ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ ራዕይ የሕጻናት እና የቤተሰብ ልማት ማህበርን የስራ እንቅስቃሴ ተመለከቱ፡፡

ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ ራዕይ የሕጻናት እና የቤተሰብ ልማት ማህበርን የስራ እንቅስቃሴ ተመለከቱ፡፡

የድርጅቱ መስራችና ባለራዕይ ወ/ሮ ፍሬሕይወት ጉግሳ የረር ሰፈራ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ የግል ት/ቤት ለማስፋፋት ቤት ተከራይተው አስፈላጊውን ግብዓትና ቁሳቁስ በሟሟላት ለምዝገባ በራቸውን ከፍተው ቢጠብቁም በወቅቱ ልጆቻቸውን አስመዝግበውና ከፍለው ለማስተማር አቅም ያላቸው የሕብረተሰብ ክፍሎች በዛን አከባቢ አልነበሩም፡፡
በአንጻሩ ልጆቻቸውን ለማስመዝገብ የሚመጡት በጣም ችግረኞችና በተለያየ ህመም የተጎዱ ወላጆች/አሳዳጊዎች ሲሆኑ የእነርሱም ጥያቄ ምንም ዐይነት የገቢ ምንጭ የሌላቸውና አቅመ ደካማ ስለሆኑ በነጻ አስተምሩልን የሚል ሀዘን የተሞላበትና ልብን የሚነካ ጥያቄ ነበር፡፡
ይህ ሁኔታ የመስራቿን የወ/ሮ ፍሬሕይወት እና የቤተሰቡን ልብ ስለነካ ማን ፈረንጅ ብቻ ረጂ አደረገው እኛ ኢትዮጵያዊያን የራሳችንን ዜጎች መርዳት እንችላለን በሚል ቁጭት የግል ትምህርት ቤት ለማስፋፋት የነበራቸውን እቅድ ወደ ጎን በመተው በፍቃደኝነት የበጎ አድራጎት አገልግሎት ለመስጠት ድርጅቱ በ1998 ዓ.ም ህጋዊ ፍቃድ አግኝቶ እንደተመሰረተ ወ/ሮ ፍሬሕይወት ጉግሳ ነግረውናል ፡፡
ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ የድርጅቱን የስራ እንቅስቃሴ ከተመለከቱ በኋላ ድንገተኛ ጉብኝት /Surprise visit/ ብናደርግም በተመለከትኩት ስራ ተደስቻለሁ ብለዋል፡፡
በርካታ እንደነዚህ አይነት ድርጅቶች እራሳቸውን ሳይገልጹ በየቦታው ማህበረሰብን የሚያገለግሉ መኖራቸውን እንረዳለን ያሉት ም/ዋና ዳይሬክተሩ ሃሳብን በመሸጥ እና የገቢ ማስገኛ ስራ ላይ በመሰማራት የድርጅቱን ራዕይ ማስቀጠል ያስፈልጋል ለዚህም ተቋማችን አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ድርጅቱ በአሁኑ ግዜ ሁለት መቶ ስልሳ ሰባት ተማሪዎችን በመቀበል ከኬጂ አስከ አራተኛ ክፍል በማስተማር ላይ የሚገኝ ሲሆን የተማሪዎቹን ቁርስና ምሳ፣ህክምና እንዲሁም የትምህርት ቁሳቁስ ወጪን ይሸፍናል፡፡


    China Foundation for Rural Development በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ስር ለሚገኙ የየካ ቦሌና የዱቢሳ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመማር ማስተማር ሂደት የሚረዱ የትምህርት ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ።

    China Foundation for Rural Development በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ስር ለሚገኙ የየካ ቦሌና የዱቢሳ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመማር ማስተማር ሂደት የሚረዱ የትምህርት ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ።

    በፕሮግራሙ የክፍለ ከተማው ስራ አስፈጻሚ ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እና ተጋባዥ እንግዶች ታዳሚ ሆነዋል፡፡
    በፕሮግራሙ ላይ ንግግር ያደረጉት የተቋሙ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ እንዳሉት ከለውጡ በኋላ ለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምቹ ሁኔታ የተፈጠረ መሆኑን አስታውሰው ይህንን እድል በመጠቀም በርካታ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በተቋሙ መመዝገብ መቻላቸውን ገልጸዋል፡፡
    China Foundation for Rural Development የተባለ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅትም ይህንን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም የተመዘገበ እና ትምህርት ላይ የሚሰራ መሆኑን አንስተዋል፡፡
    ም/ዋና ዳይሬክተሩ በከተማ አስተዳደሩ የተከናወኑ ሰው ተኮር ስራዎች አድንቀው በአዲስ አበባ ከተማ የሚንቀሳቀሱ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችም ይህንን ልማት ተኮር ስራዎች እንድደግፉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡
    የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ በበኩላቸው ድርጅቱ ከትምህርት ጋር ተያይዞ በርካታ ስራዎችን እየሠራ መሆኑን ገልጸው ከተማ መስተዳድሩም ከሌሎች አጋር አካላት ጋር በጋራ በመረባረብ ትምህርት ቤቶች ለተማሪዎች ምቹ፣ሳቢ እንዲሁም ማራኪ የማድረግ ስራ በቀጣይ ትኩረት አድርገን እንሰራለን ብለዋል፡፡
    ድርጅቱ በትምህርት ላይ የሚሰራ ሲሆን በዚህ በጀት ዓመት ብቻ በሃገሪቱ ለአርባ አምስት ሺህ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡


      የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ለ11ኛ ጊዜ የደም ልገሳ መርኃ ግብር አከናውኗል፡፡

      የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ለ11ኛ ጊዜ የደም ልገሳ መርኃ ግብር አከናውኗል፡፡

      የደም ልገሳ መርኃ ግብሩ በዋነኛነት የተቋሙ ሰራተኞች በበጎ ስራዎች ላይ እንዲሳተፉ እና የበጎ ፈቃደኝነት ባህል በተቋሙ ሰራተኞች እንዲዳብር ማድረግን ዓላማ ያደረገ ሲሆን በቋሚነት በየሶስት ወሩ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ በደም ልገሳ መርኃ ግብሩ ላይ የተለያዩ የስራ ክፍል ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡


        ለተቋሙ አጠቃላይ ሰራተኞች በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ስልጠና ተሰጠ፡፡

        ለተቋሙ አጠቃላይ ሰራተኞች በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ስልጠና ተሰጠ፡፡

        በስልጠናው ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የተቋሙ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ በፍቃዱ ወ/ሰንበት የሰራተኛውን የመፈጸምና የማስፈጸም አቅም ለማጎልበት፣ በብቃትና በእውቀት ስራዎችን እንዲያከናውኑ ለማስቻል ስልጠናዎች ሲሰጥ መቆየቱን ገልጸው በዘንድሮ በጀት ዓመትም ተመሳሳይ ስልጠናዎች ለመስጠት በእቅድ መያዙን እና ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡ በመድረኩ የአገልግሎት አሰጣጥ፣የበጎ ፍቃድ ምንነት፣የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ህዝባዊና ሃገራዊ ፋይዳ ፣በሃገራችን ያለው የበጎ ፍቃድ አተገባበር እና ሌሎች ጉዳዮች በሰነድ ቀርበው ውይይት ተደርጎበታል፡፡


          የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ Heavenly culture, World peace, Restoration of Light የተባለ አለም አቀፍ ድርጅት ማናጀር ጋር በጽ/ቤታቸው ተወያዩ፡፡

          የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ Heavenly culture, World peace, Restoration of Light የተባለ አለም አቀፍ ድርጅት ማናጀር ጋር በጽ/ቤታቸው ተወያዩ፡፡

          Heavenly culture, World peace, Restoration of Light መቀመጫውን በኮሪያ ያደረገው ድርጅት በኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ቢሮ ለመክፈት የሚያስችለውን ቅድመ ሁኔታዎች በተመለከተ ከባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ጋር ፍሬያማ ውይይት አድረገዋል ፡፡
          በውይይቱ ዋና ዳይሬክተሩ እንዳሉት በሰላም፣በዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ላይ የሚንቀሳቀሱ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አስፈላጊ መሆናቸውን ገልፀው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከዚህ ረገድ የሚያግዝና የሚያበረታታ መሆኑን አንስተዋል፡፡ አያይዘውም Heavenly culture, World peace, Restoration of Light ድርጅትም በኢትዮጵያ ከሰላም አንጻር ለመስራት በማሰቡ ምስጋናቸውን በማቅረብ ባለስልጣኑ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልፀዋል፡፡ የድርጅቱ ዳይሬክተር በበኩላቸው ድርጅታቸው ከ20 በሚበልጡ አገራት ላይ ሰላምን ከማስፈን አንጻር በርካታ ስራዎች እየሰሩ መሆኑን በመግለጽ በኢትዮጵያም ቅርንጫፍ ቢሮ በመክፈት ያላቸውን ልምድና ተሞክሮዎችን ለማካፈል አንዳሰቡ ተናግረዋል፡፡


            በዝውውር ለመጡ ሰራተኞች በአዋጅ1064/2010 እና በስነምግባር ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡

            በዝውውር ለመጡ ሰራተኞች በአዋጅ1064/2010 እና በስነምግባር ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡

            ባለስልጣን መስሪያቤቱ ከመንግስት መስሪያቤት በዝውውር ለመጡ ሰራተኞች የተቋሙን አጠቃላይ ሁኔታ እና በሁለት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ስልጠና ሰጠ፡፡
            በስልጠናው ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣን መስሪያቤቱ የስራ አመራር ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተስፋዬ ሽፈራው እንዳሉት ባለስልጣን መስሪያቤቱ በአዋጅ 1113/2011 በአዲስ አደረጃጀት የተዋቀረ መሆኑን በማንሳት የተሰጠውን ተልዕኮ በአግባቡ እየተዋጣ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡ አያይዘውም በተቋሙ ያሉ ሰራተኞች የተለያየ የስራ ድርሻ ቢኖራቸውም ለተቋሙ የተሰጠውን ሀላፊነት ከግብ እንዲደርስ የድርሻውን መወጣት እንዳለባቸው አንስተዋል፡፡ ሌላ ያነሱት አዋጁን በሚገባ በመረዳት እና ስራዎችን በጋራ እና በመተጋገዝ በመስራት ተቋሙ ያስቀመጣቸውን እሴቶችንም በማወቅ መተግበር እንዳለባቸው ስራ አስፈጻሚው አንስተዋል፡፡
            የብቃትና የሰው ሀብት አስተዳደር ስራ አስፈጻሚ አቶ ደጀኔ እንዳሉት ይህ ስልጠና መሰጠት የነበረበት ቀድሞ ቢሆንም የተመደቡት ሰራተኞች በወቅቱ ባለመምጣታቸው ሊዘገይ መቻሉን አንስተው ስልጠናው አስፈላጊ በመሆኑ ሰልጣኞች ትኩረት ሰጥተው መከታተል እንደሚገባቸው አሳስበዋል፡፡


              ተቋሙ የ2016 ሩብ ዓመት አፈጻጸም በማኔጅመንት ደረጃ ገምግሟል፡፡

              ተቋሙ የ2016 ሩብ ዓመት አፈጻጸም በማኔጅመንት ደረጃ ገምግሟል፡፡

              በሪፖርቱ በዝግጅት ምዕራፍ የተከናወኑ በርካታ ጉዳዬች ተነስተው ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን የዴስክና የመስክ ክትትል አፈፃፀማችን የተሻለ መሆኑ፤ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችና ባለድርሻ አካላት ጋር የሚካሄዱ መድረኮች ወቅቱን ጠብቀው መካሄዳቸው፤በፀደቁ መመሪያዎች ለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እና ባለድርሻ አካላት ስልጠና ፤በጎ ፈቃደኛንና በጎ ፈቃድ ፈላጊ ድርጅቶችን ሊያገናኝ የሚችል ሶፍትዌር (VMIS) በልፅጎና ደረጃው ተሻሽሎ ስራ ላይ መዋሉ እና አቅምን ሊያሳድጉ የሚችሉ ስልጠናዎች ለሰራተኞች መሰጠቱ በአፈጻጸሙ የታዩ ጠንካራ ጎኖች መሆናቸው ተገምግሟል፡፡
              ከግዢና ከፋይናንስ አጠቃቀም አንጻር መሻሻል ስለሚገባቸው ጉዳዮችም ተጠቁሟል፡፡


                4ተኛው ተቋማዊ የንባብ ቀን በደማቅ ሁኔታ ተካሂዷል፡፡

                4ተኛው ተቋማዊ የንባብ ቀን በደማቅ ሁኔታ ተካሂዷል፡፡

                በመርሃ ግብሩ የንባብ ክህሎትን የሚያጎለብቱ የሰራተኞችን የእርስ በእርስ ግንኙነት የሚያጠናክሩ ዝግጅቶች ቀርበዋል፡፡


                የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በኢትዮጵያ የተርኪዬ አምባሳደር ከሆኑት በርክ ባራን ጋር ተወያይተዋል፡፡

                የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በኢትዮጵያ የተርኪዬ አምባሳደር ከሆኑት በርክ ባራን ጋር ተወያይተዋል፡፡

                የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ በኢትዮጵያ የተርክዬ አንባሳደር የሆኑትን አምባሳደር በርክ ባራንን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡ በውይይታቸው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር በተያያዘ እየሰራቸው ስለሚገኙ ስራዎች እንዲሁም ከተርኪዬ መንግስትና በተርኪዬ ከሚገኙ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር ስላለው ጠንካራ ግንኙነት ሰፊ ውይይት አድርገዋል፡፡
                ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ በኢትዮጵያ በተለያዩ ስራዎች ላይ የተሰማሩ የተርክዬ ባለሃብቶች ማህበራዊ ሃላፊነታቸውን ለመወጣት ድርጅቶችን ቢከፍቱ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ድጋፍ እንደሚያደርግ ጠቁመዋል፡፡ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ዓይነተኛ ሚና ያላቸው በመሆኑ መንግስት ትብብርንና አጋርነትን መሰረት ያደረገ ስትራቴጂ የሚከተል መሆኑን አንስተው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱም ይህን መርህ ተከትሎ ግልጽና ህግን መሰረት ያደረገ ድጋፋዊ ከትትል እያደረገ እንደሚገኝ ገልጸዋለል፡፡
                አምባሳደር በርክ ባራን በተደረገላቸው ገለጻ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው በቀጣይም ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጋር በጋራ በርካታ ስራዎችን እንደሚሰሩ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡


                  የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከአፍሪካን ዲሴቢሊቲ ፎረም (African disability forum) እና ሴንተር ፎር ኢንተርናሽናል ፕራይቬት ኢንተርፕራይዝ (center for international private enterprise) ከተባሉ ሁለት ዓለም ዓቀፍ ድርጅቶች ጋር የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ፡፡

                  የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከአፍሪካን ዲሴቢሊቲ ፎረም (African disability forum) እና ሴንተር ፎር ኢንተርናሽናል ፕራይቬት ኢንተርፕራይዝ (center for international private enterprise) ከተባሉ ሁለት ዓለም ዓቀፍ ድርጅቶች ጋር የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ፡፡

                  ከአፍሪካን ዲሴቢሊቲ ፎረም (African disability forum) እና ሴንተር ፎር ኢንተርናሽናል ፕራይቬት ኢንተርፕራይዝ (center for international private enterprise የተባሉ ሁለት ኣለም ዓቀፍ ድርጅቶች በኢትዮጵያ ክልላዊ (regional) ቢሯቸውን ለመክፈት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ጋር ተፈራርመዋል፡፡
                  የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ ስምምነቱን በፈረሙበት ወቅት እንደገለጹት ድርጅቶቹ በኢትዮጵያ ክልላዊ ቢሮ ለመክፈት በመምጣታቸው ደስተኛ መሆናቸውን ጠቁመው መሰል ድርጅቶችም በኢትዮጵያ ክልል አቀፍና አህጉር አቀፍ ቢሮዎችን ቢከፍቱ ፍላጎታቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡
                  የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ በበኩላቸው ቀደም ሲል በሁለትዮሽ ስምምነት ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ድርጅቶች ወደባለስልጣን መስሪያ ቤቱ መጥተው እንዲመዘገቡ እና መስራት ኢንዲችሉ የሚያስችል ምቹ ሁኔታዎች በአዋጅ ቁጥር 1113/11 መፈጠሩን አንስተው ትብብርንና አጋርነትን መሰረት ያደረገ ግንኙነት እንደሚኖራቸው ጠቁመዋል፡፡
                  በአፍሪካን ዲሴቢሊቲ ፎረም በኩል የስምምነት ፊርማቸውን ያኖሩት ወ/ሮ ሽታየ አስታወስ ድርጅታቸው በ45 ሀገራት ከ56 በላይ አባላትን ይዞ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኝ በድህነት ቅነሳ ላይ አካል ጉዳተኞችን አካታች ያደረገ የፖሊሲ ለውጥ እንዲመጣ የሚሰራ ድርጅት መሆኑን አንስተው ይህ የተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት የድርጅቱን የአፍሪካ ቅርንጫፍ ቢሮ በኢትዮጵያ ለመክፈት የሚያስችል ስምምነት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
                  በሴንተር ፎር ኢንተርናሽናል ፕራይቬት ኢንተርፕራይዝ በኩል የመግባቢያ ስምምነቱን የፈረሙት የድርጅቱ የምስራቅ አፍሪካ ተወካይ አቶ ኃይለመለኮት አስፋው በበኩላቸው ድርጅታቸው በሴንተር ፎር ኢንተርናሽናል ፕራይቬት ኢንተርፕራይዝ ከ40 ዓመታት በፊት የተመሰረተና ጠንካራ የግል ተቋም በመፍጠር ዲሞክራሲን ማሳደግ ላይ እንደሚሰራ ገልጸው በአሁን ጊዜ ከ75 በላይ በሚሆኑ ሀገራት ላይ እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ አክለውም ድርጅቱ በኢትዮጵያ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን እየሰራ እንደሚገኝ ጠቁመው ይህ የመግባቢያ ስምምነት የድርጅቱን የምስራቅ አፍሪካ ቢሮ ለመክፈት ከማስቻሉም ባሻገር በርካታ ጠቀሜታዎች እንደሚኖሩት አንስተዋል፡፡