በተቋሙ አዘጋጅነት በሁሉም ክልሎች በማህበራዊ ተጠያቂነት ዙሪያ የሚሰጠው ስልጠና ተጀመረ፡፡



የመገናኛ ብዙኃን ኃላፊዎችና ባለሙያዎች የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን የስራ እንቅስቃሴ ጎበኙ
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ያዘጋጀው የሚድያ ተቋማት ኃላፊዎችና ባለሙያዎች የተሳተፉበት የመስክ ጉብኝት ተካሂዷል፡፡ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱን ተግባርና ሃላፊነት ለሚዲያ ተቋማት ግንዛቤ ማስያዝ፣የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን እንቅስቃሴ በአካል ማሳየት እና የሚዲያ ሽፋን እንዲያገኙ ብሎም ማህበረሰቡ ስለድርጅቶቹ ግንዛቤ እንዲይዝና በዚህ ሂደት የማህበረሰቡን የላቀ ተጠቃሚነት ማረጋገጥን ዓላማ አድርጎ የተዘጋጀው ይህ የመስክ ምልከታ በተመረጡ አምስት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ፕሮጀክቶች ላይ የተደረገ ነው፡፡ ከተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን የተሳባሰቡት ሃላፊዎቹ በትምህርት፣ በተፈጥሮ ሀብትና አካባቢ ጥበቃ፣ በህጻናት እንክብካቤና ድጋፍ እንዲሁም በውኃና ውኃ አቅርቦት ላይ የሚሰሩ ድርጅቶችን ፕሮጀክቶች ፕሮጀክቶቹ በሚከናወኑበት አካባቢ በመገኘት ተመልክተዋል፡፡ በሞጆ ከተማ በትምህርትና ስልጠና እንዲሁም በህጻናት እንክብካቤና ድጋፍ ላይ የሚሰራው ራፊቅ ፋውንዴሽንና በተፈጥሮ ኃብት ጥበቃና በአካባቢ ጥበቃ ላይ የሚሰራውን ሴዳ (SEDA) የተባሉ ድርጅቶችን ፕሮጀክቶችን በማየት የጀመረው የመስክ ምልከታ በዝዋይ የክርስቲያን ኤድ ድርጅትን የውኃ ፕሮጀክቶችን እንዲሁም በወንዶ ገነት የሚገኘውን የመና ህጻናትና የቤተሰብ መርጃ እና የህብረተሰብ ልማት ድርጅትን የተመለከተ ሲሆን የካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የልማት ድርጅት በምዕራብ አርሲ ሻሸመኔ፣ በምስራቅ ሸዋ መቂና የመቂ ዙሪያ የሚገኙ ማህበረሰብ አቀፍ የልማት ስራዎችን ያካተተ ነው፡፡



የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ዘርፍ ባለፉት ሶስት ዓመታት ከፍተኛ የሪፎርም ስራ የተሰራበት ዘርፍ መሆኑን ለጉብኝት ተሳታፊዎች ገልጸው የሚድያ ተቋማት ለዘርፉ ልዩ ትኩረት በመስጠት ለሀገር እያበረከተ ያለውን በጎ አስተዋጽዖ ለህዝብ እንዲያደርስና ድርጅቶችም የሚሰሩትን ስራ የሚድያ ሽፋን እንዲያገኙ ትልቅ አስተዋጽዖ አለው ሲሉ ተናግረዋል፡፡ በተቋሙ ከ4000 በላይ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ተመዝገበው እንደሚገኙ የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ ከ2011 ጀምሮ ከ2000 በላይ አዲስ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች መመዝገባቸውን አንስተው ባለስልጣኑ ድርጅቶችን ከመመዝገብ ባለፈ በትክክል መሬት ላይ ምን እየሰሩ ነው የሚለውን ሚዲያዎችና ማኅበረሰቡ ማወቅ ይኖርበታል ብለዋል፡፡ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በተለያዩ ዘርፎች ተሰማርተው የህብረተሰቡን የላቀ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሰሩ መሆኑን ለማሳየት የመስክ ጉብኝቱ በተቻለ መጠን አካታች እንዲሆን ጥረት አድርገናል ያሉት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የኮሚዩኒኬሽንና ቴክኖሎጂ ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት በቀጣይም በተለያየ አካባቢዎች በመዘዋወር የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን የስራ እንቅስቃሴ ለሚዲያዎችና ለህዝብ የማስተዋወቅ ስራዎችን አጠንክረን እንቀጥላለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡



የጉብኝቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን እንቅስቃሴ እንዲመለከቱ በማድረጉ መደሰታቸውን ገልጸው ከሚድያ ተቋማት ጋር ያለውን ግንኙነት በማጠንከር ዘርፉን በሚገባ ማስተዋወቅና እንደዚህ ዓይነት የመስክ ምልከታዎችንም በማድረግ በሁሉም አካባቢ የሚሰሩ ድርጅቶችን ሚዲያዎች እንዲያውቋቸውና እንዲያግዟቸው ብታደርጉ የሚል አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ ባለስልጣኑ በሚሰራቸው የኮሚዩኒኬሽን ስራዎች ሁሉ አብሮ ለመስራትና የዘርፉን አበርክቶ ለህዝብ ለማድረስ የበኩላቸውን እንደሚወጡ የገለጹት የጉብኝቱ ተሳታፊዎች የዘርፉን አበርክቶ ለማህበረሰቡ ለማስተዋወቅ ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጋር በጋራ እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡ ከጉብኝት መርኃ ግብሩ በተጨማሪ በተሳታፊዎች የተለያዩ ችግኞችን የመትከል መርኃ ግብር ተካሂዷል፡፡ ልዩ ልዩ የትምህርት፣ የህጻናት ድጋፍና እንክብካቤ፣ የውኃና የውኃ መሰረተ ልማት፣ ተፈጥሮ ኃብትና የአካባቢ ጥበቃ ላይ የተሰሩ ፕሮጀክቶች የታዩበት የመስክ ምልከታው ለሶስት ቀናት የተካሄደ ሲሆን በቀጣዩ በጀት ዓመት ተጠናክሮ የሚቀጥል እንደሚሆን ተጠቁሟል፡፡
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከፍተኛ አመራርና ባለሙያዎች በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማና በተለያዩ የክልሉ ወረዳዎች የሚገኘውን The Pharos Foundation የመስክ ምልከታ ተደረገ፡፡



.
የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለማረም ኢንተር ሚኒስትሪያ ታስክ ፎረስ (inter-ministerial task force) የወሰዳቸውን ርምጃዎች አስመልክቶ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከፍትህ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በመንግስት የተቋቋመው ኢንተር ሚኒስትሪያል ታስክ ፎርስ (inter-ministerial task force) እየወሰዳቸው ስላላቸው ርምጃዎች ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር እየተወያየ ይገኛል፡፡ የውይይቱ ዓላማ በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል በነበረው ጦርነት ተፈጸሙ የተባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለማረም መንግስተ የወሰዳቸውን ርምጃዎች ለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ለማሳወቅ ነው፡፡ በውይይቱ መክፈቻ ላይ የተገኙት የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ መንግስት ከሰብዓዊ መብት ጋር የተያያዙ ጥብቅ ርምጃዎችን ወስዷል ያሉ ሲሆን እነዚህ እርምጃዎች ምን ያህል አጥጋቢ ናቸው በተለይ ከሰብዓዊ መብት ጥሰት ጋር በተያያዘ ለወሰዳጀው አዎንታዊ ርምጃዎች የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምን አይነት እይታ አላቸው የሚለውን ለማወቅና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ዘርፍ በጉዳዩ ላይ ሀሳቡን መግለጽ እንዲችል ተከታታይ መድረኮች እየተዘጋጁ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡




የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በርካታ ኃላፊነቶች አሉበት ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ በተለይም ማህበረሰቡን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከሚደርስበት ጥቃት መከላከልና መጠበቅ እንዲሁም ጥፋት አድራሾችን ለህግ በማቅረብ ሂደት ውስጥ ትልቅ ኃላፊነት አለባቸው ብለዋል፡፡ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በሰሜኑ ጦርነት ወቅት በርካታ ድጋፎችን ማድረጋቸውን አንስተው ነገር ግን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ችግር ከመከሰቱ በፊት የነበራቸው እንቅስቃሴ ደካማ እንደነበር አውስተዋል፡: አያይዘውም አቅም ያለው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እየተፈጠሩ መሆኑን ጠቁመው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ድምጽ በሁሉም ዘርፍ መሰማት አለበት ያሉ ሲሆን ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ለዚህ መሳካት ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡ የኢንተር ሚኒስትሪያል ታስክ ፎርስ (inter ministrial task force) ኃላፊ ዶ/ር ታደሰ በበኩላቸው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እንደማንነኛውም የሚመለከተው አካል መንግስት የሚወስዳቸውን ርምጃዎች የማወቅ፣ የመረዳትና የራሱን አበርክቶ የማድረግ ኃላፊነት እንዳለበት በመረዳት መድረኩ እንደተዘጋጀ ጠቁመዋል፡፡
የውይይት መድረኩን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ እና የኢንተር ሚኒስትሪያል ታስክ ፎርስ ኃላፊው ዶ/ር ታደሰ መርተውታል፡፡
በበጎ ፈቃድ ይዘት፣ በማህበራዊ በጎነትና በማህበራዊ ተጠያቂነት ዙሪያ ለተቋሙ ሰራተኞች ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡




አዋጅ ቁጥር 1113/2011 መሰረት አድርገው በቀረቡ ሰባት ረቂቅ መመሪያዎች ላይ ከተለያዩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ህብረቶች ጋር ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡






የሲቪል ማኀበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን MSI Ethiopia reproductive choices ጋር በመተባበር ከዚህ ቀደም ስልጠናውን ላልወሰዱ ሰራተኞች በስነ-ተዋልዶ ጤናና ቤተሰብ ዕቅድ ዙርያ ስልጠና ተሰጠ፡፡



በእውቀት ላይ የተመሰረተ የሃብት አስተዳደር እና ውሳኔ ሰጪነት ያስፈልጋል፡፡ የተቋሙ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ ከተናገሩት የተወሰደ ነው፡፡



የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የእናቶች ቀንን አስቦ ዋለ፡፡



ዋን ቻይልድ ኢንተርናሽናል (one child international) የተባለ ድርጅት የመሪዎች ጉባዔ በኢትዮጵያ አካሄደ ፡፡









