ዋን ቻይልድ ኢንተርናሽናል (one child international) የውጭ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ሲሆን በተለያዩ ሃገራት የሚሰራ እና በኢትዮጵያም እ.ኤ.አ በ2014 ተመዝግቦ በተለያዩ ክልሎች ከ5000 በላይ ህፃናትን እየረዳ ያለ ድርጅት ነው፡፡ በመድረኩም የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ በንግግራቸው እንደገለጹት ይህ የመሪዎች ጉባዔ አፍሪካን እና መካከለኛውን ምስራቅ አንድ ላይ ያገናኘ፣ አጋርነትን ለማጠናከርና በሁለንተናዊ የልማት ፕሮጀክቶቻችን የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት ያለመ ነው ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ ሲሉ ተናግረዋል፡፡ የፕሮግራሙ ዓላማ ጠቅላላ ጉባኤውን ማካሄድና በጋራ ከሚሰሩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር የተጠናከር ግንኙነት እንዲኖረው እንዲሁም የልምድ ልውውጥ ለማድረግ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል፡፡