የአካል ጉዳትና የአካል ጉዳተኞች ጉዳይ የሁሉም ማህበረሰብ ጉዳይ በመሆኑ ምቹ የሆነ የስራና የመኖሪያ አካባቢ መፍጠር ለነገ የሚባል ጉዳይ አይደለም፡፡



የተሻለች፣ የበለጸገች፣ የዲሞክራሲ ስርአት የሰፈነባት ሀገር በኢትዮጵያ ወጣቶች ግንባር ቀደም ሚና እንገነባለን፡፡
“የተሻለች፣ የበለጸገች፣ የዲሞክራሲ ስርአት የሰፈነባት ሀገር በኢትዮጵያ ወጣቶች ግንባር ቀደም ሚና እንገነባለን፡፡“ ይህ የተባለው “ተስፋ ለኢትዮጵያ” የማህበራዊ ሚዲያ ንቅናቄ ዘመቻ የመክፈቻ መርሃግብር ላይ የባለስልጣኑ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ የተናገሩት ነው፡፡



‹‹ሃገርን ለማዳን መክፈል የሚገባንን ሁሉ እናደርጋለን››
‹‹ሃገርን ለማዳን መክፈል የሚገባንን ሁሉ እናደርጋለን›› ክቡር አቶ ጂማ ዲልቦ በደብረብርሃን ከተማ በመገኘት የተለያየ የምግብና የቁሳቁስ ድጋፍ ለተፈናቃይ ወገኖች እና ለጸጥታ አካላት ድጋፍ ሲያደርጉ የተናገሩት ነው፡፡ ተቋሙ የተለያዩ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችን በማስተባበር በርካታ የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ ያሰባሰበ ሲሆን የመጀመሪያ ዙር ድጋፉን በደብረብርሃን ከተማ በአሸባሪው ህወሓት ወረራ ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች እና ለጸጥታ አካላት ድጋፍ አድርጓል፡፡



የመደራጀት መብት፣ ሰብዓዊነት፣ የህብረተሰቡ የላቀ ተጠቃሚነት!!!
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት!!!
የተቋሙ ሰራተኞች የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል ሰበሰቡ


"ደማችን ለመከላከያ ሰራዊታችን"





በደም ልገሳ መርሃ ግብሩ ላይ የታደሙት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ሰራተኞችና አመራሮችም በቀጣይ የአገራችን ህልውና እስኪረጋገጥና ሰላም ሰፍኖ ሀገራችን ወደልማቱ ፊቷን እስክታዞር ድረስ የማያቋርጥ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ገልፀዋል፡፡
በዴሞክራሲና በሰብዓዊ መብት ላይ ለተሰማሩ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ስልጠና ተሰጠ፡፡

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከፕሮጀስቲስ ሪሰርች ኤንድ ትሬኒንግ ሴንተር ጋር በመተባበር በዴሞክራሲና በሰብዓዊ መብት ላይ ለተሰማሩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በተለያዩ ዙሮች በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ህግና አስተዳደር ዙሪያ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡ በስልጠናው ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ እንደተናገሩት የቀድሞው አዋጅ ቁጥር 621/2001 በርካታ ክፍተቶች የነበሩበት መሆኑን ጠቁመው በተለይም ድርጅቶች ቦርዱ በወሰነው ውሳኔ ላይ ይግባኝ ብለው ወደ ፍርድ ቤት የማይሄዱበትና የገቢ ምንጫቸው ከውጪ የሆኑ ድርጅቶችንም እንቅስቃሴ በእጅጉ የገደበ ነበር ሲሉ ገልፀዋል፡፡ አያይዘውም ለውጡ ይዟቸው ከመጣቸው ቱርፋቶች አንዱ ሴክተሩ ነጻና ገለልተኛ ሆኖ መንቀሳቀስ እንዲችል ገዳቢ እና አሳሪ የነበረውን ህግ ማሻሻልና መለወጥ ነው፡፡ ይህ የሆነበት ዋና ምክንያትም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በሀገር ልማት፣ እድገትና ብልጽግና እንዲሁም ሰላም ትልቅ ሚና ያላቸው በመሆኑና በህገ መንግስቱ የተቀመጠውን የመደራጀት መብት ድንጋጌ ለመፈጸም ነው ሲሉ አብራርተዋል፡፡




የመደራጀት መብት፣ ሰብዓዊነት፣ የህብረተሰቡ የላቀ ተጠቃሚነት!!!
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት!!!
"ለ21 ቀን የደም መስጠት ድጋፍ ለወገናችን"


ሁሉም ኢትዮጵያዊ ከቃል በላይ በተግባር ከመከላከያ ጎን በመቆም ደጀንነቱን እየገለፀ እንደሚገኝ በመግለጽ ይህንንም አጠናክሮ መቀጠል አለበት ተብሏል፡፡ በመርሀ ግብሩ ላይም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጥምረት ለኢትዮጵያ (ኮክሲ) ከተለያዩ የመንግስት ተቋማት ጋር የመግባቢያ ስምምነት በመፈራረም የመጀመሪያ ዙር የደም ልገሳ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እንደሚጀመር እና በቀጣይ በሁሉም ክለሎችና የመንግስት ተቋማት ጋር እንደሚከናወን ተገልጿል፡፡

የመደራጀት መብት፣ ሰብዓዊነት፣ የህብረተሰቡ የላቀ ተጠቃሚነት፡፡
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬትRead more
በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳይ ላይ የኤጀንሲው አመራርና ሰራተኞች ውይይት አደረጉ፡፡
ውይይቱ በዋናነት በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳይ ላይ የመንግስት ሰራተኛው ሚና ምንድን ነው የሚል ሲሆን በዚህ ዙሪያ የተዘጋጀ ሰነድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ ከውይይቱ በኋላ የባለስልጣን መስሪያቤቱ አመራርና ሰራተኞች 9 የአቋም መግለጫዎችን አውጥተዋል፡፡
-
- አሸባሪው ትህነግ/ህውሃት በአገራችን ህዘብ ትግል የተረጋገጠውን ለውጥ እንዲቀለበስ ከለውጡ መባቻ ጀምሮ ሳያሳልስ ሰው ሲገድል፣ ሲያፈናቅል አገራችን እንደትበታተን ሲሰራ የነበረውን እኩይ ተግባር ቀጥሎበት የአገር መከታ የሆነውን መከላከያችን በተለይም በሰሜን እዝ ላይ ያደረሰውን ጥቃት በፅኑ እናወግዛለን፤
- አሸባሪው ትህነግ/ህውሃት በአገራችን ላይ የጀመረውን ጥቃት አጠናክሮ በመቀጠል በአማራና አፋር ክልል እያደረገ ያለውን ወራር እንዲሁም እያደረሰ ያለውን ውድመት በከፍተኛ ደረጃ እናወግዛለን፤ ይህ ወረራ እንዲቀለብስ በአስፈላጊው ሁሉ እንፋለማለን፤
- በባለስልጣኑ መስሪያ ቤት ተመዝግበው በአገራችን የሚንቀሳቀሱ የአገር በቀል እና የውጭ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የአገራችንን ህልውና የማስጠበቅ እንቅስቃሴው ጎን በመቆም የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ እናሳስባለን፤ ህግን የሚተላለፉት ላይ ደግሞ ተገቢውን የእርምት እርምጃ የምንወስድ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- ምእራብውያን እና አንዳንድ ዓለም አቀፍ ተቋማት ከአሸባሪው ጎን በመቆም አገር በማፍረስ ሂደት ላይ በመሳተፍ በአሳፋሪ የታሪክ መስመር ላይ እንዳይሰለፉ አካሄዳቸው ቆም ብለው እንዲመረምሩ እና ከኢትዮጵያ ህዝብ ጎን እንዲቆሙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፤
- በአሸባሪው ትህነግ እና ተላላኪዎች ጭምር በውሸት ሀገርን ለማፍረስ የሚያደርጉትን ተግባርና እኩይ ሴራ ለማጋለጥ ዝግጁ መሆናችንን እናረጋግጣለን፡፡
- ሁላችንም የተቋማችንን እና የአከባቢያችንን ሰላም እና ጸጥታ ዘብ ሆነን ለመጠበቅ ዝግጁ መሆናችንን እናረጋግጣለን፡፡
- በተቋማችን የተሰጠንን ተግባርና ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት፤ ከመንግስት የስራ ሰዓት ውጭ ለመስራት ዝግጁ መሆናችንን እናረጋግጣለን፡፡
- የሀሰት የመረጃ ምንጮችን ላለመጠቀም እና እውነተኛ መረጃን ለማሰራጨት ቃል እንገባለን፡፡
- ሃገራችን በምትፈልገን በማንኛውም አይነት ተልዕኮ ለመሰማራት ዝግጁ መሆናችንን እናረጋግጣለን፡፡



አልረሳውም፤ እኔም የኢትዮጵያ ወታደር ነኝ!!!



አያይዘውም አሁንም ይህንኑ የክህደት ተግባሩን በማጠናከር ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር በማበር በህዝባችን ላይ መከራና ሰቆቃ በማድረስ ላይ ይገኛል፡፡ በመሆኑም የህዝባችንን ሰቆቃ ለማስቆምና የሀገራችንን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ ሁላችንም የበኩላችንን ልንወጣ ይገባል፡፡ በዚህ አጋጣሚ ከጁንታው ጋር በማበር በውስጣችን ሆነው መረጃ በማቀበልና አመቺ ጊዜ ፈልገው ጥቃት የሚፈጽሙብንን ጸንተን ያለርህራሄ ልንታገላቸው ይገባል፡፡ የጠላት መሣሪያ የሆኑ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችንም እየለየን ተገቢውን ህጋዊ እርምጃ መውሰድ ለነገ የሚባል ጉዳይ አይደለም፡፡ ከአትዮጵያ የምናስቀድመው ምድራዊ ሃይል ሊኖር አይገባምና! ድላችንን እውን እስኪሆን ድረስ እንደ አንድ ልብ መካሪ፣ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ በመሆን አሸባሪንና ወራሪውን ጁንታ ልንዋጋው ይገባል፡፡ የምንኖርበትና የምንሠራበትን አካባቢዎች ነቅተን መጠበቅ ይኖርብናል፡፡ ይህንን ከሃዲ ጁንታ የመዋጋት ኃላፊነት የጥቂቶች ብቻ ሳይሆን የሁላችንም መሆኑን በመገንዘብ መላው የተቋማችን ሰራተኞችና አመራሮች በምንችለው መንገድ ሁሉ ሀገራችንን እንድንታደግና ለመከላከያ ሰራዊታችንና ለመላው የጸጥታ ኃይሎች አስፈላጊን ድጋፍ እንድናደርግ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በመጨረሻም በዚሁ አጋጣሚ ድላችንን ለማፋጠን ሲባል በትናትናው ዕለት የወጣውን የአስቸኳያ ጊዜ አዋጅ በማክበርና በማስከበር የበኩላችንን መወጣት እንደሚገባን ለማሳሰብ እወዳለሁ በማለት ገልጸዋል፡፡

ለአገር ባለውለታ የሆኑ አረጋውያን እድሜያቸው ሲገፋና አቅማቸው ሲዳከም እንዳገለገለ እቃ መጣል የለባቸውም ተባለ፡፡











