አስቸኳይ መግለጫ ለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በሙሉ
አስቸኳይ መግለጫ
ለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በሙሉ
የኢትዮጵያ መንግስት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ከየትኛውም ህጋዊ ምንጭ ሃብት በማሰባሰብ በህጋዊና ሞራላዊ በሆኑ ዓላማዎች ላይ መስራት እንደሚችሉ የሚደነግግ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ 1113/2011 አውጥቶ ተግባራዊ እያደረገ መሆኑ ይታወቃል፡፡
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ከአገር ውስጥም ሆነ ከውጭ ምንጭ የሚያገኙትን ሃብት በህግ መሰረት በመጠቀም በስራቸው የህዝብን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የሚገባቸው መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ ይህንንም ለማሳካት ባለስልጣን መ/ቤታችን አስፈላጊውን የክትትልና ቁጥጥር ስራዎችን እያከናዎነ ይገኛል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞም ባለስልጣን መ/ቤቱ በየጊዜው በዘርፉ የሚከሰቱ አገራዊና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎችን በቅርበት በመከታተልና አንድምታቸውንና ተፅዕኖዎቻቸውን በመተንተን አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲሁም ክትትል ያደርጋል፡፡
ከሰሞኑ በአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (ዩ.ኤስ.ኤይድ) በኩል የእርዳታ ማቆም ውሳኔ የተወሰነ መሆኑን መረዳት ተችሏል፡፡ ባለስልጣን መ/ቤታችን ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለ ሲሆን ዝርዝር ሁኔታዎችን መሰረት በማድረግ በቀጣይ አስፈላጊው ድጋፍና ክትትል የሚያከናዎን ይሆናል፡፡ ይህ እንደተጠበቀ ሆነ በአሁኑ ወቅት ከዩ.ኤስ.ኤይድ የገንዘብ ድጋፍ የሚያገኙ ድርጅቶች ይህንን ውሳኔ ተከትሎ ያለ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ግልፅ ፍቃድ ንብረት የማስተላለፍ፣ የማስወገድ ወይም የመሸጥ ወይም ከመደበኛ/ፕሮጀክት ስራዎች ጋር ተያያዥ ከሆኑ ጉዳዮች ውጭ በማናቸውም መልኩ ሃብትና ገንዘብን ለሶስተኛ ወገን ማስተላለፍ የተከለከለ መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን፡፡ ይህንን ማሳሰቢያ በመተላለፍ በሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች ላይ ባለሥልጣን መ/ቤቱ ተገቢውን እርምጃ የሚወስድ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ጥር 27 ቀን 2017
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ
በባለስልጣን መስሪያቤቱ እያንዳንዱን ተግባር በቴክኖሎጂ ለማስደገፍ የጀመረው ስራ አበረታች መሆኑን በህዝብ ተወካዬች ምክር ቤት የህግና ፍትህ ጉዳዬች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ተገለጸ፡፡

በባለስልጣን መስሪያቤቱ እያንዳንዱን ተግባር በቴክኖሎጂ ለማስደገፍ የጀመረው ስራ አበረታች መሆኑን በህዝብ ተወካዬች ምክር ቤት የህግና ፍትህ ጉዳዬች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ተገለጸ፡፡
የቋሚ ኮሚቴው አባላቱ በባለስልጣን መስሪያቤቱ በባለፉት ስድስት ወራት የተከናወኑ ተግባራትን በአካል በመገኘት ተመልክተዋል፡፡
የቋሚ ኮሚቴ አባላት የባለስልጣን መስሪያቤቱን ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ከየስራ ክፍሉ የተውጣጡ ባለሙያዎችና አገልግሎት ፈልገው ወደ ተቋሙ የመጡ ደንበኞችን አነጋግረዋል፡፡ በምልከታቸውም ባለስልጣን መስሪያቱ አሰራሩን በቴክኖሎጂ ለማስደገፍ የተጀመረው ተግባር አበረታች መሆኑን፣የክትትልና የድጋፍ ስራው ፣መንግስትና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በቅንጅት ተግባራትን በማከናወን የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተከናወነ ያለው ተግባር፣የበጎ ፍቃድና የበጎ አድራጊነት ባህል በማህበረሰቡ ዘንድ እንዲሰርጽ ግንዛቤ መፈጠሩ ፣ ከሚመለከታቸው የክልል፣የፌደራል ባለድርሻ አካላት ጋር የተጀመሩ ቅንጅታዊ የአሰራር ስርዓቶች እና ሌሎች በዘርፉ የተጀመሩ አበረታች ስራዎች ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው ቋሚ ኮሚቴው ገልጿል፡፡
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በእቅዳቸው መሰረት እንዲያከናውኑ እና የላቀ የማህበረሰብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ልዩ ትኩረት በመስጠት ማከናወን እንደሚገባው የተገለጸ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም የእርስ በእርስ ቁጥጥር ስርዓቱ እንዲጠናከር የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤትን ማጠናከር ይጠይቃል ብለዋል፡፡
የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ የህግና ፍትህ ቋሚ ኮሚቴ አባላት ተቋሙን ለመደገፍና በአካል ስለተገኙ ምስጋናቸውን አቅርበው ቋሚ ኮሚቴው የሰጧቸውን አስተያየቶች በማጠናከር ለተሻለ የማህበረሰብ ተጠቃሚነት ተቋማቸው እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡

ባለስልጣን መስሪያቤቱ ከኢትዮጵያ ሴቶች ማህበራት ቅንጅት ጋር በመተባበር ለሠራተኞች ክፍያ የማይጠየቅባቸው የቤት ውስጥ ስራዎች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ፡፡

ባለስልጣን መስሪያቤቱ ከኢትዮጵያ ሴቶች ማህበራት ቅንጅት ጋር በመተባበር ለሠራተኞች ክፍያ የማይጠየቅባቸው የቤት ውስጥ ስራዎች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ፡፡
ማይከፈልባቸው የቤት ውስጥ ስራዎች (Unpaid Domestic Work) ይህ በቤት ውስጥ የሚከናወን ነገር ግን በገንዘብ የማይገለጽ የዕለት ተዕለት ስራዎችን ያጠቃልላል። እነዚህ ስራዎች ለቤተሰብ ደህንነት እና ማህበራዊ ደህንነት የማይቀሩ ቢሆኑም፣ ብዙውን ጊዜ በሴቶች እና በልጃገረዶች ላይ የሚወድቁ ሲሆን፣ ይህም የጾታ እኩልነትን እና ኢኮኖሚያዊ እድሎችን በተመለከተ ችግሮችን ያስከትላል።
በስልጠናው ላይ የተገኙት የባለስልጣን መስሪያቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ እንደተናገሩት የሰራተኞቻችንን አቅም ለመገንባት የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን እየሰጠ እንደሚገኝ በመግለፅ ቀጣይነት እንደሚኖረውም አንስተዋል፡፡
አክለውም የኢትዮጵያ ሴቶች ማህበራት ቅንጅት ለሃያ ዓመታት በሴቶች ላይ እየተሰሩ ያሉት ስራዎች የሚበረታቱ መሆኑን አንስተው የሴቶችን እኩልነት ሴቶችን በማንቃት ሴቶችን በማደራጀት ያላቸውን እምቅ አቅም እንዲጠቀሙ እንዲሁም በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ ውስጥ ያላቸው ተሳትፎ እንዲጎለብት ትልቅ አስተዋጽኦ እያደረጉ በመሆናቸው ዋና ዳይሬክተሩ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
ሌላው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በተለያየ ዘርፍ የተደራጁትን ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የመመዝገብ የመቆጣጠር እና የመደገፍ ስራዎችን እንደሚሰራ በመግለፅ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን አቅም ለማሳደግ የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ እያገዛቸው መሆኑን አንስተዋል፡፡
በተለይ በሴቶች በወጣቶችና በህፃናት ላይ የሚሰሩ ድርጅቶች እያደረጉ ያለው እንቅስቃሴ የሚበረታታ ነው ሲሉ ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡
በመጨረሻም ሴቶች የሚገባቸውን ክብር በመስጠት ማግኘት የሚገባቸውንም እንዲያገኙ በማድረግ የበኩላችንን ሀላፊነት መወጣት አለብን ሲሉ ተናግረወ፡፡
የኢትዮጵያ ሴቶች ማህበራት ቅንጅት ዳይሬክተር ሳባ ገ/መድን እንዳሉት ማህበሩ ትኩረቱን በሴቶች ላይ አድርጎ የሚንቀሳቀስ ሲሆን በዋናነት በሴቶች እኩልነት እንዲሁም ሴቶችን በማህበራዊ፡ በኢኮኖሚያዊ እና በፖለቲካዊ ላይ ያላቸው ተሳትፎ ከማጎልበት አንፃር ማህበራቸው ሴቶችን በስልጠናዎች የማብቃት ስራዎችን እየሰራ እነደሚገኝ ገልፀዋል፡፡
አያይዘውም ማህበራቸው ለሃያ ዓመታት ከአስር በላይ ማህበራትን በማቀፍ ለህብረተሰቡ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ በመግለፅ ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጋርም በመተባበር ለሰራተኞች ስልጠናዎችን እንደሰጠ ተናግረዋል፡፡
ቋሚ የሆነ የትብብርና የቅንጅት አሰራርን መዘርጋት አስፈላጊ መሆኑ ተገለጸ፡፡

ቋሚ የሆነ የትብብርና የቅንጅት አሰራርን መዘርጋት አስፈላጊ መሆኑ ተገለጸ፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አዲስ ከተመረጡ የኢትዮጵያ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ምክርቤት ስራ አስፈጻሚ አባላት ጋር ትውውቅና ውይይት አድርጓል፡፡
በውይይቱ በዘርፉ ስለተከናወኑ ተግባራት፣ ስለ ምክር ቤቱ ሁኔታ፣ በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ እና በምክር ቤቱ መካከል ስለሚኖረው ቅንጅታዊ አሰራር እና በቀጣይ የትኩረት መስኮች፣ በቅርቡ የእግድ እርምጃ በተወሰደባቸው ድርጅቶች ጉዳይ ዙሪያ ሃሳቦች ቀርበው የጋራ መግባባት መፍጠር ተችሏል፡፡
ለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የተመቻቸ ምህዳር የፈጠረ ህግ የማውጣት እንዲሁም ህጉን ተግባራዊ ለማድረግ ላለፉት የለውጥ ዓመታት የተካሄዱ ተቋማዊ ሪፎርሞች በኃላፊነት ስሜት የሚሰራ፣ ገንቢ በሆነ የትብብር ማዕቀፍ የሚሰራ፣ የተቋቋመበትን ዓላማ መሰረት በማድረግ በህግ አግባብ የሚንቀሳቀስ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት ዘርፍ ለመፍጠር መሆኑ በውይይቱ የተነሳ ሲሆን ይህንን በመረዳት የሲቪል ማህበራት የህዝብን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ እንዲሆኑ ማድረግ የሚያስፈልግ መሆኑ በባለስልጣን መ/ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች በኩል በውይይቱ በአፅንኦት ተነስቷል፡፡
የባለስልጣኑ አመራሮች በተቋቋሙበት ዓላማ መሰረት ህግን ተከትለው የሚሰሩ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችን መደገፍ የሚቀጥል መሆኑን በማንሳት በአንፃሩ ደግሞ ከዓላማቸው ውጭ ከፖለቲካ ገለልተኛ ባለመሆን እና ሃላፊነትን በጎደለው ሁኔታ በመንቀሳቀስ የሃገር እና የማኅበረሰብ ደህንነትን አደጋ ላይ የሚጥል ስራ የሚሰሩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ላይ የተጠናከረ የክትትልና ቁጥጥር ስራ በማከናዎን ተገቢውን የእርምት እርምጃ በመውሰድ የህግ የበላይነት የሚረጋገጥ መሆኑን አስታውቋል፡፡
ከዚህ ረገድ አዲስ የተመረጠው የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የምክር ቤቱን ያለፉ አፈፃፀሞችን በመገምገም፣ ዓላማው ላይ ግልፅነት በመፍጠር፣ በተለይም ዋነኛ የተቋቋመበት ዓላማ የሆነውን የራስ አስተዳደርና ቁጥጥርን ተግባራዊ በማድረግ የህግ የበላይነት መከበር ላይ ኃላፊነቱን መወጣት እንደሚገባው ተገልፆል ፡፡
ምክር ቤቱን ለማቋቋም ከምስረታ ጀምሮ ባለስልጣን መ/ቤቱ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደረገ ሲሆን በምክር ቤቱ የተከናወኑ ተግባራት አበረታች መሆናቸውን ጠቁመው የበለጠ እንዲጠናከር የሚያስችሉ ሃሳቦች በውይይቱ ተነስተው የጋራ መግባባት ተፈጥሮባቸዋል፡፡ በውይይቱ የሲቪል ማህበራት ዘርፍ ሃላፊነቱን በመወጣት የተሻለ የማህበረሰብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ባለስልጣኑ እና ምክር ቤቱ በቋሚነት የሚገኛኑበትና የሚመክሩበት የትብብርና የቅንጅት መድረክ እንዲፈጠር ስምምነት የተደረሰበት ሲሆን ይህንኑ ስርዓት ለመዘርጋት የሚያስችል ሰነድ የሚያዘጋጁ የጋራ ኮሚቴ ተቋቁሟል፡፡
ከዚህ ረገድ ባለስልጣን መስሪያቤቱ በህግ የተሰጠውን ሃላፊነት እንዲወጣ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ትብብር ማድረግ የሚገባቸው ሲሆን በተመሳሳይ ምክር ቤቱ እንዲጠናከር ባለስልጣኑ ድጋፉን የሚቀጥል መሆኑ ተገልፆል፡፡
የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት በበኩላቸው ከየትኛውም ጊዜ በላይ ለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምቹ ሁኔታ የተፈጠረበት ወቅት በመሆኑ መንግስትና የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በጋራ የተጀመረውን ሪፎርም የሚያጸና ስራ ላይ ትኩረት አድርገን መስራት አለብን ሲሉ የገለፁ ሲሆን የተነሱ ችግሮችን በመውሰድ ምክር ቤቱ የሚሰራበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በተያያዘም ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ላይ ያለን አካላት የውክልና ብቻ ሳይሆን የወከለንን ሲቪል ማህበረሰብ ሃሳብና አስተያየት መሰረት አድርገን ለውጥ የሚያመጣ ስራ መስራት አለብን ሲሉ ገልጸዋል፡፡
የኢፌዴሪ ፍትህ ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋማት የ2017 የስድስት ወራት እቅድ አፈጻጸማቸው ተገመገመ::
የኢፌዴሪ ፍትህ ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋማት የ2017 የስድስት ወራት እቅድ አፈጻጸማቸው ተገመገመ::
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትህ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሃና አርዓያሥላሴ በተገኙበት የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን፣የኢፌዴሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን፣የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት እና የፌዴራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን የ2017 የስድስት ወራት እቅድ አፋጻጸማቸው ቀርቦ ተገምግሟል፡፡
ክብርት ሚኒስትሯ በማብራሪያቸው አንደገለጹት ሁሉም ተቋማት ከእቅድ አንጻር ያከናወኗቸው ተግባራት አበረታች መሆኑን አንስተው ተቋማት እቅዶቻቸውን ስትራቴጂክ መሆናቸውን ማረጋገጥና በዛ መሰረት መፈጸም ፣ሪፎርሙን የተረዳና የተገነዘበ ሰራተኛን ከመፍጠር አንጻር ትኩረት አድርጎ መስራት እና ዲጂታል ተቋም ከመገንባት አንጻር በተጠሪ ተቋማቱ የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫ ሆኖ እንዲፈጸም አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡
አያይዘውም በፍትህ ሚኒስቴር መታየት የሚገባቸው ጉዳዬች ተለይቶ እንደሚሰራ ተናግረው ተጠሪ ተቋማት እቅድን መሰረት አድርገው ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ሚኒስትር መስሪያቤታቸው ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ባለስልጣን መስሪ ቤቱ ለእንጦጦ ቴክኒክና ሙያ ስልጥና ኮሌጅ በበጎ ፈቃደኝነት ላይ ለግማሽ ቀን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ::
የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የበጎ ፈቃድ ማጎልበትና ትብብር መሪ ስራ አስፈጻሚ የበጎ ፈቃድ እና የበጎ አድራጊነት ባህልን በህብረተሰቡ ውስጥ ለማስረጽ በተለያዩ ዩኒቨርሶቲዎች እና ቴክኒክና ሙያ ተቋማት ለሚገኙ ተማሪዎች የግነዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን እየሰጠ ይገኛል፡፡
የበጎ ፈቃድ ማጎልበትና ትብብር መሪ ስራ አስፈጻሚ በእንጦጦ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ በበጎ ፈቃድ ዙሪያ ለሚሰሩ ተማረሪዎች በበጎ ፈቃደኝነት ምዝገባ ዌብ ሳይት አጠቃቀም (VIMS) እና በበጎ ፈቃደኝነት ዙሪያ ለግማሽ ቀን ስልጠና ሰጥቷል፡፡
ስልጠናውን የሰጡት የበጎ ፈቃድ ማጎልበትና ትብብር መሪ ስራ አስፈጻሚ ቡድን መሪ ወ/ሮ ሽልማት መርሻ ለሰልጣኞች ያስተላለፉት መልዕክት ባለስጣን መስሪያ ቤቱ በአዋጅ 1113/2011 በተሰጠው ስልጣን መስረት የበጎ ፈቃድ እና የበጎ አድራጊነት ባህልን በህብረተሰቡ ውስጥ ለማስረጽ በዩኒቨርሲቲዎች እና በቴክኒክና ሙያ ተቋማት ለሚገኙ በበጎ ፈቃድ ላይ ለተሰማሩ ተማሪዎች ስልጠናዎችን እየሰጠ እንደሚገኝ በመግለጽ ይህንንም አጠናክሮ ለማስቀጠል በቴክኒክና ሙያ ተቋማት ውስጥ የበጎ ፈቃደኝነት ክበብ እንዲቋቋም ለማድረግ ትኩረት አድርጎ የሚሰጥ ስልጠና መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በበጎ ፈቃደኝት ላይ የሚሳተፉ አካላት በፍላጎታቸውና በክህሎታቸው ላይ እንዲሁም በእድሜያቸው ተመርኩዘው የተለያዩ ሚናዎችንና ፕሮጀክቶችን የመሞከር እድል እንዲያገኙ የሚረዳ ሲሆን ዋንኛ ዓላማው በበጎ ፈቃድ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች የማህበረሰብን ስሜት ይረዳሉ፣ ማህበራዊ ክህሎቶችን ያዳብራሉ ጠቃሚ የሆኑ ችሎታዎችን ያገኛሉ የሥራ ዕድሎች ይፈጠራሉ፣ በሕይወታቸው ውስጥ አስደሳች ነገሮች ይፈጠራሉ፣ አዳዲስ ክህሎቶች እና እውቀት እንደሚያገኙ በስልጠናው ላይ ተገልጧል።

የፍትህ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት በጋምቤላ ክልል በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት መርሃ ግብር ከሶስት ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ያስገነቡትን የአቅመ ደካማ መኖሪያ ቤቶችን አስረከቡ::

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትህ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት በጋምቤላ ክልል በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት መርሃ ግብር ከሶስት ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ያስገነቡትን የአቅመ ደካማ መኖሪያ ቤቶች አስረክበዋል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ አለሚቱ ኡሞድ እንዳሉት ከለውጡ በኃላ በክልሉ በርካታ የሪፎርም ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ ገልጸው፣ በተለይም ሰው ተኮር የሆኑ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ስራዎች ማህበረሰቡን ተጠቃሚ እያደረጉ መሆኑን አውስተዋል፡፡
የበጎ ፍቃድ ስራዎች አንድነትን የሚፈጥሩ በመሆኑ ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሯ ፍትህ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት በክልሉ በበጎ ፍቃድ ስራ ላይ ተሰማርተው ግንባታውን አጠናቀው ለአቅመ ደካሞች በማስረከባቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ የተከበሩ አቶ አገኘሁ ተሻገር በበኩላቸው ማህበራዊ ሰው ተኮር ልማቶች በሀገራችን መጎልበት አለባቸው ያሉ ሲሆን፣ በተለይም ወጣቶችን ለበጎ ፍቃድ አገልግሎት በማስተባበር በማህበረሰቡ ውስጥ ለችግር የተጋለጡ ወገኖችን ማገዝ እንደሚገባ በማሳሰብ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት የማህበረሰቡ ባህል መሆን እንደሚገባው አመላክተዋል።
የፍትህ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ኤርምያስ የማነብርሃን (ዶ/ር) በርክክቡ ወቅት እንደገለጹት ከመደበኛ ስራ በተጨማሪ በማህበራዊ ሃላፊነት ዙሪያ ባለፉት ዓመታት የፍትህ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማትን በማስተባበር በተለያዩ ጊዜያት በርካታ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ስራዎችን ማከናወን መቻሉን አስታውሰው፣ በጋምቤላ ክልልም ለአምስት አቅመ ደካሞች የቤት ግንባታ በማከናወን በዛሬው ዕለት ርክክብ ማድረጋቸውን ገልፀዋል፡፡ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በአዋጅ 1113/2011 መሰረት የበጎ ፍቃድ ስራን በማህበረሰቡ ዘንድ ባህል ለማድረግ በተሰጠው ተግባርና ሃላፊነት መሰረት በርካታ ተግባራትን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡

12ኛው የኢፌዲሪ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን እና የክልልና የፌዴራል ባለድርሻ አካላት የጋራ ጉባኤ ተጠናቋል፡፡
12ኛው የኢፌዲሪ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን እና የክልልና የፌዴራል ባለድርሻ አካላት የጋራ ጉባኤ ተጠናቋል፡፡
በመድረኩ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር ጨምሮ በርካታ የመንግስት እና የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
የፌዴሬሽን ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር በመክፍቻ ንግግራቸው እንዳሉት መንግስት በርካታ ፈተናዎችን እያለፈ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል ብለዋል። የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ከለውጡ በኋላ በመንግሥትና በግል ባለሃብቱ የማይሸፈኑ የልማት ሥራዎችን በመተካት ወሳኝ ሚና እየተወጡ እንደሚገኙ አብራርተዋል።
ሲቪል ማኀበረሰብ በሀገሪቱ ላይ የሚከሰቱ ችግሮችን መፍታት እንዲችሉ ህግና ፖሊሲዎችን አዘጋጅቶ በነፃነት እንዲንቀሳቀሱና መብቶቻቸው እንዲከበሩ አድርጓል። ሲቪል ማህበረሰቡ ለኢትዮጵያ ልማት እና ሰላም ግንባታ በሙሉ አቅማቸው እንዲሰሩ መንግስት የሚያደርገውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አፈ-ጉባኤው አስታውቀዋል።

የጋምቤላ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ጋትሉዋክ ሮን በበኩላቸው የሲቪል ማህበረሰብ በሀገራችን ተመዝግበው በልማት፣ በዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ፣ በሰላም ግንባታ፣ በሰብዓዊ ድጋፍ እና በሌሎች ጉዳዮች ላይ በስፋት መንቀሳቀስ የሚችሉበት አውድ መፍጠር ተችሏል ብለዋል። በቀጣይም በኢኮኖሚ ዕድገት ተጨማሪ አቅም በመሆን በማህበራዊ ልማት የነቃ ተሳትፏቸው እንዲጎለብት፤ አርዓያነት ያለዉን ተግባር በማሳየት አወንታዊ ሚናቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።
የባለስልጣን መስሪቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ እንደገለፁት ባለፉት የለውጥ ዓመታት በሪፎርም ሂደት ውስጥ በማለፍ ላይ ያለው የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብን ኑሮ ለማሻሽል የሚየስችሉ ዘርፈ በዙ ተግባራትን ማከናወኑን ተናግረዋል። ሲቪል ማህበረሰብ ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆኑ እና በዘርፉ የተጀመሩ ሪፎርሞች መሰረት እንዲይዙ ጥረት እየተደረገ መሆኑንም አስረድተዋል።

በቀጣይም የሲቪል ማህበረሰብ ምክር ቤትን ጨምሮ ህግን አክብረው የሚሰሩ ሲቪል ማህበረሰብ ሁሉ ድጋፍ ሊያደርጉ እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል። በሁለት ቀናት ቆይታ በርካታ ርዕሰ ጉዳዬች የተነሱ ሲሆን በተለይም የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ክትትል እና ቁጥጥር ለማህበረሰብ እና ለሃገር ተጠቃሚነት በሚል ርዕስ በአቶ ፋሲካው ሞላ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የክልል የሲቪል ማህረሰብ ድርጅቶች NGO desk ላይ የሚሰሩ ሃላፊዎች የተወያዩበትን ተሞክሮ እና በቀጣይ ቢከናወኑ ብለው ያነሷቸውን ጉዳዬች ለጉባኤው አቅርበዋል፡፡

በሀላባ ዞን በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስትያን መካነ ኢየሱስ የተገነባ የውሃ ፕሮጀክቶች ተመረቀ፡፡

በሀላባ ዞን በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስትያን መካነ ኢየሱስ የተገነባ የውሃ ፕሮጀክቶች ተመረቀ፡፡
በሀላባ ዞን በ2ኛ መቃላ ሀ እና የሸቃጤ ወልድያ ቀበሌዎች ለማህበረሰቡ የሚያገለግል የንጽህ መጠጥ ውሃ በዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ ተመርቋል፡፡ የዞኑ ም/ዋና አስተዳዳሪ ሀጂ ኑሪዬ እንደገለጹት በሀላባ አብዛኛው አከባቢዎች የንጽህ መጠጥ ውሃ ችግር መኖሩን ገልጸው ከዚህ አልፎ እናቶች ከሃያ ኪሎ ሜትር በላይ ተጉዘው እንደሚቀዱ ካልሆነም ከኩሬ ቀድተው ይጠቀሙ እደነበር አንስተዋል፡፡አሁን ላይ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስትያን መካነ ኢየሱስ በሁለቱ ቀበሌዎች ከሃያ ሺህ በላይ ማህበረሰባችንን ተጠቃሚ ያደረገ የውሃ ፕሮጀክት በመገንባቱ የዞኑ አስተዳደርና ማህበረሰቡ ምስጋና ያቀርባል ሲሉ ገልጸዋ፡፡ይህ የውሃ ፕሮጀክት ከማህበረሰቡ አልፎ ለትምህርት ቤቶችና ጤና ተቋማት አገልግሎት እንደሚሰጥ ተጠቅሷል፡፡ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስትያን መካነ ኢየሱስ ፕሮግራም ዳይሬክተር አቶ ቢቂላ አብያ በፕሮጀክት መጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላደረጉ ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበው የተገነቡ የውሃ ፕሮጀክቶችን ማህበረሰቡ በጥንቃቄ መያዝና ቀጣይነቱን ማረጋገጥ ይገባቸዋል ብለዋል፡፡ አክለውም የአላባን የውሃ ችግር ለመቅረፍ በቀጣይ የፕሮጀክት እቅዶች ላይ በማካተት እንደሚሰሩ ለማህበረሰቡ ቃል ገብተዋል፡፡
በሀላባ ዞን በ2ኛ መቃላ ሀ እና የሸቃጤ ወልድያ ቀበሌዎች ለማህበረሰቡ የሚያገለግል የንጽህ መጠጥ ውሃ በዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ ተመርቋል፡፡ የዞኑ ም/ዋና አስተዳዳሪ ሀጂ ኑሪዬ እንደገለጹት በሀላባ አብዛኛው አከባቢዎች የንጽህ መጠጥ ውሃ ችግር መኖሩን ገልጸው ከዚህ አልፎ እናቶች ከሃያ ኪሎ ሜትር በላይ ተጉዘው እንደሚቀዱ ካልሆነም ከኩሬ ቀድተው ይጠቀሙ እደነበር አንስተዋል፡፡
አሁን ላይ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስትያን መካነ ኢየሱስ በሁለቱ ቀበሌዎች ከሃያ ሺህ በላይ ማህበረሰባችንን ተጠቃሚ ያደረገ የውሃ ፕሮጀክት በመገንባቱ የዞኑ አስተዳደርና ማህበረሰቡ ምስጋና ያቀርባል ሲሉ ገልጸዋ፡፡
ይህ የውሃ ፕሮጀክት ከማህበረሰቡ አልፎ ለትምህርት ቤቶችና ጤና ተቋማት አገልግሎት እንደሚሰጥ ተጠቅሷል፡፡ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስትያን መካነ ኢየሱስ ፕሮግራም ዳይሬክተር አቶ ቢቂላ አብያ በፕሮጀክት መጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላደረጉ ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበው የተገነቡ የውሃ ፕሮጀክቶችን ማህበረሰቡ በጥንቃቄ መያዝና ቀጣይነቱን ማረጋገጥ ይገባቸዋል ብለዋል፡፡ አክለውም የአላባን የውሃ ችግር ለመቅረፍ በቀጣይ የፕሮጀክት እቅዶች ላይ በማካተት እንደሚሰሩ ለማህበረሰቡ ቃል ገብተዋል፡፡
Change the color to match your brand or vision, add your logo, choose the perfect layout, modify menu settings, add animations, add shape dividers, increase engagement with call to action and more.













