የባለስልጣኑ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ፎረም ፎር ሶሻል ስተዲስ (FSS) የተባለ አገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት የስራ እንቅስቃሴ ተመልክተዋል፡፡

የባለስልጣኑ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ፎረም ፎር ሶሻል ስተዲስ (FSS) የተባለ አገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት የስራ እንቅስቃሴ ተመልክተዋል፡፡

የሲሺል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከፍተኛ አመራሮች ፎረም ፎር ሶሻል ስተዲስ (FSS) የተባለ አገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት ጉብኝት ያካሄዱ ሲሆን የድርጅቱን የስራ እንቅስቃሴ በተመለከተ ከድርጅቱ የስራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አድርገዋል።
በጉብኝቱ ወቅት ገለጻ ያደረጉት የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ ዶ/ር የራስወርቅ አድማሴ እንደገለጹት FSS ከ25 አመታት በፊት በአንጋፋ ምሁራን የተመሰረተና በማህበራዊና ልማታዊ የፖሊሲ ጉዳዮች ላይ ጠለቅ ያለ ጥናትና ምርምር የሚያካሂድ እንዲሁም ባለድርሻ አካላት በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውይይት እንዲያደርጉ መድረኮችን የሚያዘጋጅና በመንግሥት የፖሊሲ አወጣጥና ትግበራ ሂደት የበኩሉን ድርሻ የማበርከት ዓላማ አንግቦ የተመ

ሰረተ አገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት መሆኑን ገልጸዋል።

ባለስልጣን መ/ቤቱ ለሙያ ማህበራት በተለይም ጥናትና ምርምር ላይ ትኩረት አድርገው ለሚሰሩ ድርጅቶች (Think thanks) ድጋፍና አገልግሎት የሚሰጥ የተለየ የስራ ክፍል ያቋቋመ መሆኑን ገልጸው የተጀመረውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ ጠቁመዋል።


የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በወጣቶች ሰላም ግንባታ እና በስሜታዊ ብልህነት (Emotional Intelligence) ላይ ያተኮረ ስለጠና ሰጠ።

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በወጣቶች ሰላም ግንባታ እና በስሜታዊ ብልህነት (Emotional Intelligence) ላይ ያተኮረ ስለጠና ሰጠ።የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከSOS Children's village ጋር በመተባበር በወጣቶች ሰላም ግንባታ እና በስሜታዊ ብልህነት (Imotional Intelligence) ላይ ትኩረት ያደረገ የሁለት ዙር ስልጠና ለተቋሙ ወጣት ሰራተኞች ሰጥቷል።

ስልጠናው ወጣቶች በሰላም ግንባታ ላይ ያላቸውን ግንዛቤ እንዲያሳድጉና ከሰላም ግንባታ ጋር በተያያዘ እንደወጣት የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት መወጣት እንዲችሉ በማለም የተዘጋጀ ስልጠና ነው፡፡በተጨማሪም ከስሜታዊ ብልህነት (Emotional Intelligence) ጋር በተያያዘ ወጣቶች በምን መልኩ ማዳበር እንዳለባቸውና ለሰላም ግንባታ ያለውን ሚና በሚመለከት ገለጻ ተደርጓል፡፡
ስልጠናው በሁለት ዙር ለተከታታይ አራት ቀናት የተሰጠ ሲሆን በስልጠናው ላይ የSOS childrens village Location program manager በረከት ማቴዎስ ድርጅቱን በሚመለከት ገለጻ አድርገዋል፡፡ ወ/ሮ ትዕግስት አቡዬ በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ስራ አስፈፃሚ እንዲሁም ወ/ሮ ቤተልሄም ጌታቸው የLeave No Youth Behind Project አስተባባሪ የስልጠናውን ዓላማ በተመለከተ ገለፃና ማብራሪያ አድርገዋል፡፡።


በሲቪል ማህበራት ዘርፍ በተከናወኑ የሪፎርም ተግባራት ሲቪክ ምህዳሩ ከመቼውም ጊዜ በላይ ሰፍቷል፡፡

 

በሲቪል ማህበራት ዘርፍ በተከናወኑ የሪፎርም ተግባራት ሲቪክ ምህዳሩ ከመቼውም ጊዜ በላይ ሰፍቷል፡፡

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በኢትዮጵያ ሀገረ መንግስት ግንባታ፣ በልማት፣ በዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ እና በዘላቂ ሰላም ማረጋገጥ ረገድ የማይተካ ሚና የሚጫወቱ ዋነኛ ተዋናዮች ናቸው። በተለይም የሕግ ማዕቀፍ ሪፎርሙን ተከትሎ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ተሳትፏቸው እየጎላ የመጣ ሲሆን፣ ከመንግስትና ልማት አጋሮች ጋር በመተባበር ለሀገር ሁለንተናዊ እድገትና ለፖሊሲ ግብዓት በማመንጨት ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክታሉ።
ይህንን ሚና በመገንዘብም ከለውጡ በፊት አሳሪ የነበሩ ህጎችና ተቋማዊ አሰራሮች ላይ የሪፎርም እርምጃዎችን በመዉሰድ የሚጨበጥ ለዉጥ ከተመዘገበባቸዉ ዘርፎች መካከል አንዱ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች(ሲማድ) ነዉ፡፡
መንግሥት የኢትዮጵያን ዘላቂ ሰላምና ብልጽግና ለማሳካት የሁሉም ዜጎች አስተዋጽዖ አስፈላጊ መሆኑን በጽኑ በማመን ሰዎች በተለያዩ ፍላጎቶቻቸውና ዝንባሌያቸው ተደራጅተው ለመሥራት ሳንካ የሆኑባቸውን እንቅፋቶች ለማስወገድ ከወሰዳቸው ጉልህ የሪፎርም እርምጃዎች አንዱ አዲሱ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ 1113/2011 መውጣቱ ነው። አዋጁ ቀደም ብሎ የሲቪክ ምኅዳሩን ያላግባብ ያጣበቡ ድንጋጌዎችና አሠራሮችን በማረም ሀሳብን በነጻነት የመግለጽና የመደራጀት ሕገ መንግሥታዊ መብቶች እንዲጠበቁ ጉልህ ሚና ተጫውቷል።

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች አስተዳደር ማሻሻያ በክልሎችም እንዲተገበር ባለፉት ዓመታት በተደረገው ክትትል 11 ክልሎች ተመሳሳይ የሪፎርም ሕጎች አውጥተው በትግበራ ላይ ይገኛሉ።


ሲቪክ ማህበራት በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚኖራቸውን የክትትልና ድጋፍ ሚና አጠናክረው መቀጠል አለባቸው::

ሲቪክ ማህበራት በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚኖራቸውን የክትትልና ድጋፍ ሚና አጠናክረው መቀጠል እንደሚገባቸው የኢትዮጵያ ሲቪክ ማህበራት ድርጅቶች ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ፋሲካው ሞላ አስገነዘቡ።
ምናልባት የአንድ ወይም ከዚያ በላይ ሰዎች፤ የዜና ክፍል፤ ከፍ ያለ መድረክ እና ጽሑፍ ምስል
 የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን እና የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት  “ለዲሞክራሲያዊ ምርጫ ስኬት የመገናኛ ብዙሃን ሚና” በሚል ርዕስ በጋራ ያዘጋጁት መድረክ በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል። መድረኩ ዴሞክራሲያዊ እና ፍትሃዊ ምርጫ ማካሄድ የሁሉም ባለድርሻ አካላት የጋራ ኃላፊነት መሆኑን ለማስገንዘብ ታስቦ የተዘጋጀ ነው። በመድረኩ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናትዓለም መለሰ፣ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ፣ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ ሰይፈ ደርቤ፣ የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ፋሲካው ሞላ፣ የመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን የስራ ሃላፊዎች፣ የመገናኛ ብዙሃን የስራ ሀላፊዎች እና ጋዜጠኞች ታድመዋል። በመድረኩ የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክትል ዋና ዳይሬክተር ፋሲካው ሞላ የሲቪክ ማህበራት በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚኖራቸውን የክትትልና ድጋፍ ሚና አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። ዴሞክራሲያዊ እና ፍትሃዊ ምርጫን ማካሄድ የሁሉም ባለድርሻ አካላት የጋራ ኃላፊነት መሆኑን ጠቁመው የሲቪክ ማኅበራት ሚና እጅግ ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል። ሲቪል ማህበራት በምርጫ ወቅት ያላቸው ሚና ታዛቢነት ብቻ ሳይሆን፣ ዜጎች ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ በኃላፊነትና በባለቤትነት እንዲቆሙ የማድረግ ትልቅ ኃላፊነት አለባቸውም ነው ያሉት። በዚህም ማህበራቱ ዜጎች ስለ ምርጫ አስፈላጊነት በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው በማድረግ በኩል ኃላፊነታቸው ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል። ህብረተሰቡ በምርጫው ሂደት ንቁ ተሳታፊ እንዲሆን ማብቃት ላይ በትኩረት ሲሰሩ መቆየታቸውን ጠቁመው ይህንኑ ጥረታቸውን አጠናክረው መቀጠል ይገባቸዋል ብለዋል።
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ግዛው ተስፋዬ በበኩላቸው መገናኛ ብዙሃን ምርጫውን በተመለከተ በሚሰሯቸው ዘገባዎች ህግጋትን ተከትለው መስራታቸውን ክትትል እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል። መገናኛ ብዙሃን ለፖለቲካ ፓርቲዎች የተመደቡትን ነጻ የቅስቀሳ እና የማስተዋወቂያ ሰዓት አጠቃቀም ላይ ችግር እንዳልተከሰተ ተናግረዋል። መገናኛ ብዙሃን በምርጫ ወቅት በሰላም ግንባታ ላይ በትኩረት እንዲሰሩ ባለስልጣኑ ሲሰራ መቆየቱንና ይህንኑ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
በምርጫ ወቅት የሚጠበቁ የስነምግባር መርሆዎች እንዲጠበቁ ስራዎችን እየሰራ መሆኑንና ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የአቅም ግንባታ ስራ መሰራቱን ገልጸዋል። መገናኛ ብዙሃን ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣው ፕሮግራም መሰረት ምርጫውን በተመለከተ የተለያዩ የዘገባ ስራዎችን ለህዝብ ተደራሽ ሲያደርጉ ቆይተዋል ብለዋል። በዚህም ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ሚናቸውን እየተወጡ ይገኛሉ ነው ያሉት። ከፓናሉ ተሳታፊዎች በምርጫው ወቅት የመገናኛ ብዙሃንና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሚናን የተመለከቱ አስተያየቶች እና ጥያቄዎች የተሰነዘሩ ሲሆን በፓናሊስቶቹ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በስራዎቻቸው ሁሉ ለሰላም አስተዋጽኦ የሚያደርግ እና ግጭት አባባሽ የሆኑ ጉዳዬችን የሚቀርፍ መሆን እንደሚገባው ተገለጸ፡፡

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በስራዎቻቸው ሁሉ ለሰላም አስተዋጽኦ የሚያደርግ እና ግጭት አባባሽ የሆኑ ጉዳዬችን የሚቀርፍ መሆን እንደሚገባው ተገለጸ፡፡
ይህ የተባለው “የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ለሰላም እና ለሀገር ግንባታ” በሚል መሪ ሐሳብ ከሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ጋር በሐዋሳ ከተማ በተደረገ የአንድ ቀን የውይይት መድረክ ላይ ነው፡፡ በመድረኩ የኢፌዲሪ የሰላም ሚኒስቴር የፌዴራሊዝም እና ግጭት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ቸሩጌታ ገነነ ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት መንግስት በሀገር ግንባታ ተዋንያን መካከል የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች መሆናቸውን በመረዳት በርካታ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ገልጸው ይህ

ምናልባት የአንድ ወይም ከዚያ በላይ ሰዎች ምስል የውይይት መድረክም የዚሁ አካል ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በዲሞክራሲ፣በሰላም ግንባታ፣በህዝብና በመንግስት መካከል መተማመን እንዲፈጠር መስራት ይጠበቅባቸዋል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው ድርጅቶች በስራዎቻቸው ሁሉ ለሰላም አስተዋጽኦ የሚያደርግ እና ግጭት አባባሽ የሆኑ ጉዳዬችን የሚቀርፍ መሆን ይገባዋል ብለዋል፡፡ በመጨረሻም የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ውክልናቸው የህዝብ በመሆኑ ማኅበረሰብን የሚጠቅም ተግባር እንጂ ፈንድ የሚሰጥን አካል ዓላማ ለማስፈጸም መሆን አይገባውም ሲሉም አሳስበዋል፡፡
የአፌዲሪ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ በበኩላቸው እንደ ሀገር ያለምነውን ብልጽግና ለማምጣት ሰላምን ማጽናት አስፈላጊ መሆኑን አንስተው ከዚህ ረገድ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ሚና ከፍተኛ ሊሆን ይገባዋል ብለዋል፡፡ ይህንኑ ተፈጻሚ ለማድረግ ባለስልጣን መስሪያቤቱ ከኢፌዲሪ የሰላም ሚኒስቴር ጋር የመግባቢያ የስምምነት ሰነድ (MOU) ተፈራርሞ ወደ ስራ መገባቱን ገልጸዋል፡፡ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሰላምን ለማስጠበቅ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን እና የንቅናቄ መድረኮችን መፍጠር፣ ለሠላም ግንባታ አጋዥ የሆኑ እስትራቴጂያዊ ጉዳዮችን መለየትና ለመንግስት የፖሊሲ ግብዓት እንዲሆን ማቅረብ፤ከሚመለከታቸው የክልል ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መስራት ይጠበቅባቸዋ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ በመድረኩ ዶ/ር አወቀ አጥናፉ የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ መሪ ስራ አስፈጻሚ እና አቶ ገመቺስ ኢቲቻ የሰላም ሚኒስቴር የሀገር ግንባታ መሪ ስራ አስፈጻሚ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን የኢፌዲሪ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ ውይይቱን መርተዋል፡፡

በም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ የተመራ ልዑካን ቡድን WELT HUNGER HILFE (WHH) ከሌሎች ሃገር በቀል ድርጅቶች ጋር በመሆን በአፋር ክልል ያከናወናቸውን የልማት ስራዎች ተመልክቷል፡፡

በም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ የተመራ ልዑካን ቡድን WELT HUNGER HILFE (WHH) ከሌሎች ሃገር በቀል ድርጅቶች ጋር በመሆን በአፋር ክልል ያከናወናቸውን የልማት ስራዎች ተመልክቷል፡፡

WHH ከሌሎች ሃገር በቀል ድርጅቶች ጋር ማለትም APDA,AISDA,ORDA Ethiopia ፣Empowerment for Development ፣ DAGU እና DEC በአፋር ክልል በዞን አራት ጉሊና ወረዳ እና በዞን አንድ አፋንቦ ወረዳ ላይ ያከናወናቸውን የልማት ስራዎች በም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ የተመራ ልዑካን ቡድን ተመልክቷል፡፡
WHH በ37 የተለያዩ ሃገራት ላይ የሚሰራ እና በኢትዮጵያ ስራ ከጀመረ 62 ዓመታትን ያስቆጠረ የውጭ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ነው፡፡
ድርጅቱ ከዚህ ቀደም ጀርመን አግሮ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን አሁን ላይ WHH በሚል መቀየሩን የድርጅቱ ካንትሪ ዳይሬክተር ወ/ሮ ሳራ ወርቁ ገልጸዋል፡፡
የተቀናጀ ፕሮጀክት ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራ የገለጹት ካንትሪ ዳይሬክተሯ በግብርና፣ኒውትሪሽን፣ውሃ፣ለሃገር በቀል ድርጅቶች የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በመስጠት እና ሌሎች ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራትን በአጋሮቻቸው በኩል እንደሚያከናውኑም አብራርተዋል፡፡
ድርጅቱ ከአስራ አምስት የሃገር በቀል ድርጅቶች እና ከ58 ሰብ ግራንት ጋር እንደሚሰራ የገለጹት ሃላፊዋ አሁን ላይ በሃገሪቱ 270 በላይ የውሃ ጉርጓዶችን የማስቆፈር፣በርካታ ሶላሮችን የማስገጠም እና ለህብረት ስራ ማህበራት የቡና ማጠቢያና መፈልፈያ ማሽን አቅርቦት ስራ ከተከናወኑ ተግባራት መካከል ተጠቃሽ መሆኑን አንስተዋል፡፡

WHH ከሃገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር በመሆን በአፋር በሁለት ዞኖች ላይ የተከናወኑ ተግባራትን ለሃላፊዎቹ ያስጎበኘ ሲሆን በምልከታውም በዞን አራት ጉሊና ወረዳ ነዋሪ ለሆኑ 500 ለሚሆኑ አባወራዎች ስልጠና በመስጠት እና የግብዓት ድጋፍ በማድረግ በጓሯቸው ለምግብነት የሚውሉ አትክልትና ፍራፍሬን በማምረት ተጠቃሚ እንዲሆን አስችሏል፡፡ በተያያዘም በበሃላዊ መንገድ አሳን የሚያጠምድ ወጣቶችን በማደራጀት በዘመናዊ መልኩ ማምረት የሚያስችል ቦታ ደረጃውን ከጠበቀ ፍሪጅ ጋር ለማስረከብ እየሰሩ መሆኑን ለመመልከት ተችሏል፡፡ ድርጅቱ ከዚህ በተጨማሪ የዳቦ ማምረቻ ማሽን ገዝቶ በማቅረብ እና ስልጠና በመስጠት በአፋር የመጠለያ ካንፕ ለሚገኙ ወጣቶች የስራ እድል መፍጠር ችሏል፡፡ በዞን አንድ አፋንቦ ወረዳ እና ሌሎች አከባቢዎች ላይ አርባ የሚሆን ሶላር ፓኔል ያስገነባ ሲሆን በዚህም ከዞኑ አስተዳዳሪ ጀምሮ በሶላሩ ተጠቃሚ የሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎች ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
የባለስልጣን መስሪያቤቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ በማጠቃለያ ንግግራቸው እንደገለጹት ተቋሙ ጥቂት አብሮ ለመስራት የስምምነት ሰነድ ከተፈራረማቸው ድርጅቶች መካከል WHH አንዱ መሆኑን ገልጸው ለሃገር በቀል ድርጅቶች የፋይናንስ ድጋፍ በማድረግ፣ስልጠና በመስጠት እና ክትትልና ድጋፍ በማድረግ የሰራው ስራ አስተማሪ ነው ብለዋል፡፡
አያይዘውም የተከናወኑ ተግባራት ዘላቂነት እንዲኖራቸው ከማህበረሰቡ እና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ የመንግስት አካላት ጋር በቅንጅት መሰራቱን አድንቀው ከሎካላይዜሽን አንጻር በተግባር መሬት ላይ የታየ እና ለሌሎች ድርጅቶች ምሳሌ የሚሆን ተግባር መፈጸሙን አክለው ገልጸዋል፡፡

Click the button

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የግማሽ ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ከተቋሙ የማኔጅመንት አባላት እና ከአጠቃላይ ሰራተኞች ጋር ውይይት አድርጓል።

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ባለፉት ስድስት ወራት ያከናወናቸውን ተግባራት በሚመለከትና የቀጣዩን አምስት አመታት ስትራቴጂክ እቅድ ላይ ከአጠቃላይ ሰራተኛው ጋር ውይይት አድርጓል፡፡ በውይይቱ ላይ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች አቶ ፋሲካው ሞላ እና አቶ መስፍን ሙሉነህ፣ የተቋሙ የስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል። የውይይቱን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት አቶ ፋሲካው ሞላ እንደጠቆሙት ባለፉት ስድስት ወራት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ህግንና ስርዓትን ተከትለው መስራት እንዲችሉ የሚያስችል የክትትልና ቁጥጥር ስራዎች የተጠናከሩበት እና ከፍተኛ አፈጻጸም የታየባቸው ነበሩ።

ከትብብርና ቅንጅት ጋር በተያያዘም ከፌደራልና ከክልል ባለድርሻ አካላት እንዲሁም በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች መካከል ጠንካራ የትብብርና የቅንጅት መድረኮች እንዲፈጥሩና እንዲደራጁ የተደረገበት ግማሽ ዓመት ነበር። ከበጎ ፈቃደኝነትና ትብብር ስራዎች ጋር በተያያዘም አዳዲስ እና ውጤታማ ተግባራት የተከናወኑበት ወቅት መሆኑ የተጠቆመ ሲሆን ለዚህም እንደማሳያ የዩኒቨርሲቲ ክበባትን ማጠናከርና ቅን ልብ የተሰኘ የሞባይል መተግበሪያ በማስተዋወቅ ወደስራ በማስገባት ረገድ ከፍተኛ ስራ ተከናውኗል። ዲጂታል ተቋምን ለመገንባት የምናደርገው ጥረት ወደተግባር የተቀየረበት እንደሆነ የጠቆሙት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ በቀጣይም የወረቀት ስራዎችን ሙሉ በሙሉ ወደዲጂታል አገልግሎት ለመቀየር የሚያስችሉ ስራዎች በጥሩ ሂደት ላይ እንደሚገኙም ተጠቁመዋል።

በቀጣይም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አዳዲስ የክትትልና የቁጥጥር ስልቶችን ተግባራዊ በማድረግ የክትትልና የቁጥጥር ስራዎችን ማጠናከር ላይ እንደሚሰራ ጠቁመው ተቋሙ የጀመረው አገልግሎትን ወደዲጂታል ስርዓት የመቀየር ስራ ከዳር እንዲደርስና ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንዲሆን በማድረግ አገልግሎቱ ስኬታማ እንዲሆን ሁሉም ሰራተኛ የበኩሉን እንዲወጣ አሳስበዋል። ከውስጥ አሰራር ጋር በተያያዘ አሰራሮቻችንን ማጠናከር እና ዘመኑን እያየን መሻሻል ያሉባቸውን እያሻሻልን መቀጠል ይኖርብናል ብለዋል። በዕለቱ ተቋሙ ባለፉት ስድስት ወራት የተከናወኑ ተግባራትን ከመገምገም ባለፈ የተቋሙን የቀጣይ አምስት አመታት ስትራቴጂክ እቅድ በሚመለከት ውይይት ተደርጓል።


የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ Safe light initiatives በመባል የሚታወቀውን በወጣቶች ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራ ድርጅትን ጎበኙ፡፡

የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ Safe light initiatives በመባል የሚታወቀውን በወጣቶች ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራ ድርጅትን ጎበኙ፡፡

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ከባለስልጣኑ ከተለያየ የስራ ክፍሎች ከተውጣጡ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ጋር በመሆን በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የመዝገብ ቁጥር 4906 ተመዝግቦ በወጣቶች ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራውን Safe light initiatives የተባለውን ሀገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት የስራ እንቅስቃሴ በአዲስ አበባ የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት ጉብኝት አድርገዋል፡፡ SAFE LIGHT በወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ፣ በአመራርና የሙያ ድጋፍ፣ በዲጂታል ስርዓት ተሳትፎ እና ወጣቶችን ማብቃት ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራ ሀገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ሲሆን የተቋቋመውም በፈረንጆቹ አቆጣጠር 2018 በአምባሳደር ስለሺ ሳልስ ኡመር አማካኝነት ነው፡፡

ድርጅቱ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ በርካታ ወጣቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑና ዓለምአቀፍ ልምድና ተሞክሮ እንዲያገኙ እንዲሁም የአመራርና የስራ ፈጠራ አቅማቸው እንዲዳብር የሚያደርጉ ስራዎችን ሲያከናውን መቆየቱን የድርጅቱ መስራችና ዳይሬክተር አምባሳደር ስለሺ ገለጻ አድርገዋል፡፡
ድርጅቱ ወጣቶችን መሰረት አድርጎ የሚሰራ በመሆኑ ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱና ከሌሎች የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ የድርጅቱ የስራ እንቅስቃሴ እጅግ የሚበረታታና የሚደገፍ መሆኑን ጠቁመው ከሀገር አልፈው በዓለም አቀፍ ደረጃ ተጽዕኖ መፍጠር የሚችሉ ወጣቶችን እየተመለከትን ስለሆነ መደገፍና ማበረታታት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ መሰል ድርጅቶችን ለመደገፍ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን የጠቆሙት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ለድርጅቱ ስኬት ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የሚያደርገውን ድጋፍ የሚቀጥል መሆኑን ጠቁመዋል፡፡


በወላይታ የሚገኙ ጠረጤዛ ልማት ማህበር እና ቼንትሮ የተባሉ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በባለስልጣኑ ም/ዋና ዳይሬክተሮች አቶ ፋሲካው ሞላ እና አቶ መስፍን ሙሉነህ ከሌሎች የስራ ሃላፊዎች ጋር በመሆን ጎብኝተዋል፡፡

በወላይታ የሚገኙ ጠረጤዛ ልማት ማህበር እና ቼንትሮ የተባሉ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በባለስልጣኑ ም/ዋና ዳይሬክተሮች አቶ ፋሲካው ሞላ እና አቶ መስፍን ሙሉነህ ከሌሎች የስራ ሃላፊዎች ጋር በመሆን ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝቱ የኢፌዲሪ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ም/ዋና ዳይሬክተሮች፣የክልሉ የሲማድ ዴስክ ዳይሬክተር እና ሌሎች የተቋሙ የስራ ክፍል ሃላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ ጠረጤዛ ልማት ማህበር ሃገር በቀል የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት ሲሆን በሃገራችን በተለያዩ አከባቢዎች በአከባቢ ጥበቃ ላይ ትኩረት በማድረግ ይሰራል፡፡
ድርጅቱ 16 ፕሮጀክቶች ስራ ላይ ያሉት ሲሆን ከአከባቢ ጥበቃ ስራ በተጨማሪ የምርጥ ዘር አቅርቦት፣ስልጠና፣የህጻናት ጥበቃ ፣ጤና እና ሌሎች ዘርፎች ላይ ይሰራል፡፡ የተቋሙ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ በሰጡት አስተያየት ባለስልጣን መስሪያቤቱ ጠንካራ ሃገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እንዲፈጠሩ ይሰራል ለዚህ ማሳያ ስለሆናችሁ ምስጋና ይገባችኋል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

አያይዘውም በባለስልጣን መስሪያቤቱም ሆነ በክልሉም ጥሩ አፈጻጸም ካላቸው ድርጅቶች መካከል በመሆናችሁ ይህንን ስራችሁን አጠናክራችሁ መቀጠል ይኖርባችኋል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ቼንትሮ በኢትዮጵያ ከ43 ዓመት በፊት በጣሊያን ተወላጅ በሆኑት አቶ ሮቤርቶ የተመሰረተ ሲሆን ወላጅ አልባ እና የአካል ጉዳት ያለባቸውን ህጻናት በማዕከል የማሳደግ እና መሰረታዊ ግብዓት የሟሟላት ስራ ይሰራል፡፡ አሁን ላይ 130 በላይ ህጻናትን በማዕከል እንዲሁም ከ 3000 በላይ ህጻናትን በያሉበት እርዳታ እያደረገ የሚገኝ የሲቪለe ማህበረሰብ ድርጅት መሆኑ በጉብኝቱ ወቅት ተገልጿል፡፡


14ኛው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣንና የክልልና የፌደራል ባለድርሻ አካላት መድረክ የግልገል ጊቤ 3 የኃይል ማመንጫን በመጎብኘት ተጠናቀቀ።

14ኛው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣንና የክልልና የፌደራል ባለድርሻ አካላት መድረክ የግልገል ጊቤ 3 የኃይል ማመንጫን በመጎብኘት ተጠናቀቀ።

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን እና የክልልና የፌደራል ባለድርሻ አካላት የጋራ ጉባዔ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ መስፍን ሙሉነህ እና የደቡብ ኢትዮጵያ የፋይናንስ ቢሮ ተወካዮች እንዲሁም የጉባዔው ተሳታፊ የክልልና የፌደራል ባለድርሻ አካላት በተሳተፉበት የጊቤ ሦስት የኃይል ማመንጫን ጉብኝት በማድረግ ተጠናቋል። በጉባዔው ማጠቃለያ የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ በክልሉ የሚገኘውን በርካታ እሴት በማስተዋወቅ በክልሉ የሚገኙ የልማት ስራዎች ከክልሉ አልፎ ለሀገር እያደረጉ ያሉትን አስተዋፅዖ በጉልህ አሳይቷል። 15ኛውን ጉባዔ የትግራይ ክልል ለማስተናገድ የተመረጠ ሲሆን ከስድስት ወራት በኋላ በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ የሚካሄድ ይሆናል።

Click the button