ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ከፕላን ኢንተርናሽናል ጋር በመተባበር በፋይናንስ አሰራር ስርዓት፣ በግዢ አፈፃፀም እና ንብረት አስተዳደር ዙሪያ ለተቋሙ ሰራተኞች ስልጠና ሰጠ፡፡
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በተቋሙ ለሚገኙ የፋይናንስና የንብረት አስተዳደር ባለሙያዎች ትኩረቱን በፋይናንስ አሰራር ስርዓትና በንብረት አያያዝ ላይ ያደረገ ስልጠና ከፕላን ኢንተርናሽናል ጋር በመተባበር ከገንዘብ ሚንስቴር በመጡ ባለሙያዎች ስልጠና ሰጥቷል፡፡ በስልጠናው ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የዋና ዳይሬክተር አማካሪ አቶ ተስፋዬ ሽፈራው ወጪ ቆጣቢ የኃብት አጠቃቀምን በማሳደግ ዓላማችንን ማሳካት ይጠበቅብናል ያሉ ሲሆን የሂሳብ አያያዝ ስርዓታችንን በማዘመን ስራዎቻችንን መከወን ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡አያይዘውም በእውቀት ላይ የተመሰረተ አፈጻጸምን ለማጎልበት ስልጠናው እጅግ ጠቀሜታ ያለው በመሆኑ ስልጠናውን እንድንሰጥ ላገዙን ሁሉ ምስጋናችን ከፍ ያለ ነው ብለዋል፡፡ በፋይናንስ የሪፖርት ስርዓታችን ላይ ማሻሻል የሚገቡን በርካታ ስራዎች ያሉን በመሆኑ ተሳታፊዎች በትጋት እንድትከታተሉ ሲሉ አሳስበዋል፡፡ ከገንዘብ ሚንስቴር በመጡት ከፍተኛ ባለሙያ አቶ መኮንን ጌታሁንና ወ/ሮ ተናኘ ጌታሁን አማካኝነት ስልጠናው ለሶስት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የቆየ ሲሆን የተቋሙ የፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ባለሙያዎች፣ የውስጥ ኦዲት ባለሙያዎችና የተቋሙ ንብረት ክፍል ባለሙያዎች የስልጠናው ተሳታፊዎች ሆነዋል፡፡ ስልጠናው በዋናነት ትኩረቱን ያደረገው የመንግስት ሂሳብ አያያዝ፣ የጥሬ ገንዘብ አስተዳደርና ቁጥጥር በእጅ ያለ ጥሬ ገንዘብ፤ በባንክ ያለ፣ ተሰብሳቢ ሂሳብ፣የወጪ አስተዳደር፣ ደመወዝና አበል ክፍያ፣ግዥ፣ ንብረት አስተዳደር፣ ስጋት እና የስጋት አስተዳደር ፣ በሚሉ መሰል ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ነው፡፡



ከስልጠናው መጠናቀቅ በኋላ ተሳታፊዎች ሃሳባቸውን የሰጡ ሲሆን በስራ ላይ ያሉብንን ከፍተቶች በጥልቀት ያየንበትና ሁላችንንም ክፍተታችን የቱ ጋር እንደሆነ የገመገምንበት ስልጠና ነው ብለዋል፡፡ አያይዘውም ወደስራችን ስንመለስ በአዲስ መንፈስ ያሉብንን ክፍተቶች ሁሉ ሞልተን ለተቋማችን የበኩላችንን አበርክቶ እንወጣለን ሲሉ ሃሳባቸውን ሰጥተዋል፡፡ በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ የባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን ተቋሙ ሞዴል ተቋም ይሆን ዘንድ ፍላጎት ብቻ ሳይሆን ቁርጠኝነቱም እንዳለ ጠቁመው ለዚህም ደጋፊ የስራ ሂደቶችን እና ዋና የስራ ሂደቶችን በእኩል እይታ መመልከት ተገቢ ነው ብለዋል፡፡ ያለንን ሀብት በአግባቡ መምራትና ማስተዳደር ተገቢ በመሆኑ የውስጥ ኦዲት ጉድለታችንን እንድናርም ክፍተታችንን እንድናስተካክል ስልጠናው ትልቅ ሚና አለው፡፡ እናንተም የተቋማችን ባላደራ ሆናችሁ ልትቀጥሉ ይገባል ብለዋል፡፡

ስልጠናውን ለሰጡት ባለሞያዎችና ለስልጠናው አስተባባሪዎች እንዲሁም ለፕላን ኢንተርናሽናል ስላደረጉት አስተዋጽዖ ምስጋናቸውን አቅርበው ሰልጣኞችም ስልጠናውን ወደተግባር በመቀየር የድርሻቸውን እንደሚወጡ እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡

የኤ.ፌ.ዲሪ ፍትህ ሚኒስትርና ተጠሪ ተቋማት የበላይ አመራሮች በኦንላይን የሃብት ምዝገባ ስነስርዓት አካሄዱ ፡፡



የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን በተለያዩ ዝግጅቶች አከበረ፡፡
የባለስልጣኑ ሴቶችና ህፃናት ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት ማርች 8 የሴቶች ዓለም አቀፍ ቀንን “እኔም የእህቴ ጠባቂ ነኝ“ በሚል መሪ ቃል አመራሩና ሰራተኛው በአዳማ ከተማ በደማቅ ስነስርዓት አከበረ፡፡ በእለቱም በአለም የሴቶች ቀን እንዲከበር መነሻ የሆኑ፤ ታሪካዊ ዳራ የሚገልፅ ፅሁፍ በክፍሉ ዳይሬክተር ወ/ሪት ፀሃይ ሽፈራው የቀረበ ሲሆን በተጨማሪም በዓሉን ስናከብር በተለያዩ አካባቢዎች በተከሰተው አለመረጋጋት በሴቶችና ህፃናት ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃቶች በመከላከልና ድጋፍ በማድረግ መሆን እንዳለበትም ተናግረዋል፡፡ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ ባስተላለፉት መልዕክት የሴቶች ጥያቄ የፍትህ፣ የእኩልነት እንዲሁም ከሌሎች በልጦ የመገኘት ሳይሆን ከወንዶች እኩል መብታቸው እንዲከበር የመጠየቅ መብት መሆኑን በመጥቀስ የኤ.ፌ.ደሪ ህግ-መንግስት እንቀፅ 35 ሴቶች ህግመንግስቱ ባረጋገጠላቸው መብቶችና ጥበቃዎች ከመጠቀም አንጻር ከወንዶች እኩል መብት እንዳላቸው ያረጋግጣል ይህም የዘመናት ጥያቄያቸው መልስ ያገኘበት እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡



አያይዘውም ሴቶችን የሚጨቁኑ ወይም በአካላቸው ላይ እንዲሁም በአእምሮአቸው ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ህጎች፣ ስርዓቶችና ልምዶችን የተከለከሉ መሆኑንም ህግ መንግስታችን በግልፅ ይደነግጋል፡፡ ስለዚህ የሴቶችን እኩልነት በተገቢው መንገድ በህገ-መንግስታችን ሙሉ በሙሉ የተቀመጠ መሆኑን በማስታወስ ወንዶችም በአጋርነት የሴቶችን እኩልነት ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል ብለዋል ፡፡ ሌላው ያነሱት ዋና ዳይሬክተሩ የዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን ስናከብር በርካታ ነገሮችን እናስታውሳለን ይህም በሃገራችን በሰሜኑ ክፍል የተከሰተው ጦርነት በሴቶችና ህፃናት ላይ በርካታ መከራና ስቃይ ማድረሱን በመጥቀስ ይህንንም በማዘን ብቻ ሳይሆን ሊደግፍ የሚችል ተግባራትን በማከናወን የምንችለውን ሁሉ ማድረግ ይኖርብናል በማለት ገልጸዋል፡፡ በመጨረሻም የዘንድሮውም ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን የሚከበረው የተጎዱ ሴቶችና ህፃናት ድጋፍ በማድረግ እንዲሁም የተሻለ አፈፃፀም ያላቸውን ሴቶች ደግሞ እውቅና በመስጠት ይሆናል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋ፡፡ በፕሮግራሙ ላይ የተለያዩ ተጋባዥ እንግዶች፣ የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮችና ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ ፕሮግራሙን በመደገፍ እገዛ ላደረጉ ኮንሰር እና አዲስ ህይወት የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ምስጋናውን አቅርበዋል፡፡
"በኢትዮጵያዊነቱ የሚኮራና ለሀገሩ ኃላፊነቱን የሚወጣ ትውልድ መፍጠር የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሚና ነው"



በሰብዓዊ መብት ላይ የሚሰሩ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ውጤታማ ስራ መስራት እንደሚጠበቅባቸው ተገለጸ፡፡



Concern worldwide የተባለ የውጭ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት በአማራ ክልል በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው ነዋሪዎች ድጋፍ አደረገ፡፡



ባለስልጣኑ በፀደቁ አራት መመሪያዎች ላይ የአሰልጣኞች ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡




ዘርፉ ወጥ የሆነ አሰራር እንዲከተል እነዚህ ማንዋሎችና መመሪያዎች ትልቅ እገዛ ያደርጋሉ ሲሉ የገለፁት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ይህ መድረክ የተዘጋጀበት ትልቁ ምክንያትም መመሪያዎችን የሚፈፅሙት ክልሎች፣ በክልሎች የሚንቀሳቀሱ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እንዲሁም የባለሥልጣኑ ባለሙያዎች በመሆናቸውና መመሪያዎች መውጣት ብቻ ሳይሆን ተግባራዊ እንዲሆኑ ለማስቻል ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ በስልጠናው ማጠናቀቂያ ላይ እንደተናገሩት ይህ የአሰልጣኞች ስልጠና እየተሰጠ ያለው በመመሪያዎቹ ላይ የጋራ መረዳት እንዲኖርና በምትሄዱበትም ክልል መመሪያው በትክክል ተግባራዊ እንዲሆን የበኩላችሁን እንድትወጡ በማለም ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡
የአሰልጣኞች ስልጠናው የሚሰጠው የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የአስተዳደር ወጪ አፈፃፀም መመሪያ፣ የሲቪል ማኅበረሰብ ፈንድ አስተዳደር መመሪያ፣ የሙያ ማኅበራት ድጋፍና አስተዳደር መመሪያ እንዲሁም የሂሳብ አጣሪዎች፤ የድርጅት ንብረት ግዢ፣ ሽያጭና አወጋገድ መመሪያዎች ላይ የሚሰጥ ሲሆን በቀጣይ በሁሉም ክልልሎች ስልጠናው ተሰጥቱዋል፡፡
በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ላይ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡



አድዋ

የአድዋ ድል የሁሉም ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የጋራ ድል ከመሆኑም በላይ ጊዜ የማይሽረዉ በደምና በአጥንት የተፃፈ የጋራ ታሪካችን ጭምር ነዉ፡፡ ዛሬ ላይ ሆነን ስንመለከት የአድዋ ድል ትሩፋት ከጦር ሜዳ አሸናፊነት በላይ ነዉ፡፡ አገራዊ እንድነታችንና ሉዓላዊነታችን የተረጋገጠበት ታሪካዊ ድል ነው፤አድዋ፡፡ የአሸናፊነታችን ምሥጢር መተባበራችንና አንድነታችን ስለመሆኑ አባቶቻችን በተግባር ያስተማሩበት የተግባር ልምምድም ነበር፡፡ መላዉ ኢትዮጵያዊያን ያለ አንዳች ልዩነት በአንድነት ለአገራቸዉ ሉዓላዊነትና ለሕዝቦቿ ክብር ተሰልፈዉ በጋራ የተዋደቁና የጋራ ድል ያስመዘበገቡ በመሆናቸዉ የአድዋ ድል የጋራ ታሪካችን ነዉ፡፡ ከሁሉም በላይ አድዋ የብሔራዊ ኩራታችን ምንጭም ነዉ፡፡ ከኢትዮጵያም አልፎ የመላ ጥቁር ሕዝቦች ኩራት ነዉ፡፡ የአድዋ ድል የአፍሪካዊያን የነፃነት ፋና ወጊ በመሆን የነፃነት ትግል ማቀጣጠያ ከመሆኑም በላይ ኢትዮጵያ የፓን አፍሪካኒዝም ተምሳሌት ተደርጋ አንድትቆጠር አድርጓታል፡፡
(ከየመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ከተሰጠ መግለጫ የተወሰደ)









