‹‹ሃገርን ለማዳን መክፈል የሚገባንን ሁሉ እናደርጋለን›› ክቡር አቶ ጂማ ዲልቦ በደብረብርሃን ከተማ በመገኘት የተለያየ የምግብና የቁሳቁስ ድጋፍ ለተፈናቃይ ወገኖች እና ለጸጥታ አካላት ድጋፍ ሲያደርጉ የተናገሩት ነው፡፡ ተቋሙ የተለያዩ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችን በማስተባበር በርካታ የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ ያሰባሰበ ሲሆን የመጀመሪያ ዙር ድጋፉን በደብረብርሃን ከተማ በአሸባሪው ህወሓት ወረራ ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች እና ለጸጥታ አካላት ድጋፍ አድርጓል፡፡

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ እንደገለጹት ተቋሙ ሃገራችን የተቃጣባትን ዘርፈ ብዙ ችግሮች ለመታደግ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችን በማስተባበር ከስምንት ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የቁሳቁስ እና የገንዘብ ድጋፍ ማሰባሰቡን ገልጸዋል፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም ይህንን ችግር ለመፍታት የጸጥታ አካላት እርብርብ ብቻ በቂ ባለመሆኑ እውቀት ያለው በእውቀቱ ፣ገንዘብ ያለው በገንዘቡ እንዲሁም ጉልበት ያለው ግንባር በመሄድ ይህንን ዘመቻ መቀላቀል አለበት ያሉ ሲሆን እኛም ሃገርን ለማዳን መክፈል የሚገባንን ሁሉ እናደርጋለን ብለዋል፡፡ በመጨረሻም ይህንን ድጋፍ ላደረጉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በሙሉ ምስጋናቸውን በማቅረብ በቀጣይም ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር‼

የመደራጀት መብት፣ ሰብዓዊነት፣ የህብረተሰቡ የላቀ ተጠቃሚነት!!!

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት!!!