


Ethiopian Intergenerational dialogue initiative በትውልዶች መካከል የውይይትን ባህል በማሳደግ ህብረ ብሄራዊት የሆነችውን ኢትዮጵያን በጋራ ለማሳደግ፣ ልዩነቶችን በውይይትና በንግግር መፍታት የሚቻልበትን ሁኔታ ለመፍጠር እንዲሁም ለሀገር ግንባታ፣ ለሰላም እና ለተሻለ እድገት በጋራ በመቆም አስተዋጽዖ ለማድረግ የሚያግዝ ፕሮግራም ነው፡፡ በፕሮግራሙ ላይ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላን ጨምሮ ከተለያዩ የሀይማኖት፣ የፖለቲካ፣ የዲያስፖራ፣ የሲቪክ ማህበራት የተውጣጡ ተሳታፊዎች እንዲሁም በተለያዩ የእድሜ ክልሎች የሚገኙ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል፡፡
ተሳታፊዎች በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ውይይት ያደረጉ ሲሆን አሁን ያለው ትውልድ ችግሮችን በውይይት የሚፈታ ለሀገር እድገት፣ ለሰላም ግንባታ ንግግር ማድረግ ትልቅ ሚና እንዳለው በመረዳት በጋራ እና በአንድነት እንድንቆም የሚረዳ መድረክ እንደሆነ የመድረኩ ተሳታፊዎች ጠቁመዋል፡፡
መድረኩን O yes Global Foundation ያዘጋጀው ሲሆን በእለቱ የፋውንዴሽኑ መስራችና ዳይሬክተር አቶ ከማል አብደላ የኢኒሼተቩን ዝርዝር አላማ እንዲሁም በቀጣይ የሚከናወኑ ተግባራትን በሚመለከት ለተሳታፊዎች ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ፕሮግራሙ የመጀመሪያ እንደመሆኑ የማስተዋወቂያ እና የልምድ መለዋወጫ መድረክ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ከማል ፕሮግራሙን በቀጣይ በተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች በማስተዋወቅ ሀገር አቀፍ እንዲሆን እንሰራለን ብለዋል፡፡

