለማስቀጥል ባለስልጣኑ KOREA INTERNATIONAL VOLUNTEER ORGANIZATION (KVO INTERNATIONAL) ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
በስምምነቱ ወቅት የተገኙት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ም/ ዋና ዳይሬክተሮች አቶ ፋሲካው ሞላ ፣ አቶ መስፍን ሙልነህ እና ከKOREA INTERNATIONAL VOLUNTEER ORGANIZATION (KVO INTERNATIONAL) ካንትሪ ዳይሬክተር አቶ ሚኪስ ግርም ተገኝተዋል፡፡
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ም/ ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ እንዳሉት በመጀመሪያ በጎ ፈቃደኝነት ለማስተዋወቅ ከባለስልጣኑ ጋር አብሮ በጋራ ለመስራት ዝግጁ በመሆናቸው ምስጋናቸውን በማቅረብ በኢትየጵያ የበጎ ፈቃደኝነት ጉዳይ በማህበረሰቡ ውስጥ ባህል ሆኖ እንዲጎለብት ስርዓት ተዘርግቶ ተግባራዊ እንዲሆን ስራዎችን ለመስራት ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ እንደሚጠበቅ ገልፀዋል፡፡
ሌላው ያነሱት ም/ዋና ዳይሬክተሩ ባለስልጣን መስሪያቤቱ የተሰጠውን ሀላፊነት ለመወጣት ከተለያዩ አካላት ጋር በመነጋገር በበጎ ፈቃደኝነት ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር በጎ ፈቃደኝነት የሚመራበት ፖሊሲ፣ መመሪያዎች እና ማንዋሎች የማዘጋጀት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን አንስተዋል፡፡
አለም አሁን ከደረሰችበት ስልጣኔ አንጻር ወጣቱ እንዲሁም በውጭ የሚገኘው ዲያስፖራው በቴክኖሎጂ በማገዝ በጎ ፈቃደኝነትን በኦን ላይን ለማድረግና ግንዛቤ ለመፍጠር ጥረቶች በማድረግ ከተባባሪ አካላት ጋር በመሆን(vmis) ፕላት ፎርም በማዘጋጀት ተግባራዊ መደረጉን ገልፀው የዛሬ ፕሮጀክትም ዋና አላማ KOREA INTERNATIONAL VOLUNTEER ORGANIZATION (KVO INTERNATIONAL) ድርጅትም ከበጎ ፈቃደኝነት ጋርም በተያያዘ ልምድ ያለው በመሆኑ እና የበጎ ፈቃደኝነት ስራን ቀለል ለማድረግ የሞባይል አፕልኬሽን በመጠቀም አቅምና እውቀት ባለው መንገድ ቴክኖሎጂን በመጠቀም በበጎ ፈቃደኝነት ላይ ለወጣቱ ግንዛቤ ለመፍጠር ስልጠናዎችን እንዲያገኙ የሚያስችል መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በጎ ፈቃደኝነት በኢትዮጵያ ውሰጥ ስርዓት ተገንብቶለት የለት እለት ልምምድ እስኪሆን ድረስ አስፈላጊውን ስራ የሚሰራ ተቋም መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በመጨረሻም ይህ ፕሮጀክት ውጤታማ እንዲሆን የቀረውን ጊዜ የሚያካክስ ስራዎችን እንዲሰሩ አሳስበዋል፡፡
ከKOREA INTERNATIONAL VOLUNTEER ORGANIZATION (KVO INTERNATIONAL) ካንትሪ ዳይሬክተር አቶ ሚኪያስ ግርማ እንዳሉት የዛሬው የስምምነት ሰነድ እንድንፈራረም በበጎ ፈቃደኝነት ላይ ስራዎችን በጋራ ለመስራት የባለስልጣኑ አመራሮች ከፍተኛ ድጋፍ ስላደረጉ ምስጋናቸውን በማቅረብ ድርጅታቸው በኢትየጵያ ከተቋቋመ ረጅም አመት ማስቆጠሩን ገልፀዋል፡፡
ካንትሪ ዳይሬክተሩ አያይዘውም በጎ ፈቃደኝነት ላይ ስራዎችን ለመስራት ሁለት መሰረታዊ ጉዳዮች አሉ አንደኛው ሪሶርስ ሲሆን ሁለተኛው የአመለካከት ለውጥ ነው ሲሉ የፕሮጀክቱም አካል ዋንኛው በበጎ ፈቃደኝነት ላይ የአመለካከት ለውጥ ለማምጣት በአመለካከት ላይ መሰራት ነው ብለዋል፡፡


ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ በደቡብ ኢትዮጵያ ኮሬ ዞን በእናቶችና ህጻናት ዘርፈ ብዙ የልማት ድርጅት (MCMDO) የተሰሩ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል፡፡


በለውጡ ዓመታት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን በማጠናከር ረገድ ውጤታማ ተግባራት ተከናውነዋል'' ክቡር አቶ አደም ፋራህ

በለውጡ ዓመታት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን በማጠናከር ረገድ ውጤታማ ተግባራት ተከናውነዋል'' ክቡር አቶ አደም ፋራህ

በለውጡ ዓመታት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን በማጠናከር ረገድ ውጤታማ ተግባራት መከናወናቸውን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ሃላፊ ክቡር አቶ አደም ፋራህ ገለጹ፡፡
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችና የፌዴራል ባለድርሻ አካላት የትብብርና የቅንጅት መድረክን በተመለከተ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡
በውይይቱ ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ሃላፊዎች፣ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ተወካዮች፣ የፌዴራል ተቋማት ተወካዮችን ጨምሮ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ሃላፊ ክቡር አቶ አደም ፋራህ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፥የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ፣ ሰላም ግንባታ እና ግጭት አፈታት፣ በዜጎች ተሳትፎና ተጠቃሚነት፣ በዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ እንዲሁም በአካባቢ ጥበቃ ጉልህ ሚና ይጫወታሉ፡፡
ድርጅቶቹ ሚናቸውን በላቀ ደረጃ እንዲወጡ መንግሥት በርካታ የሪፎርም ተግባራት ማከናወኑን ጠቁመው፤ በዚህም አበረታች ውጤቶች መገኘታቸውን አንስተዋል።
በተለይም አሳሪ ህጎችና አዋጆችን በማሻሻል ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በተሻለ መንቀሳቀስ የሚችሉበት አውድ መፈጠሩን ገልጸዋል፡፡
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር፣ በስራ ዕድል ፈጠራና ሌሎችም ሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከቱ መሆኑንም ነው ያነሱት።

በቀውስ ጊዜም አስቸኳይ ድጋፎችን በማስተባበርና ተደራሽ በማድረግ ረገድ ተጠቃሽ ተሳትፎ ማድረጋቸውን ጠቁመው፤አገራዊ ጉዳዮች ላይ ተሳትፏቸው ይበልጥ ሊጠናከር እንደሚገባም አመልክተዋል።
በሀገር ግንባታ ሂደትም ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ድርሻ የላቀ ሊሆን እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥተዋል።

ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የሚጫወቱትን ሚና ይበልጥ እንዲያሳድጉ መሰል የቅንጅትና ውይይት መድረክ ፋይዳው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል።

መንግሥት ለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የሚሰጠውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።
የባለስልጣን መስሪያቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ ባስተላለፉት መልዕክት የኢትዮጵያ መንግስት ባለፉት የለውጥ ዓመታት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ዘርፍን በማጠናከር በሲቪል ማህበራት እንቅስቃሴ የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል የፖሊሲ፣ የህግና የተቋማዊ ሪፎርም እርምጃዎች በስፋት የወሰደ መሆኑ አንስተው በዘርፉም ቀላል የማይባሉ ውጤቶችን ማስመዝገብ መቻሉን አንስተዋል፡፡
በዚህ ዘርፍ እየተካሄደ ያለውን ሪፎርም የበለጠ ለማጠናከር ከፌዴራል ጀምሮ እስከ ክልል ድረስ በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እና ባለድርሻ አካላት መካከል በትብብርና በቅንጅት መስራት የሚቻልበት አውድ እንዲፈጠር በከፍተኛ የመንግስት እርከን የሚመሩ አደረጃጀቶችን ለመፍጠር ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡


በመልካም አስተዳደርና መሰል ዘርፎች ላይ ከሚሰሩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችል የውይይት መድረክ ተካሄደ።


የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከሰላም ሚኒስቴር ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ።

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከሰላም ሚኒስቴር ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ።

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከሰላም ሚኒስቴር ጋር ሀገራዊ የሰላም ግንባታና ብሄራዊ መግባባትን የሚያረጋግጥ ተግባራትን በጋራ ለማከናወን የትብብር ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በሰላም ግንባታ ስራዎች ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት እና ሀገራዊ መግባባትን ለመፍጠር ትልቅ ሚና አላቸው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው በተለይም ከሪፎርም በኋላ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጁ መሻሻልና ሌሌች ተያያዥ ተግባራት በዘርፉ ለውጥ እንዲመጣ የመንግስትን ቁርጠኝነት ያመላክታል ብለዋል፡፡
ክቡር ከይረዲን ተዘራ(ዶ/ር) ይህ ስምምነት የሰላም ስራ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ርብርብ የሚጠይቅ በመሆኑ በፍቃደኝነት የሚሰሩ ተቋማት፣ ቡድኖችና ግለሰቦችን ለማበረታታትና አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ በሰላም ግንባታ ሂደት ላይ የድርሻቸውን እንዲወጡ የሚያግዝ ነው ብለዋል፡፡
ከባለስልጣኑ ጋር በቅንጅት መስራት ለዘላቂ ሰላምና ጠንካራ ሀገር ግንባታ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያለው መሆኑን የጠቀሱት ዶ/ር ከይረዲን ለስኬቱ ሚኒስቴር መ/ቤቱ ቁርጠኛ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ በበኩላቸው በተቋማችን የሰላም እሴት ግንባታ ላይና የግጭት አፈታት ስራዎችን ለመስራት የተመዘገቡ 349 የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች መኖራቸው ጠቅሰው የሲቪል ማህበረሰቡን በማቀናጀት ለዘላቂ ሰላም ግንባታ የድርሻቸውን ለመወጣት የተጀመሩ ስራዎችን በማጠናከር እንደሚሰሩም ገልጸዋል፡፡ ሰምምነቱ በሁለቱ ተቋማት መካከል ዘላቂ ሰላምና ጠንካራ ሀገረ መንግስት ለመገንባት የሚደረገውን እንቅስቃሴ እንደሚያግዝም የተገለፀ ሲሆን በቀጣይ የጋራ ተግባራትን ለመምራት የጋራ የቴክኒክ ኮሚቴ ለማቋቋምም ተስማምተዋል።

Click the button

የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከሰብዓዊና ማህበራዊ ጠቀሜታው ባለፈ የተረጋጋ ማህበረሰብን ለመፍጠርና ዘላቂ የኢኮኖሚ ልማትና እድገት እንዲኖር የሚያስችል አገልግሎት መሆኑን የባለሰስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ ጠቆሙ፡፡

የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከሰብዓዊና ማህበራዊ ጠቀሜታው ባለፈ የተረጋጋ ማህበረሰብን ለመፍጠርና ዘላቂ የኢኮኖሚ ልማትና እድገት እንዲኖር የሚያስችል አገልግሎት መሆኑን የባለሰስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ ጠቆሙ፡፡

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከባህር ተሻጋሪ የበጎ ፈቃደኞች ድርጅት (Voluntary Service overseas VSO) ጋር በመተባበር ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተለያዩ ካንፓሶች ለተውጣጡ ተማሪዎች በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ ትኩረት ያደረገ የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

ስልጠናው የዩኒቨርሲቲውን ተማሪዎች አቅም በማጎልበት በዩንቨርሲቲው የሚገኙ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ክበባትን ለማጠናከርና በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዘንድ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ባህልን ለማሳደግ ታልሞ የተዘጋጀ ነው፡፡

ስልጠናውን ያስጀመሩት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ የበጎ ፈቃድ አገልግሎትና በጎ አድራጎት ተግባራት ያለምንም ልዩነት የሰብዓዊነት መርህን ብቻ መሰረት ባደረገ መልኩ የሚከወን ተግባር መሆኑን ጠቁመው  የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከሰብዓዊና ማህበራዊ ጠቀሜታው ባለፈ የማህበረሰቡን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮችን በመቅረፍ የተረጋጋ ማህበረሰብን ለመፍጠርና ዘላቂ የኢኮኖሚ ልማትና እድገት እንዲኖር የሚያስችል መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

አክለውም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በአዋጅ የተሰጠውን ተግባርና ኃላፊነት ለመወጣት በዋነኛነት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በበጎ ፈቃድ አገልግሎትና የበጎ አድራጎት ተግባራት ላይ በስፋት እንዲሳተፉና በጎ ፍቃደኛ ትውልድን ማበረታታት ይቻል ዘንድ በሀገር ውስጥ ለሚገኙ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን መስጠት እና የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ክበባትን ማጠናከር ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

ባህር ተሻጋሪ በጎ ፈቃደኞች ወይም በእንግሊዘኛው አጠራር Voluntary service overseas (VSO) የኢትዮጵያ ተወካይ አቶ ተመስገን ዓለሙ በበኩላቸው ድርጅታቸው Voluntary service overseas VSO ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጋር በመተባበር የበጎ ፍቃደኝነት አገልግሎት እንዲስፋፋ በመስራታቸው መደሰታቸውን ገልጸው ስልጠናው በጎ ፈቃድና በጎ አድራጊነትን በሚመለከት ጠቃሚ ግንዛቤ የሚጨብጡበት እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡ አያይዘውም ተማሪዎች ከዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸው ጋር አብረው የበጎ ፈቃድና የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን በጊዜ እንዲያስቡትና በበጎ ፍቃድ ተግባራት ላይ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ በር የሚከፍት መሆኑን አንስተው ተማሪዎች ስልጠናውን ከወሰዱ በኋላ ከባለሰልጣን መስሪያ ቤቱ እና ከ VSO ጋር በጋራ በመሆን የግንዛቤ ማስስበጫ ስልጠናዎችን ለዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች የሚሰጡበት ትልቅ እድል የሚፈጥር እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ ተገኝኝው የማጠቃለያ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ በበኩላቸው በጎ ፈቃድ አብሮነትን፣ እርስ በርስ መደጋገፍን፣ አንድነትንና መተሳሰብን የሚያመጣ በመሆኑ በጎ ፈቃደኛ ትውልድ መገንባት እንደሚያስፈልግ ጠቁመው እንደሀገር ያሉ ስብራቶችን ለመጠገን በጎ ፈቃድ አገልግሎት ትልቅ ሚና እንዳለው ጠቁመዋል፡፡ የበጎ ፈቃደኝነት ጉዳይ ሀገርን የመገንባት ትልቅ ጉዳይ መሆኑን ያነሱት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ የበጎ ፈቃደኝነት አገልግሎት በተለይም በትምህርት ላይ ለሚገኙ ወጣቶችና ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ቢሰጥ በጎ ፍቃድን ባህሉ ያደረገ ትውልድን የሚፈጥርና ሀገርን የሚገነባ እንደሆነ አንስተው በተለይ በዩኒቨርሲቲዎችና በወጣቶች ላይ  መስራት የበለጠ ውጤት እንደሚያመጣ ጠቁመዋል፡፡

አክለውም የበጎ ፈቃደኝነት ስራ ትውልድን የመገንባት ስራ ስለሆነ ለሌሎች ግንዛቤውን ከመፍጠር ባሻገር በበጎ ፍቃድ ተግባራት ለይ መሰማራት ተገቢ እንደሆነ የጠቆሙ ሲሆን በዚህ ረገድ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ድጋፍ እንደሚያደርግ እና የዩኒቨርሲቲው አመራርም ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን አንስተዋል፡፡ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በዩኒቨርሲቲው የሚሰራው ስራ ስኬታማ መሆን በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች  የሚደረገውን ጥረት ውጤታማ ለመሆኑ ማሳያ ሊሆን የሚችል በመሆኑ አስፈላጊው እገዛ እንደሚደረግም አክለው ገልጸዋል፡፡

ስልጠናውን ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የበጎ ፈቃድ ማጎልበትና ትብብር መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ አሉላ ሚሊዮን፣ ከVoluntary Service Overseas VSO አቶ ጌታያውቃል አብርሃም እንዲሁም ከሊቭ ፎር ጀነሬሽን ዳይሬክተር አቶ ዮናስ ብርሃኑ የሰጡ ሲሆን Essence of voluntarism, Social Accountability, Social Inclusion and Gender in Volunteerism, VSO and Volunteerism፣ Facilitations Skill በሚሉ ርዕሶች ላይ ንድፈ ሀሳብንና ተግባርን ባካተተ መልኩ ተማሪዎች ስልጠናውን እንዲወስዱ ተደርጓል፡፡


የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በስራዎቻቸው ላይ በጎፈቃደኝነት ማሳተፍ እና የበጎ ፈቃደኝነት ፕሮጀክቶችን ቀርፀው መተግበር እንዳለባቸው ተገለጸ፡፡

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በስራዎቻቸው ላይ በጎፈቃደኝነት ማሳተፍ እና የበጎ ፈቃደኝነት ፕሮጀክቶችን ቀርፀው መተግበር እንዳለባቸው ተገለጸ፡፡


አሜን በጎ አድራጎት ድርጅት በባለስልጣን መስርያቤቱ ከፍተኛ አመራሮች ተጎበኘ፡፡

አሜን በጎ አድራጎት ድርጅት በባለስልጣን መስርያቤቱ ከፍተኛ አመራሮች ተጎበኘ፡፡

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከፍተኛ አመራሮች እና ከተለያዩ የስራ ክፍል የተውጣጡ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች አሜን በጎ አድራጎት ድርጅት የሰራቸውን ስራዎች ተመልክተዋል፡፡ አሜን የበጎ አድራጎት ድርጅት በሲቪል ማሰህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በ2009 ዓ.ም በአራት በጎ ፍቃደኞች ህፃናትን መሰረት አድርጎ የተመሰረተ ድርጅት መሆኑን የድርጅቱ መስራችና ስራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን ሀብቴ ተናግረዋል ፡፡
አቶ ሰሎሞን አክለውም ይህ ድርጅት ሲመሰረት ምንም አይነት ድጋፍና በጀት ያልነበረው ቢሆንም ህፃናት በየመንገዱ ተጥለው ፣ በየጎዳናው ተወልደው በመመልከታቸው እንዲሁም በርካታ ህፃናት እንደመለመኛነት ሲጠቀሙባቸው በማየታችን በበጎ ፍቃደኘነትና በራስ ተነሳሽነት ይህን ስራ ሊጀምሩ መቻላቸውን ተናግረዋል ፡:
በ25 ህፃናት እንክብካቤ የተጀመረው የህፃናት እንክብካቤ ዛሬ ላይ ሃምሳ ያህል ህፃናት በድርጅቱ ድጋፍ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
ህፃናቱ ከመደበኛ ትምህርታቸው ጎን ለጎን የእደ ጥበብ ሙያዎችን እንደሚማሩና የእደጥበብ ስራዎቻቸውም እንደገቢ ማስገኛ በመሸጥ ለድርጅቱ ተጨማሪ ገቢ ማስገባት መቻላቸውን የተናገሩ ሲሆን በኬክ ፣እንጀራ እንዲሁም ደቦ መጋገርያ በመክፈት የድርጅቱን የተለያዩ ወጪዎቹን እየሸፈኑ እንደሚገኙም ነግረውናል ፡፡
ይሁን እንጂ ድርጅቱ የሚሰራበት ቦታ ከመጥበቡ የተነሳ ከህፃናት መኖርያ ጀምሮ በገቢ ማስገኛነት የምንሰራቸው ስራዎች በኪራይ እንደመሆኑ መጠን የወር ወጪያችን ፈታኝ እንዲሆን አድርጎታል ብለዋል ፡፡ በዚህም አጋጣሚ የሚመለከተው አካል ይህን ችግራችንን ድርጅታችን ድረስ መጥቶ በመጎብኘትና በማረጋገጥ ድጋፍ እንዲያደርግልን ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ብለዋል ፡፡
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣንም ድርጅቱ ከተመሰረተበት ጊዚያት ጀምሮ በርካታ ሙያዊ ድጋፎችን ሲያደርግልን ነበር ያሉት አቶ ሰለሞን ዘንድሮም የተሽከርካሪ ድጋፍ በማድረግ አጋርነቱን ቀጥሏል ለዚህም እጅግ ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል ፡፡
በጉብኝቱም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ የተገኙ ሲሆን ሰውን መሰረት በማድረግ እንዲሁም ትውልድን በመልካም ስነምግባር ይዞ እንዲያድግ ለመቅረፅ እየተሰራ ያለው ስራ የሚያኮራ በመሆኑ ይህ ተግባር ከሁላችን የሚጠበቅ በመሆኑ ከወትሮው በተሻለ የባለስልጣን መስርያቤታችን ለድርጅቱ ድጋፍ ማድረጉ የሚቀጥል ይሆናል ብለዋል ፡፡


Strategic leadership ዙሪያ ለተቋሙ አመራርና ሰራተኞች ስልጠና ተሰጠ ፡፡ ስልጠናውን የሰጡት የተከበሩ ፕሮፌሰር ምህረቱ ሻንቆ የህዝብ ተወካዬች ምክር ቤት አባል እና የኢፌደሪ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የቦርድ አባል ናቸው፡፡

Strategic leadership ዙሪያ ለተቋሙ አመራርና ሰራተኞች ስልጠና ተሰጠ ፡፡
ስልጠናውን የሰጡት የተከበሩ ፕሮፌሰር ምህረቱ ሻንቆ የህዝብ ተወካዬች ምክር ቤት አባል እና የኢፌደሪ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የቦርድ አባል ናቸው፡፡

ከስልጠናው በተጨማሪ የሰዎች ለሰዎች የስራ እንቅስቃሴ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
በስልጠናው ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢፌደሪ ፍትህ ሚኒስቴር አማካሪ ሚኒስት ዴኤታ አቶ ዑሙድ ኡጁሉ ባለስልጣን መስሪያቤቱ የጀመራቸው የሪፎርም ስራዎች አበረታች መሆናቸውን በመግለጽ ለለውጡ ቀጣይነት እንደዚህ አይነት ስልጠናዎች አስፈላጊ ናቸው ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የባለስልጣን መስሪያቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ በበኩላቸው ተቋሙ የሰራተኞችን የመፈጸምና የማስፈጸም አቅም ለማጎልበት በርካታ ተግባራት እያከናወነ መሆኑን ገልጸው ሰዎች ለሰዎች ድርጅትም ለትውልድ ተሻጋሪ የሆኑ እና ከመንግስት የልማት እቅዶች ጋር የተቀናጁ ስራዎች መስራታቸው ምሳሌ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡
አያይዘውም ሰዎች ለሰዎች ድርጅት ይህ ስልጠና እንዲሳካ ላደረጉት ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋለ፡፡
በስልጠናው ማጠቃለያ በዲሞክራሲ ማስተባበሪያ ማዕከል የሲቪል ባህል ግንባታ ዳይሬክተር አቶ ደስታ ብዙአየሁ በሰጡት አስተያየት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ዘርፍ ሁለት መሰረታዊ ጉዳዬችን እንዲያሟሉ ይጠበቃል በዓላማቸው መሰረት ተግባራቸውን ማከናወን እና ከፖለቲካ ነጻና ገለልተኛ ሆነው መስራት ይንን ባህሪ ከሰዎች ለሰዎች ድርጅት በመመልከቴ ደስታ ተሰምቶኛል በሌሎች የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችም ይሄ ይጠበቃል ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
የሰዎች ለሰዎች ድርጅት የዛሬ 44 ዓመት በዶ/ር ካርል መመስረቱን የገለጹት የድርጅቱ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ሙሉነህ ቶለሳ ድርጅቱ በገጠር የተቀናጀ ልማት ላይ ማለትም በውሃ፣በትምህርት፣በሰብዓዊ ድጋፍ፣የአከባቢ ጥበቃ እና የሰውሃብት ልማት ላይ ትኩረት አድርጎ በመስራት ከስድስት ሚሊየን ህዝብ በላይ ተደራሽ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
ስልጠናው እራሳችንን እንድንመለከትና በቀጣይ ተቋሙ ባስቀመጠው ራዕይ እና በተሰጠን የስራ ሃላፊነት የድርሻችንን እንድንወጣ የሚያግዝ ነው ሲሉ ሰልጣኞች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

Click the button

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን አለም አቀፍ የሴቶች ቀንን በተለያዩ ፕሮግራሞች አክብሯል፡፡

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን አለም አቀፍ የሴቶች ቀንን በተለያዩ ፕሮግራሞች አክብሯል፡፡

በፕሮግራሙ በዲሞክራሲ ማስተባበሪያ ማዕከል የሲቪል ባህል ግንባታ ዳይሬክተር አቶ ደስታ ብዙአየሁን ጨምሮ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ፣ም/ዋና ዳይሬክተር ፣የተቋሙ ሰራተኞችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ እንዳሉት በሃገር አቀፍ ደረጃ የዘንድሮው የሴቶች ቀን አከባበር ከወትሮው በተለየ መልኩ የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሴቶች ላይ በተጨባጭ የተሰሩ ስራዎችን ምልከታ በማድረግ፣በአካል ከማህበረሰቡ ጋር በመገኘት እና የሀገራችን ሴቶችን ፍላጎቶችና አንገብጋቢ ችግሮች ከራሳቸው አንደበት በማዳመጥ የተካሄደ እንደነበር ገልጸው የዚህን አመት አለም አቀፍ የሴቶች ቀን የተገኙ መልካም ተሞክሮዎች በመቀመር ወደ ሌሎች አካባቢ እንዲስፋፉ ለማድረግ እና ሁሉም ባለድርሻ አካላት የራሳቸውን ድርሻ በመውሰድ ሴቶችን በሁሉም ዘርፍ በማብቃት ሚናቸውን መወጣት እንዳለባቸው አቅጣጫ መቀመጡን አንስተዋል፡፡

ከዚህ ረገድ በባለስልጣን መስሪያቤቱ ተመዝግበው የሚንቀሳቀሱ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ዓላማቸውን ለማሳካት ሲንቀሳቀሱ የሴቶችና የህጻናትን እንዲሁም ተጋላጭ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችን አካተው እንዲሰሩ ማድረግ እና ቀኑን ከማክበር በዘለለ በባለስልጣን መስሪያቤቱ ያሉ ሴት ሰራተኞችን አቅም በማጎልበት ፣ ውጤታማ ሴቶች ወደ ፊት በማምጣት፤የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች በመቅረፍ እና የስርዓት ጾታ እኩልነትን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ውስጥ የወንዶችም ሚና እንዲጎብት በማበረታታት ረገድ በትኩረት መስራት ይጠይቃል ብለዋል፡፡
የተቋሙ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዬች አካቶ ትግበራ ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ትግስት አቡዬ በበኩላቸው የዘንድሮው አለም አቀፍ የሴቶች ቀን /ማርች 8/ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ114ኛ ጊዜ “For ALL Women and Girls: Rights. Equality. Empowerment.” በሚል መሪ ቃል እና በሃገራችን ደግሞ ለ49ኛ ጊዜ “ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ሁሉን አቀፍ ለውጥ በሴቶች ተሳትፎ ይረጋገጣል’’ በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር ገልጸው የሴቶችን ሁንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሁሉም ረገድ መከናወን የሚገባቸው ተግባራትን በመለየት ትኩረት ተሰጥቶት ይሰራል ብለዋል፡፡
በፕሮግራሙ ላይ ወ/ሮ ማርያ ሙኒር የሴቶች ማረፍያ ድርጅት መስራችና ስራ አስኪያጅ የህይወት ተሞክሯቸውን ለሰራተኞች ያካፈሉ ሲሆን በንግግራቸውም በምንም ሁኔታ ውስጥ ሴቶች ተስፋ መቁረጥ እንደሌለባቸውና አልችልም የሚል መንፈስ ሊኖራቸው እንደማይገባ አንስተዋል፡፡
ሌላው በእናት ባንክ ለሰራተኞች የቁጠባ ባህልን እንዲያጎለብቱ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡