
Strategic leadership ዙሪያ ለተቋሙ አመራርና ሰራተኞች ስልጠና ተሰጠ ፡፡ስልጠናውን የሰጡት የተከበሩ ፕሮፌሰር ምህረቱ ሻንቆ የህዝብ ተወካዬች ምክር ቤት አባል እና የኢፌደሪ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የቦርድ አባል ናቸው፡፡
ከስልጠናው በተጨማሪ የሰዎች ለሰዎች የስራ እንቅስቃሴ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
በስልጠናው ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢፌደሪ ፍትህ ሚኒስቴር አማካሪ ሚኒስት ዴኤታ አቶ ዑሙድ ኡጁሉ ባለስልጣን መስሪያቤቱ የጀመራቸው የሪፎርም ስራዎች አበረታች መሆናቸውን በመግለጽ ለለውጡ ቀጣይነት እንደዚህ አይነት ስልጠናዎች አስፈላጊ ናቸው ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የባለስልጣን መስሪያቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ በበኩላቸው ተቋሙ የሰራተኞችን የመፈጸምና የማስፈጸም አቅም ለማጎልበት በርካታ ተግባራት እያከናወነ መሆኑን ገልጸው ሰዎች ለሰዎች ድርጅትም ለትውልድ ተሻጋሪ የሆኑ እና ከመንግስት የልማት እቅዶች ጋር የተቀናጁ ስራዎች መስራታቸው ምሳሌ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡
አያይዘውም ሰዎች ለሰዎች ድርጅት ይህ ስልጠና እንዲሳካ ላደረጉት ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋለ፡፡
በስልጠናው ማጠቃለያ በዲሞክራሲ ማስተባበሪያ ማዕከል የሲቪል ባህል ግንባታ ዳይሬክተር አቶ ደስታ ብዙአየሁ በሰጡት አስተያየት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ዘርፍ ሁለት መሰረታዊ ጉዳዬችን እንዲያሟሉ ይጠበቃል በዓላማቸው መሰረት ተግባራቸውን ማከናወን እና ከፖለቲካ ነጻና ገለልተኛ ሆነው መስራት ይንን ባህሪ ከሰዎች ለሰዎች ድርጅት በመመልከቴ ደስታ ተሰምቶኛል በሌሎች የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችም ይሄ ይጠበቃል ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
የሰዎች ለሰዎች ድርጅት የዛሬ 44 ዓመት በዶ/ር ካርል መመስረቱን የገለጹት የድርጅቱ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ሙሉነህ ቶለሳ ድርጅቱ በገጠር የተቀናጀ ልማት ላይ ማለትም በውሃ፣በትምህርት፣በሰብዓዊ ድጋፍ፣የአከባቢ ጥበቃ እና የሰውሃብት ልማት ላይ ትኩረት አድርጎ በመስራት ከስድስት ሚሊየን ህዝብ በላይ ተደራሽ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
ስልጠናው እራሳችንን እንድንመለከትና በቀጣይ ተቋሙ ባስቀመጠው ራዕይ እና በተሰጠን የስራ ሃላፊነት የድርሻችንን እንድንወጣ የሚያግዝ ነው ሲሉ ሰልጣኞች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡


