የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ሰራተኞች በኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የበቾ ወረዳ ዘማች ቤተሰቦችን ሰብል ሰበሰቡ፡፡ በወረዳው በሶዮማ ቀበሌ በመገኘት የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል በመሰብሰብ፤ አለኝታነታቸውን ያሳዩ ሲሆን በቀጣይም እገዛ እንደሚቀጥል የበጎ አድራትና ፈንድ አስተዳድር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አሉላ ሚሊየን ገልጸዋል ። የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ “አሸባሪው ህወሓት በኢትዮጵያ ላይ የደቀነውን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ ሁሉም በሚችለው አቅም መረባረብ አለበት” ብለዋል፡፡
የአገር መከላከያ ሰራዊት እና ሌሎች የፀጥታ አካላት የኢትዮጵያን አንድነት ለማረጋገጥ የህይወት መስዋዕትነት እየከፈሉ እንደሆነ ጠቅሰው፤ “እኛም በቻልነው ሁሉ ከጎናቸው መሆን አለብን” ሲሉ ተናግረዋል፡፡ “ከሰራዊቱ ጎን ከመሰለፍ ባለፈ ደጀን በመሆን የዘማች ቤተሰቦችን መደገፍና ማገዝ ይኖርብናል” ብለዋል። የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችም ተፈናቃዮችን በመደገፍ እና መልሶ በማቋቋም ረገድ በስፋት ሊሰሩ እንደሚገባ አመልክተዋል፡፡ በፕሮግራሙ ላይ የተሳተፉ ሰራተኞችም የአገሪቱን ህልውና ለማስቀጠል የቻሉትን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የመደራጀት መብት፤ ሰብዓዊነት፤ የህብረተሰቡ የላቀ ተጠቃሚነት!!!
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን!!!
Authority for civil society organizations (ACSO)