አሜን በጎ አድራጎት ድርጅት በባለስልጣን መስርያቤቱ ከፍተኛ አመራሮች ተጎበኘ፡፡
የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከፍተኛ አመራሮች እና ከተለያዩ የስራ ክፍል የተውጣጡ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች አሜን በጎ አድራጎት ድርጅት የሰራቸውን ስራዎች ተመልክተዋል፡፡ አሜን የበጎ አድራጎት ድርጅት በሲቪል ማሰህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በ2009 ዓ.ም በአራት በጎ ፍቃደኞች ህፃናትን መሰረት አድርጎ የተመሰረተ ድርጅት መሆኑን የድርጅቱ መስራችና ስራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን ሀብቴ ተናግረዋል ፡፡
አቶ ሰሎሞን አክለውም ይህ ድርጅት ሲመሰረት ምንም አይነት ድጋፍና በጀት ያልነበረው ቢሆንም ህፃናት በየመንገዱ ተጥለው ፣ በየጎዳናው ተወልደው በመመልከታቸው እንዲሁም በርካታ ህፃናት እንደመለመኛነት ሲጠቀሙባቸው በማየታችን በበጎ ፍቃደኘነትና በራስ ተነሳሽነት ይህን ስራ ሊጀምሩ መቻላቸውን ተናግረዋል ፡:
በ25 ህፃናት እንክብካቤ የተጀመረው የህፃናት እንክብካቤ ዛሬ ላይ ሃምሳ ያህል ህፃናት በድርጅቱ ድጋፍ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
ህፃናቱ ከመደበኛ ትምህርታቸው ጎን ለጎን የእደ ጥበብ ሙያዎችን እንደሚማሩና የእደጥበብ ስራዎቻቸውም እንደገቢ ማስገኛ በመሸጥ ለድርጅቱ ተጨማሪ ገቢ ማስገባት መቻላቸውን የተናገሩ ሲሆን በኬክ ፣እንጀራ እንዲሁም ደቦ መጋገርያ በመክፈት የድርጅቱን የተለያዩ ወጪዎቹን እየሸፈኑ እንደሚገኙም ነግረውናል ፡፡
ይሁን እንጂ ድርጅቱ የሚሰራበት ቦታ ከመጥበቡ የተነሳ ከህፃናት መኖርያ ጀምሮ በገቢ ማስገኛነት የምንሰራቸው ስራዎች በኪራይ እንደመሆኑ መጠን የወር ወጪያችን ፈታኝ እንዲሆን አድርጎታል ብለዋል ፡፡ በዚህም አጋጣሚ የሚመለከተው አካል ይህን ችግራችንን ድርጅታችን ድረስ መጥቶ በመጎብኘትና በማረጋገጥ ድጋፍ እንዲያደርግልን ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ብለዋል ፡፡
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣንም ድርጅቱ ከተመሰረተበት ጊዚያት ጀምሮ በርካታ ሙያዊ ድጋፎችን ሲያደርግልን ነበር ያሉት አቶ ሰለሞን ዘንድሮም የተሽከርካሪ ድጋፍ በማድረግ አጋርነቱን ቀጥሏል ለዚህም እጅግ ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል ፡፡
በጉብኝቱም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ የተገኙ ሲሆን ሰውን መሰረት በማድረግ እንዲሁም ትውልድን በመልካም ስነምግባር ይዞ እንዲያድግ ለመቅረፅ እየተሰራ ያለው ስራ የሚያኮራ በመሆኑ ይህ ተግባር ከሁላችን የሚጠበቅ በመሆኑ ከወትሮው በተሻለ የባለስልጣን መስርያቤታችን ለድርጅቱ ድጋፍ ማድረጉ የሚቀጥል ይሆናል ብለዋል ፡፡


