ተቋሙ የ2016 ሩብ ዓመት አፈጻጸም በማኔጅመንት ደረጃ ገምግሟል፡፡

በሪፖርቱ በዝግጅት ምዕራፍ የተከናወኑ በርካታ ጉዳዬች ተነስተው ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን የዴስክና የመስክ ክትትል አፈፃፀማችን የተሻለ መሆኑ፤ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችና ባለድርሻ አካላት ጋር የሚካሄዱ መድረኮች ወቅቱን ጠብቀው መካሄዳቸው፤በፀደቁ መመሪያዎች ለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እና ባለድርሻ አካላት ስልጠና ፤በጎ ፈቃደኛንና በጎ ፈቃድ ፈላጊ ድርጅቶችን ሊያገናኝ የሚችል ሶፍትዌር (VMIS) በልፅጎና ደረጃው ተሻሽሎ ስራ ላይ መዋሉ እና አቅምን ሊያሳድጉ የሚችሉ ስልጠናዎች ለሰራተኞች መሰጠቱ በአፈጻጸሙ የታዩ ጠንካራ ጎኖች መሆናቸው ተገምግሟል፡፡
ከግዢና ከፋይናንስ አጠቃቀም አንጻር መሻሻል ስለሚገባቸው ጉዳዮችም ተጠቁሟል፡፡