ባለስልጣን መስሪያቤቱ ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ጋር በጋራ መስራት በሚያስችላቸው ጉዳዬች ዙሪያ የመግባብያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ፡፡

የስምምነት ማዕቀፉ የመረጃ ልውውጥ፣የጋራ ቁጥጥር፣የአቅም ግንባታ እና የሁለትዮሽ ትብብርን ለማጠናከር ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡

በፕሮግራ ላይ ማብራሪያ የሰጡት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ኃይማኖት ዘለቀ እንደገለጹት ከዚህ ቀደም ከባለስልጣኑ ጋር የተጀመሩ ስራዎች መኖራቸውን ገልጸው በተለይም በዝርዝር የትብብር መስኮች መካከል በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ስም ተመዝግበው ህገ-ወጥ የንግድ ሚዲያ ስራ የሚሰሩ ድርጅቶችን መቆጣጠር ላይ በጋራ መስራት ይጠይቃል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የኢፌዲሪ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ እንደተናገሩት በባለስልጣኑ በርካታ የሙያ ማህበራት መመዝገባቸውን ገልጸው ዜጎች የመደራጀት መብት እንዳላቸው ሁሉ ህግን እና አሰራርን አክብረው መፈጸም ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡ በስምምነት ሰነዱም ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ጋር ያስቀመጥናቸውን ጉዳዬች ትኩረት ሰጥተን እንሰራለን ሲሉ ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን የኢፌዲሪ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣንን ጨምሮ አስራ አንድ የሚመለከታቸው ባለድርሻ የመንግስት ተቋማት ጋር ውጤታማ ሬጉላቶሪ ስርዓት ለማጠናከር የሚያስችል የስምምነት ሰነድ ተፈራርሟል፡፡