የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በኢትዮጵያ የተርኪዬ አምባሳደር ከሆኑት በርክ ባራን ጋር ተወያይተዋል፡፡

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ በኢትዮጵያ የተርክዬ አንባሳደር የሆኑትን አምባሳደር በርክ ባራንን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡ በውይይታቸው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር በተያያዘ እየሰራቸው ስለሚገኙ ስራዎች እንዲሁም ከተርኪዬ መንግስትና በተርኪዬ ከሚገኙ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር ስላለው ጠንካራ ግንኙነት ሰፊ ውይይት አድርገዋል፡፡
ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ በኢትዮጵያ በተለያዩ ስራዎች ላይ የተሰማሩ የተርክዬ ባለሃብቶች ማህበራዊ ሃላፊነታቸውን ለመወጣት ድርጅቶችን ቢከፍቱ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ድጋፍ እንደሚያደርግ ጠቁመዋል፡፡ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ዓይነተኛ ሚና ያላቸው በመሆኑ መንግስት ትብብርንና አጋርነትን መሰረት ያደረገ ስትራቴጂ የሚከተል መሆኑን አንስተው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱም ይህን መርህ ተከትሎ ግልጽና ህግን መሰረት ያደረገ ድጋፋዊ ከትትል እያደረገ እንደሚገኝ ገልጸዋለል፡፡
አምባሳደር በርክ ባራን በተደረገላቸው ገለጻ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው በቀጣይም ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጋር በጋራ በርካታ ስራዎችን እንደሚሰሩ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡