በዝውውር ለመጡ ሰራተኞች በአዋጅ1064/2010 እና በስነምግባር ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡

ባለስልጣን መስሪያቤቱ ከመንግስት መስሪያቤት በዝውውር ለመጡ ሰራተኞች የተቋሙን አጠቃላይ ሁኔታ እና በሁለት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ስልጠና ሰጠ፡፡
በስልጠናው ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣን መስሪያቤቱ የስራ አመራር ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተስፋዬ ሽፈራው እንዳሉት ባለስልጣን መስሪያቤቱ በአዋጅ 1113/2011 በአዲስ አደረጃጀት የተዋቀረ መሆኑን በማንሳት የተሰጠውን ተልዕኮ በአግባቡ እየተዋጣ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡ አያይዘውም በተቋሙ ያሉ ሰራተኞች የተለያየ የስራ ድርሻ ቢኖራቸውም ለተቋሙ የተሰጠውን ሀላፊነት ከግብ እንዲደርስ የድርሻውን መወጣት እንዳለባቸው አንስተዋል፡፡ ሌላ ያነሱት አዋጁን በሚገባ በመረዳት እና ስራዎችን በጋራ እና በመተጋገዝ በመስራት ተቋሙ ያስቀመጣቸውን እሴቶችንም በማወቅ መተግበር እንዳለባቸው ስራ አስፈጻሚው አንስተዋል፡፡
የብቃትና የሰው ሀብት አስተዳደር ስራ አስፈጻሚ አቶ ደጀኔ እንዳሉት ይህ ስልጠና መሰጠት የነበረበት ቀድሞ ቢሆንም የተመደቡት ሰራተኞች በወቅቱ ባለመምጣታቸው ሊዘገይ መቻሉን አንስተው ስልጠናው አስፈላጊ በመሆኑ ሰልጣኞች ትኩረት ሰጥተው መከታተል እንደሚገባቸው አሳስበዋል፡፡