“የዓለም አቀፍ የበጎ ፍቃደኞች ቀን ስናከብር በመድረክም ሆነ በተለያዩ ሚዲያች የማናውቃቸው ነገር ግን ከእኛ በላይ ለሃገራቸው ሉዓላዊነት፣ አንድነት፣ ሰላምና መረጋጋት ማንም ሳያስገድዳቸው በበጎ ፍቃደኝነት አገራቸውንና ህዝባቸውን እያገለገሉ የሚገኙ በርካታ ልበ-ሙሉ ጀግኖቻችንን ልናመሰግናቸው ይገባል፡፡“ ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ

ዓለማቀፍ የበጎ ፍቃደኞች ቀን ‹‹በጎ ፍቃደኝነት ለመልካም ትውልድ ግንባታ›› በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ይገኛል፡፡ ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚንስትር በመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለጹት ውዷ ሃገራችን ኢትዬጵያ በፈተና ውስጥ ብትገኝም በቁርጥ ቀን ልጇቿ አንድነትና ትብብር ሉዓላዊነቷን አስከብራ ወደ ከፍተና ብልጽግና መንገዷን ጀምራለች ፡፡ የእናት ጡት ነካሾችና ባንዳዎች አንገታችንን ለማስደፋት እና ውስጣዊ አንድነታችንና መቻቻላችን ለመሸርሸር ያለመውን እኩይ ዓላማ በቅርጥ ቀን ልጆቿ እየፈረሰ ይገኛል ብለዋ፡፡ በዚህ ዓይነት ስሜት ውስጥ ሆነን ‹‹በጎ ፍቃደኝነት ለመልካም ትውልድ ግንባታ›› በሚል መሪ ቃል የዓለም በጎ ፍቃደኝነት ቀን ማክበራችን ትልቅ እንድምታ ይኖረዋል የሚል እምነት አለኝ ምክንያቱም አገር የምትገነባው በስርዓት ታንጾ ባደገ ትውልድ እንዲሁም ቅን ልብ ፣በጎ አድራጊ ፣አስተዋይና ታታሪ ህዝቦች ነው ለዚህም ነው እኛም ይህን ቀን የምናከብረው ሲሉ አብራርተዋል፡፡
ሚኒስትሯ አክለውም እንደዛሬው አይነት የዓለም አቀፍ የበጎ ፍቃደኞች ቀን አጋጣሚዎችን ደግሞ እንደ ሃገር ለመደጋገፍ ለመረዳዳት ለመከባበር ውስጣዊ አንድነታችንን ለማጠናከር በጎ ፍቃደኞቻችንን ለማመስገንና ለማበረታታት ትልቅ አቅም ይሆናል ብዬ አስባለሁ ሲሉ ተናግረዋል፡፡ የዓለም አቀፍ የበጎ ፍቃደኞች ቀን ስናከብር በመድረክም ሆነ በተለያዩ ሚዲያች የማናውቃቸው ነገር ግን ከእኛ በላይ ለሃገራቸው ሉዓላዊነት፣ አንድነት፣ ሰላምና መረጋጋት ማንም ሳያስገድዳቸው በበጎ ፍቃደኝነት አገራቸውንና ህዝባቸውን እያገለገሉ የሚገኙ በርካታ ልበ-ሙሉ ጀግኖቻችን ልናመግናቸው ይገባል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
በመጨረሻም የበጎ ፍቃድና በጎ አድራጊነት ባህል እንዲዳብር ሁላችንም በያገባኛል ስሜት ርብርብ እንድናደርግ በጎ ፍቃደኝነት ከዘመቻ ስራ ተላቆ በስርዓት፣በፖሊሲና በመዋቅር እንዲመራ ክትትልና ድጋፍ እንድታደርጉ እንድንተጋገዝ እየጠየቅኩ ይህንን ፕሮግራም ላስተባበረው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣንና ሌሎች አጋዥ ድርጅቶችን አመሰግናለሁ ብለዋል፡፡

የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ጂማ ዲልቦ በበኩላቸው ባስተላለፉት መልዕክት ሀገራችን የገጠማትን የህልውና ዘመቻ በድል ለማጠናቀቅና በጦርነቱም ምክንያት የተፈናቀሉ ወገኖቻችንን ለመታደግ ከህይወት መስዋትነት ጀምሮ አስፈላውን የህይወት አድን ድጋፎችን በማድረግ ረገድ ዜጎች የሚመለከተውን ሁሉ አስተዋጽኦ በበጎ ፍቃደኝነት በማበርከት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

ይህንኑ የበጎ ፍቃደኝነት ባህል ለማዳበር ተከታታይነት ያለውና የማያቋርጥ ስራ መስራት ያስፈልጋል በተለይም ስራውን ተቋማዊ ማድረግና ዘርፉን በሚገባ የሚመራ የፖሊሲ ሰነድ በመንግስት እንዲጸድቅ ማድረግ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ አብይ ጉዳይ ነው ያሉ ሲሆን ፖሊሲው እስኪጸድቅ ድረስ ግን ይህንኑ ዘርፍ ሊመራ የሚችል ቮለንተሪዝም ፕሮሞሽን ኤንድ ማኔጅመንት ጋይዳንስ ኖት ከተባባሪ አካላት ጋር በማዘጋጀት ስራ ላይ እዲውል ተደርጓል ብለዋል:: በመጨረሻም የዘንድሮው ዓለማቀፍ የበጎ ፍቃደኞች ቀን ከሌላው ጊዜ በተለየ መልኩ ሀገራችን የገጠማትን የመፍረስ አደጋ የምንታደግበት ፣የተፈናቀሉ ወገኖቻችንን የምናቋቁምበት፣በጦርነቱ የወደሙ መሰረተ ልማቶችን አቅማችን በፈቀደው ሁሉ የምንገነባበት ክብረበዓል እንዲሆን በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ በፕሮግራሙ የተለያዩ ሰነዶች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል፡፡