ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እና ባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ተካሄደ፡፡
በመድረኩ በክብር እንግድነት የተገኙት የኢፌዴሪ የፍትህ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ፍቃዱ ጸጋው በንግግራቸው እንደገለጹት ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በተናጥል በርካታ ስራዎችን ስትሰሩ እንደነበር ይታወቃል ይሁን እና በችግሩ ልክ መፍትሄ ለመስጠት እንዲያስችል በእቅድ መመምራት አስፈላጊ ሆኗል ብለዋል:: ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅችም የተቋቋሙበት ዓላማ ሰብዓዊ ድጋፍ ላይ መስራት ማገዝ ስለሆነ በተናጥል ከመሄድ በጋራ ሆኖ መስራት አስፈላጊ በመሆኑ በተናጥል የነበረውን ስራ የምናቀናጅበት መድረክ እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ ሲሉ ገልጸዋል፡፡ የተራበ ዜጋ እንዳይኖር ተረባርበን የፈረሰውን መገንባት ከቻልን ድላችንን ሙሉ እናደርገዋን ብለዋል፡፡



ይህ ጦርነት ምንም ያህል ጉዳቱ የከፋ ቢሆንም አንድ ያደረገን ፣የሰበሰበን እና ያጠናከረን ጦርነት ነው ጀግኖች ለሃገር እየተሰው ባሉበት ሁኔታ ፕሮጀክቶችንም ቢሆን አጥፈን ሃገር እንድትቀጥል፣የተራበ እንዳይኖር እና የፈረሰን መገንባት ይኖርብናል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ በበኩላቸው አሸባሪው ቡድን የፈጸመውን የክህደት ተግባር ለመመከትና ኢትዬጵያን በብልጽግና ጎዳና ለማስኬድ በግንባር ሕይወቱንና አካሉን መስዋእት እያደረጉ ካሉት ከጀግኖቹ የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት ጎን ለጎን በጦርነቱ ምክንያት የተጎዱ ወገኖችን መርዳትና መልሶ ማቋቋም አንዲሁም የወደሙ መሰረተ ልማቶችን መልሶ መገንባት የዜግነት ሲያልፍም የሰብዓዊነት ግዴታ ነው ብለዋል፡፡ በጦርነቱ በግፍ የተቀጠፈውን ውድ የሆነውን የሰው ልጅ ሕይወት መመለስ ባይቻልም የደረሰውን የሰብዓዊ እና ቁሳዊ ውድመት ለመመለስ የሚያስችል መጠነ ሰፊ ስራ ምናልባትም ለሃገር ሉዓላዊነት ለማዳን ከተሰጠው ትኩረት ባልተናነሰ መልኩ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡

በዚህ ችግር የደረሰው የሰብዓዊና ቁሳዊ ጉዳት በመንግስት ብቻ የሚሸፈን ሳይሆን የብዙ ባለድርሻ አካላትን ርብርብ ይፈልጋል በማለት በተለይም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ከተቋቋሙለት ዓላማ መካከል የሰብዓዊ ቀውሶች ላይ ምላሽ መስጠት መሆኑን አብራርተዋል፡፡ ይህንን ሃገራዊ ጥሪ ተቀብላችሁ በቅንነት የሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረግ ለተገኛችሁ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እና አጋር ድርጅቶች በባለስልጣን መስሪያቤቱ እና በራሴ ስም በቅድምያ ስለምታደርጉት የበጎነት ስራ ምስጋናዬን አቀርባለሁ ሲሉ ገልጸዋል፡፡ ከፌዴራል ብሔራዊ የአደጋና ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ተወክለው የተገኙት አቶ ቢሊየን ሙዳ አጠቃላይ በሃገሪቱ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን የማህበረሰብ ክፍሎች ብሎም ከሲቪል ማህረሰብ ድጀቶች የሚጠበቅ እገዛ ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ወቅታዊ ሃገራዊ ሁኔታ የሲማድ ሚና በተመለከተ እንዲሁም የአማራ፣የኦሮሚያ እና አፋር ክልል ተወክለው የተገኙ ሃላፊዎች በክልሎቹ እየተከናወኑ ስላሉ ተግባራት እና ድጋፍ የሚሹ ዘርፎች ላይ ማብራሪያ አቅርበዋል:: በመድረኩ ከተገኙ 250 የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች መካከል ከመቶ አርባ ሁለት ሚሊየን ብር በላይ በአይነትና በገንዘብም ቃል ተገብቷል፡፡
የበጎ ፍቃድ ስራ እንደ ሃገር በህዝቦች መካከል ያለውን አንድነት ለማጠንከር፣መልካም እሴቶችን ለማዳበር፣ሰላምን ለማስፈን ያለው ሃገራዊ ፋይዳ ከፍተኛ ነው ተባለ፡፡



የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ከፍተኛ አመራርና ሰራተኞች ዓለም አቀፍ የሙስና መከላከል ቀንን አከበሩ፡፡



የነጭ ሪቫን እና የብሔር ብሔረሰቦች ህዝቦች ቀንን በጦርነቱ የተጎዱ ሴቶች፣ህጻናትና ሌሎች ወገኖቻችንን በማሰብ ተከብሯል፡፡



ዓለማቀፍ የበጎ ፍቃደኞች ቀንን ከፓናል ውይይት በተጨማሪ ስለ እናት የበጎ አድራጎት ድርጅትን በመጎብኘት እና የቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ ተከብሯል፡፡



ዓለማቀፍ የበጎ ፍቃደኞች ቀን ‹‹በጎ ፍቃደኝነት ለመልካም ትውልድ ግንባታ›› በሚል መሪ ቃል ተከበረ፡፡
“የዓለም አቀፍ የበጎ ፍቃደኞች ቀን ስናከብር በመድረክም ሆነ በተለያዩ ሚዲያች የማናውቃቸው ነገር ግን ከእኛ በላይ ለሃገራቸው ሉዓላዊነት፣ አንድነት፣ ሰላምና መረጋጋት ማንም ሳያስገድዳቸው በበጎ ፍቃደኝነት አገራቸውንና ህዝባቸውን እያገለገሉ የሚገኙ በርካታ ልበ-ሙሉ ጀግኖቻችንን ልናመሰግናቸው ይገባል፡፡“ ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ

የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ጂማ ዲልቦ በበኩላቸው ባስተላለፉት መልዕክት ሀገራችን የገጠማትን የህልውና ዘመቻ በድል ለማጠናቀቅና በጦርነቱም ምክንያት የተፈናቀሉ ወገኖቻችንን ለመታደግ ከህይወት መስዋትነት ጀምሮ አስፈላውን የህይወት አድን ድጋፎችን በማድረግ ረገድ ዜጎች የሚመለከተውን ሁሉ አስተዋጽኦ በበጎ ፍቃደኝነት በማበርከት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡



የአካል ጉዳትና የአካል ጉዳተኞች ጉዳይ የሁሉም ማህበረሰብ ጉዳይ በመሆኑ ምቹ የሆነ የስራና የመኖሪያ አካባቢ መፍጠር ለነገ የሚባል ጉዳይ አይደለም፡፡



የተሻለች፣ የበለጸገች፣ የዲሞክራሲ ስርአት የሰፈነባት ሀገር በኢትዮጵያ ወጣቶች ግንባር ቀደም ሚና እንገነባለን፡፡
“የተሻለች፣ የበለጸገች፣ የዲሞክራሲ ስርአት የሰፈነባት ሀገር በኢትዮጵያ ወጣቶች ግንባር ቀደም ሚና እንገነባለን፡፡“ ይህ የተባለው “ተስፋ ለኢትዮጵያ” የማህበራዊ ሚዲያ ንቅናቄ ዘመቻ የመክፈቻ መርሃግብር ላይ የባለስልጣኑ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ የተናገሩት ነው፡፡



‹‹ሃገርን ለማዳን መክፈል የሚገባንን ሁሉ እናደርጋለን››
‹‹ሃገርን ለማዳን መክፈል የሚገባንን ሁሉ እናደርጋለን›› ክቡር አቶ ጂማ ዲልቦ በደብረብርሃን ከተማ በመገኘት የተለያየ የምግብና የቁሳቁስ ድጋፍ ለተፈናቃይ ወገኖች እና ለጸጥታ አካላት ድጋፍ ሲያደርጉ የተናገሩት ነው፡፡ ተቋሙ የተለያዩ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችን በማስተባበር በርካታ የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ ያሰባሰበ ሲሆን የመጀመሪያ ዙር ድጋፉን በደብረብርሃን ከተማ በአሸባሪው ህወሓት ወረራ ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች እና ለጸጥታ አካላት ድጋፍ አድርጓል፡፡



የመደራጀት መብት፣ ሰብዓዊነት፣ የህብረተሰቡ የላቀ ተጠቃሚነት!!!
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት!!!
የተቋሙ ሰራተኞች የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል ሰበሰቡ








