ድጋፉ በአማራ ብ/ክ/መንግስት ደቡብ ወሎ ዞን ለጋንቦ ወረዳ አቅስታ ከተማ በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው 1080 አባወራዎች እና የአከባቢው ነዋሪዎች ነው፡፡ ድርጅቱ ጉዳት ለደረሰባቸው የማህበረሰብ ክፍሎች የቤት ውስጥ ቁሳቁስ እና አልባሳት ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን ከዚህ ቀደም በአማራ ክልል ብቻ ከ46 ሚሊየን ብር በላይ በዓይነትና 10 ሚሊየን ብር በላይ በካሽ በጦርነቱ ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አድርገዋል፡፡ በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ ድርጅቱ በሃገራችን በጦርነቱ ለተጎዱ የማህበረሰብ ክፍሎች እያደረገ ያለውን ድጋፍ በማበረታታት በጦርነቱም ችግር የደረሰባቸውን የማህበረሰብ ክፍሎች እንደ ሀገር ያጋጠመንን ፈተና ተጋግዘንና ተባብብረን እንደምንሻገረ አምናለሁ በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በተያያዘ ዜናም ዋና ዳይሬክተሩ ድርጅቱ በጭሮ 1ኛ ደረጃ ትምህርቤት በተለያዪ ምክንያቶች ትምህርታቸውን ያቋረጡ ሴት ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ እያደረገ ያለውን ድጋፍ ተመልክተዋል፡፡ ድርጅቱ ከዚህ ረገድ ”ልጃገረዶችን ማስተማር ምርጫ ሳይሆን መብት ነው’ ‘Leave no girl behind’ በሚሉ መሪ ቃሎች በርካታ ሴት ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው ተመልሰው ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ የተለያዩ የትምህርት ቁሳቁሶችና የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ተገልጷል፡፡ ፕሮጀክቱ በወረዳው በሚገኙ 32 ቀበሌዎች ተግባራዊ በመደረግ ላይ የሚገኝ ሲሆን በዚህም ከ 3000 በላይ ሴት ተማሪዎች ተጠቃሚ መሆናቸውን ተብራርቷል፡፡ ከጉብኝቱ በኋላ ዋና ዳይሬክተሩ ባስተላለፉት መልዕክት ሴትን ልጅ ማስተማር ሀገርን ማስተማር በመሆኑ ድርጅቱ የጀመረው ሥራ የሚበረታታና ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት፣ ሴቶች ዕድሉን ካገኙ የተሻሉ መሪዎች መሆናቸውን፣ በሀገር ልማት ውስጥ የሴቶች ሚና የጎላ መሆኑንና ከለውጥ በኋላ ሴቶችን ወደ አመራርነት የማምጣት ሥራ መሠራቱን፣ይህም ተጠናክሮ የሚቀጥል በመሆኑ አሁን በትምህርት ገበታ ላይ ያሉ ሴቶች የተሻለ ደረጃ ለመድረስ ትምህርታቸውን በትጋት መቀጠል አለባቸው ሲሉ ተናግረዋል፡፡