የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዳይሬክተር የብሪቲሽ ኤንባሲ የልማት ዳይሬክተር የሆኑትን ፖል ዋልተርስን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡




የስነ-ምግባር ተምሳሌትና አርበኞች ሆነን መገኘት ይኖርብናል::


የስልጠናው ዓላማ ማሻሻያ ተደርጎበት ስራ ላይ የዋለውን የፌዴራል የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1236/2ዐ13 ለኤጀንሲው አመራሮች ማስተዋወቅ፣የኮሚሽኑን አዋጅ መነሻ በማድረግ እንደ አዲስ የተደራጀውን የስነ-ምግባር መከታተያ ክፍሎች ተጠሪነት፣ የአሰራርና አደረጃጀት ማሳወቅ፣የስነ-ምግባር መከታተያ ክፍል የተቋቋመበትን ዓላማ የኤጀንሲው አመራሮች አውቀውት ቅንጅታዊ አሰራርን ለመዘርጋት፣መከታተያ ክፍሉ ስራውን በሚያከናውንበት ጊዜ በግልጽነት፣ በተጠያቂነትና በገለልተኝነት መርህ መፈፀም እንዲችል ከተቋሙና ከኮሚሽኑ ጋር የሚኖረውን አሰራርና ግንኙነት ግልጽ ማድረግ በማስፈለጉ እንዲሁም ሙስናና ብልሹ አሰራርን መከላከል የአንድ ክፍል ስራ ብቻ ሳይሆን ቅንጅታዊ አስራርና ትብብር የሚጠይቅ በመሆኑ ስልጠናው መዘጋጀቱን ወ/ሮ ትግስት አቡዬ የስነ ምግባር መከታተያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አብራርተዋል፡፡

ኤጀንሲው ከኢስት አፈሪካ ፖሊሲ ሪሰርች ኢኒስቲቲዩት ጋር በጋራ በመሆን በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ዙሪያ በጋራ ጥናት ለመስራት የመግባብያ ሰነድ ተፈራረሙ፡፡
ዓላማውም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ለሃገር ያላቸውን አስተዋጽኦ አጉልቶ ማውጣትና ያሉባቸውን ችግሮች በመለየት አማራጭ ሃሳቦች እንዲቀርቡ ለማድረግ ብሎም የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎአቸውን ለማሳየት መሆኑ ተገልጿል፡፡


በኢትዮጵያ የሲቪል ማህበራት ይዘት ጥናት ሪፖርት ላይ ውይይት ተደረገ፡፡
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከcivil society fund III እና CSSP II ጋር በመሆን በሀገር አቀፍ ደረጃ ባዘጋጁት የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበራት ይዘት ጥናት ረቂቅ ሪፖርት ላይ በኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል ውይይት አድርገዋል፡፡ በውይይቱ ላይ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተርን ጨምሮ በርካታ የአውሮፓ ህብረትና ዓለም ዓቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች እንዲሁም የክልልና የፌዴራል ባለድርሻ አካላት ታድመዋል፡፡
በመርኃ ግብሩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ እንዳሉት ሀገራችን ምንም እንኳ በበርካታ ውጫዊና ውስጣዊ ጫናዎች ውስጥ ብትሆንም በእውነትና በትጋት በመስራት የሀገራችንን ብልጽግና ለማረጋገጥ በመስራት ላይ እንገኛለን ብለዋል፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም መንግስት የተቋማችንን የመፈጸምና የማስፈጸም አቅም ከፍ ለማድረግ ወደ ባለስልጣን መስሪያ ቤት ያሳደገው በመሆኑ የኢትዮጵያን የሲቪል ማህበረሰብ ዘርፍ እንዲጎለብት ለማስቻልና የጀመራቸውን ስራዎች በበለጠ ውጤታማ ለማድረግ ዘርፉን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ በራስ አቅምና በአጋር አካላት ድጋፍ ጥናት ማድረጉን አንስተዋል፡፡



ይህ አገራዊ የCSO mapping ጥናት በዘርፉ በጥናት ላይ የተመሰረተ መረጃ ለማግኘት እንዲቻልና፣ ተቋማችንም ሆነ በአጠቃላይ የክልል መንግስታት ለሚያከናውኗቸው ስራዎች መነሻና ማጣቀሻ ሆኖ ያገለግላል በማለት ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች፣ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ እንዲሁም አጋር ድርጅቶች መንግስት በፈጠረው ምቹ ሁኔታ በመጠቀም በአገር ልማትና ዴሞክራሲ የበኩላቸውን ሃላፊነት እንዲወጡ፤ በዚህ ጥናት የቀረቡ ማጣቀሻዎችን በመጠቀም ለዘርፉ ድጋፍ እንዲያደርጉ የሚያስችላቸው ይሆናል ሲሉ በመክፈቻ ንግግራቸው ገልጸዋል፡፡ የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበራት ይዘት ጥናት 2013/14 (Ethiopian civil society mapping 2021) የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ ከአውሮፓ ህብረት የሲቪል ሶሳይቲ ፈንድና (CSF III) ከሲቪል ሶሳይቲ ሰፖርት ፕሮግራም (CSSP II) ድጋፍ በዓለም ዓቀፍ አማካሪዎችና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ያዘጋጀው የዳሰሳ ጥናት ሪፖርት ነው፡፡

በዚህ ጥናት ላይ ሁሉም ክልሎች የተሳተፉ ሲሆን አጠቃላይ የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ዘርፍ ዳሰሳ ጥናት የመጨረሻ ግብዓት የሚሰበሰብበት እንደሆነም ታውቋል፡፡ በጥናቱ ላይ የተለያዩ ዓለም ዓቀፍ ድርጅቶች፣ አማካሪዎች እንዲሁም የኤጀንሲው ባለሙያዎች እና የክልል የስራ ሃላፊዎች ተሳትፎ ያደረጉበት እንደሆነም የጥናት ቡድኑ መሪ አቶ ደበበ ኃይለጊዮርጊስ የጥናቱን ይዘት ባብራሩበት ወቅት ገልጸዋል፡፡ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ በእለቱ ከኢ.ዜ.አ ጋር በነበራቸው ቆይታ መንግስት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን በሚመለከት ባደረገው የአዋጅ ማሻሻያ ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን አንስተው የተቋቋሙለትን ዓላማ ከግብ ማድረስ የሚገባቸው መሆኑን ጠቅሰው ከዚህ ውጪ ግን የሀገርን ሉዓላዊነት አደጋ ላይ በሚጥል ተግባር ላይ በሚሳተፉና ከዓላማቸው ውጪ በሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች ላይ እርምጃዎችን ሲወስድ ቆይቷል፤ ወደፊትም አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል ብለዋል፡፡

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ካሁን በፊት ሲያደርጋቸው የነበሩ ማጣሪያዎችን ያጠናቀቀ መሆኑን የጠቀሱት ዋና ዳይሬክተሩ በቅርቡ ምርመራውን ይፋ እንደሚያደርግና ይህን መሰረት አድርጎም እርምጃዎችን የሚወስድ እንደሆነ ለኢ.ዜ.አ ተናግረዋል፡፡



ልጆች ላይ የዘሩት ለትውልድ ይተርፋል!!





ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ በበኩላቸው ድርጅቱ ብዙ ለሃር የሚጠቅም ፕሮጀክትን ይዞ እየሰራ የሚገኝ መሆኑን በመግለጽ ሃገራችንን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ በጎ ማድረግ አስፈላጊ ነው ፡፡ በጎ ስራ የሰሩ እና እየሰሩ ያሉ ሰዎች እራሳቸውን አሳልፈው የሰጡ በመሆናቸው ስራቸው ለአዲሱ ትውልድ ሊነገር ይገባል ይህንን ደግሞ ለማድረግ መንግስትም ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል፡፡



የከበረ ዝግባ ቀንበጥ የበጎ አድራጎትና የልማት ድርጅት የስራ እንቅስቃሴ በባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ተጎበኘ፡፡
የከበረ ዝግባ ቀንበጥ የበጎ አድራጎትና የልማት ድርጅት ከአዲስ አበባ 70 ኪሎሜትር ላይ በምትገኘው ውጫሌ ወረዳ ይገኛል፡፡ የመስክ ምልከታውን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተርን ጨምሮ የሆፕ ቸስት ቺልድረንስ (children’s hope chest) የስራ ሃላፊዎችና ከተለያዩ የሲቪል ማህበረሰብ ደርጅቶች ከመጡ የስራ ሃላፊዎች ጋር በመሆን ድርጅቱን ጎብኝተዋል ፡፡ በጉብኝቱ ወቅት ስለድርጅት አመሰራረት ገለፃ ያደረጉልን የድርጅቱ መስራችና ስራ አስኪያጅ ወ/ሪት ስምረት መንገሻ እንዳሉት ድርጅቱ ሲቋቋም ዓላማ አድርጎ የተነሳው ወላጅ አልባ የሆኑትና ለጥቃት የተጋለጡ ህፃናት የትምህርት፣ የምግብ፣ የጤና አገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ ቤተሰባቸውን፣ ህብረተሰባቸውን እንዲሁም ሀገራቸውን የሚወዱና በራሳቸው ሚተማመኑ፣ ሃላፊነት የሚሰማቸው፣ ከጥገኝነት ነፃ ሆነው እንዲያድጉ ለማድረግ ተብሎ የተቋቋመ ድርጅት መሆኑን ገልፀዋል፡፡



ስራ አስኪያጇ አክለውም ድርጅቱ በአሁን ጊዜ ከተለያዩ ቦታዎች የመጡ ከ50 በላይ ህፃናትን በስሩ አቅፎ በጤናና በትምህርት ድጋፍ እያደረገላቸው እንደሆነ በመግለፅ በተጨማሪም ከ120 በላይ የሆኑ ህፃናትን ከቤተሰባቸው ጋር ሆነው በትምህርትና በጤና አገልግሎት ድጋፍ እያደረጉላቸው እንዳለም ተናግረዋል፡፡ አያይዘውም የአካባቢውን ህብረተሰብ ከልማቱ ተጠቃሚ ለማድረግ ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር በጥምረት በመስራት ቺልድረንስ ሆፕ ቸስት (children’s hope chest) ከተባለው የውጭ የበጎ አድራጎት ድርጅት በተገኘ ፈንድ የንፁህ መጠጥ ውሃ ጉድጓድ በማስቆፈር ተጠቃሚ መሆን እንደቻሉ ያስረዳሉ፡፡

የበጎ አድራጎት ድርጅቱ ራሱን ለመቻል በገቢማስገኛ ስራ ላይ ከቺልድረንስ ሆፕ ቸስት (children’s hope chest) በተገኘ ድጋፍ በሰፊው በመሳተፍ ላይ መሆኑን የሚናገሩት ወ/ሮ ስምረት በንብ ማነብ፣የወተት ላሞችን በማርባት ፣በጎችን በማርባት፣የእንቁላል ዶሮችንና የዘይት መጭመቂያ ስራላይ በመሰማራት እንዲሁም የተለያዩ የጓሮ አትክልቶችን በማምረት ገቢውን ማሳደግ እንደቻሉና በቀጣይም ይህንኑ በማጠናከር በርካታ ስራዎችን ለመስራት ድርጅቱ ዕቅድ እንዳለው ተናግረዋል ፡፡

በጉብኝቱ ላይ የተገኙት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ እንደተናገሩት በተቋሙ እየተሰሩ ያሉት ስራዎችን በማድነቅ እየሰራችሁ ያለው ስራ በተለይም ድርጅቱ ቀጣይነት እንዲኖረው ከጠባቂነት መንፈስ ለመውጣት በገቢ ማስገኛ ስራ ላይ እየሰራችሁ ያለው ተግባራት የሚደነቅና የሚበረታታ ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡ አያይዘውም ለጋሽ ድርጅቶችም ቢሆኑ እንዴት አድርገን ከችግር ውስጥ መውጣት እንደምንችል መንገድ እንዲያሳዩን እንጂ እስከ ህይወት ዘመናችን እንዲረዱን መፍቀድ አይኖርብንም ሲሉ ገልፀዋል፡፡ ድርጅቱ ራሱን ለመቻልና ቀጣይነት እንዲኖረው ለማድረግ እየሰራ ያለው ስራ ትልቅ ማሳያ መሆኑን የገለፁት ዋና ዳይሬክተሩ ባለስልጣኑ አስፈላጊውን ድጋፍ ለድርጅቱ እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡ በመጨረሻም የአገራችን እድገት የሚረጋገጠው መንግስት፣ የግሉ ሴክተር እና የሲቪል ማህበረሰቡ ትስስር ሲፈጥር ነው፡፡ ይህንን ካደርግንና ሁላችንም የሚጠበቅብንን ሃላፊነት ከተወጣን የህብረተሰባችንን የላቀ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የማንችልበት እንዲሁም ከልመናም የማንላቀቅበት ምክንያት አይኖርም ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡



የሲቪል ማህበረሰብ ድጅቶች ኤጀንሲ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች አውት ኦፍ ዘ አሽ (out of the ash) የተባለ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት የስራ እንቅስቃሴን ጎበኙ፡፡
ድርጅቱ ‹‹የድህነትን ዑደት በትምህርት እንስበር›› የሚል መሪ ቃል አንግቦ በተለምዶ ቆሼ ሰፈር እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የሚገኙ ህጻናትንና ወጣቶችን የትምህርት፣ የጤና፣ የምግብና የአልባሳት፣ የመጠለያ እንዲሁም ልዩ ልዩ ስልጠናዎችን በመስጠት እየደገፈ የሚገኝ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ነው፡፡ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ የድርጅቱን የስራ እንቅስቃሴ ከተመለከቱ በኋላ በሰጡት አስተያየት ድርጅቱ ትምህርትን አንዱ የድህነት መቀነሻ መሳሪያ አድርጎ መጠቀሙ ባለትልቅ ራዕይ መሆኑን የሚያመላክት ነውና ለወደፊቱም አጠናክራችሁ መቀጠል ይኖርባችኋል ሲሉ ለድርጅቱ የስራ ኃላፊዎች መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡





በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር የሆኑትን ክቡር ሬሚ ማሬሾ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ በቢሮአቸው አግኝተው አነጋግረዋቸዋል፡፡
በውይይቱ በሃገራችን የመጣውን ለውጥ ተከትሎ በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ዘርፍ የመጡ ለውጦች፣አዲሱ አዋጅ ከተለወጠ በኋላ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ከመንግስት ጋር አብሮ ከመስራት አንጻር ያላቸው ሚና ፣ ከAFD የተባለ ፈረንሳይን መሰረት ያደረገ ድርጅት ከኤጀንሲው ጋር የ10 ዓመት ስትራቴጂክ እቅድን ከማገዝ አንጻር የተጀመሩ ስራዎች በተመለከተ እንዲሁም በቀጣይም የኤጀንሲውን አቅም ከመገንባት እና የልምድ ልውውጥ ከማድረግ አንጻር አብሮ ስለመስራት ተወያይተዋል፡፡



"በአዲስ ምዕራፍ በተሟላ ሉዓላዊነት ለሰንደቅ ዓላማችን ከፍታ!"
“በአዲስ ምዕራፍ በተሟላ ሉዓላዊነት ለሰንደቅ ዓላማችን ከፍታ!” በሚል መሪ ቃል 14ኛው የብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን በኤጀንሲው ተከብሯል፡፡
የዋና ዳይሬክተር አማካሪ አቶ ተስፋዬ ሽፈራው በንግግራቸው እንደገለጹት የዘንድሮው የሰንደቅ ዓላማ ቀን በዓል የሚከበረው አዲስ ፓርላማ እና የመንግስት ምስረታ በተካሄደበት ማግስት እና በኢትዮጵያ እውነተኛ ዴሞክራሲ ለመገንባትና ብልፅግናን ለማምጣት አዲስ ምእራፍ በጀመርንበት ወቅት በመሆኑ ልዩ ያደርገዋል በማለት እኛም እንደ ዜጋ በአዲስ ራዕይ እና በአዲስ ተስፋ ሃገራችንን ማገልገል አለብን ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡



የሲ.ማ.ድ.ኤ. የኮሚዩኒኬሽንና ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት
ኤጀንሲው ከ45 በላይ አገልግሎቶችን በኦን ላይን ለመስጠት ዝግጅቱን ማጠናቀቁ ተገለፀ ፡፡
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ የአሰራር ዘይቤውን በመቀየር ቀደም ሲል በወረቀት ይሰጥ የነበረውን የአገልግሎት አሰጣጥ በቴክኖሎጂ በመደገፍ ከአርባ አምስት በላይ በተቋሙ የሚሰጡ አገልግሎቶችን በኢ-ሰርቪስ አገልግሎት አሰጣጥ ለመስጠት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ገልፀ፡፡
በተቋሙ ውስጥ አገልግሎቱን ለመጀመር ለተቋሙ ባለሙያዎችና ሃላፊዎች በአገልግሎት አሰጣጡና በአጠቃቀሙ ዙርያ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የተለያዩ ስልጠናዎችን በመስጠት የተቋሙን ባለሙያዎች ሲያዘጋጅ እንደቆየ ይታወሳል፡፡ ይህን መነሻ በማድረግ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ ለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ስለ አገልግሎቱ አጠቃቀምና በአገልግሎቱ ስለተካተቱ የተቋሙ አገልግሎቶች በጁፒተር ኢንተርናሽናል ሆቴል ገለጻ አድርገጓል፡፡

በመድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ ባስተላለፉት መልዕክት ላለፉት ሶስት ዓመታት በሃገራችን በነበረው የለውጥ ሂደት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በኢትዮጵያ ሁለተናዊ ብልፅግና ላይ የራሳቸውን ሚና መጫወት እንዲችሉ ህግና ተቋማዊ ሪፎርሞች መካሄዳቸውን በማስታወስ በቅርቡም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስተር የመንግስት አገልግሎቶች በዲጂታል መንገድ እንዲሰጡ ለማድረግ በጀመረው እንቅስቃሴ መሰረት ኤጀንሲያችን የኢ-ሰርቪስ አገልግሎትን በማስጀመር ተቋማችን ወደ ተሻለ የአገለግሎት አሰጣጥ እንዲሸጋገር በማድረግ የሚያግዝ መሆኑን አንስተዋል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስተር የአይ ሲቲ ልማት ዘርፍ ዳይሬክቶሬት ጀኔራል ኢንጂነር አብዮት ሲናሞ በበኩላቸው በሃገራችን የዲጂታል ኢኮኖሚ ወደፊት እንዲራመድ ለማድረግ ባለፉት አመታት የሃገሪቱ የኢ ትራንዛክሽን አዋጅ ፀድቆ ስራ ላይ መዋሉ ይታወሳል፤ ይህም በዋናነት ቀደም ሲል በወረቀት ይሰሩ የነበሩ አገልግሎቶች በኤሌክትሮኒክስ ቢሰሩ ህጋዊነታቸውን አያጡም የሚል መሰረታዊ የህግ ማዕቀፍ ማስቀመጡን ገልጸዋል ፡፡ አያይዘውም በዚህ የህግ ማዕቀፍ መሰረት የ E_government ስራዎች ማለትም መንግስት ከዜጎች፣ መንግስት ከንግዱ ማህበረሰብ ወይም የመንግስት ተቋማት ከመንግስት ተቋማት ጋር የሚያደርጓቸው ግንኙነቶች በሂደት ወደ ኤሌክትሮኒክስ መጠቀሚያ ዘዴ እንዲቀየሩ የሚደረግ ይሆናል ብለዋል ፡፡



በአገልግሎቱ ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን ቴክኖሎጂው ጊዜንና ጉልበትን በመቆጠብ ያላስፈላጊ እንግልትን የሚያስቀር መሆኑን ተሳታፊዎቹ ገልጸዋል፡፡ የመንግስት ተቋማት አገልግሎታቸውን ዲጂታል በማድረግ የኢ ሰርቪስ አገልግሎት እንዲሰጡ ከተመረጡ 20 የመንግስት ተቋማት ውስጥ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ አንዱ ሲሆን በተቋሙ የሚሰጡ አርባ አምስት አገልግሎቶች በኢ ሰርቪስ የሚሰጡ ይሆናል፡፡ በአገልግሎቱ ላይ የሚነሱ አስተያየቶች ካሉም ለኤጀንሲው ማሳወቅ የሚቻል መሆኑም ታውቋል፡፡








