የተቋማችን ሰራተኞች ሞዴል በጎ ፍቃደኞች ሊሆኑ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

በጎ ፍቃደኛ የተቋሙ ሰራተኞች በጌርጌሴኖን በጎ አድራጎት ድርጅት በእውቀት እና በጉልበት የተለያዩ ስራዎችን ሰርተዋል፡፡ የባለስልጣን መስሪያቤቱ የበጎ ፍቃድ ማጎልበትና ትብብር መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ አሉላ ሚሊየን እንዳሉት በአዋጅ 1113/2011 ለተቋሙ በተሰጠው ተግባርና ሃላፊነት መሰረት በኅብረተሰብ ዘንድ የበጎ አድራጎትና በጎ ፍቃደኝነት ባሕል እንዲዳብር በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸው ከዚህ ረገድ የተቋማችን ሰራተኞች ሞዴል የበጎ ፍቃደኛ በማድረግ ለሌሎች መንግስታዊና መንግስታዊ ላልሆኑ ተቋማት ተምሳሌት ለመሆን እንሰራለን ሲሉ ገልጸዋል፡፡
አያይዘውም ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል ይህንን በጎ ተግባር በመቀላቀል በርካታ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት የሚሹ አካላትን በተለያየ መልኩ ማገዝ ይጠበቃል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ አቶ መለሰ አየለ የጌርጌሴኖን በጎ አድራጎት ድርጅት መስራች እና ስራ አስኪያጅ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ሰራተኞች ላከናወኑት ተግባር ምስጋናቸውን አቅርበው በበጎ ፍቃደኞች ከሚከናወኑ ተግባራት በተጨማሪ የአይምሮ ህሙማኑ የሚጠይቃቸው፣የሚጎበኛቸውና የሚያናግራቸው ሰው ይሻሉ ብለዋል፡፡

May be an image of 5 people and hospitalMay be an image of 7 people, hospital and text


ኢትዮጵያ በራሺያ በሚካሄደው ሲቪክ ፎረም ላይ እየተሳተፈች ትገኛለች፡፡

በመድረኩ የተቋማችን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን እና ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላን ጨምሮ ሌሎች የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ ሃላፊዎቹ በዘርፉ እየተከናወኑ ስለሚገኙ ጉዳዬች እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዬች ዙሪያ ሰነድ ለውይይት አቅርበዋል፡፡

May be an image of 14 people and text

May be an image of 4 people, dais, newsroom and text


"ከተረጅነት አስተሳሰብ መላቀቅ ለተሟላ ሀገራዊ ሉዓላዊነትና ክብር " በሚል ርዕስ ለተቋሙ ሰራተኞች ስልጠና ተሰጠ ፡፡

 

May be an image of 4 people and people studying

ስልጠናውን የሰጡት የተቋሙ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ ሲሆኑ በማብራሪያቸውም የውጭ ተረጂነት ክብረ-ነክ የሆነ ከችግር የሚያወጣን ሳይሆን በዘላቂነት በተረጂነት እንድንቀጥል የሚያደርግ መሆኑን አንስተው ለከፍተኛ ፖለቲካው፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ ቀውሶችን የሚፈጥር ስለሆነ ከዚህ መላቀቅ ብቸኛው አገራችንን ከድህነት የማላቀቅ አማራጭ በመሆኑ በዚህ ላይ በአመለካከት ደረጃ መግባባት ላይ መድረስ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
መንግስት ለዚህ የፖለቲካ ቁርጠኝት ያለው መሆኑን እና የመሪነት ሚናው ለመወጣት እንዲያስችለው መነሻ ፖሊሲና ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን ተናግረው ከዚህ አንጻር የመንግስት ሰራተኛውም ሆነ ማህረበሰቡ ድርሻውን በቁጭት መወጣት ይገባዋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
አገራችን ትላልቅ ፕሮጀክቶችን እና ጉዳዮችን ማሳካት የቻለች ከመሆኑ አኳያ ይህንንም ማሳካት የማይቻልበት ምንም ምክንያት የለም በማለት በቁርጠኝነት እንደ አገር በአንድነት ከተንቀሳቀስን የሚሳካ ጉዳይ መሆኑን አብራርተዋል፡፡ በም/ዋና ዳይሬክተሩ ለውይይት የተዘጋጀው ሰነድ ለተሳታፊዎች ቀርቦ ሰፊ ውይይት የተደረገበት ሲሆን በውይይቱ መደምደሚያም ፖሊሲው እንደሃገር በጣም አስፈላጊ እና ከድህነት እና ከተረጂነት የሚያላቅቅ በመሆኑ ሁላችንም የድርሻችንን በመወጣት ተፈጻሚ ማድረግ ይገባናል ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡

ሙስና እና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል የሚዲያ ተቋማትና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሚና የጎላ ነው - የተከበሩ አቶ አዝመራ አንደሞ

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ሰኔ 19/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከሚዲያ ተቋማት እና ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር የትውልድን ሥነምግባር ለመገንባትና ሙስናን መከላከል የሚያስችል የፎረም ምስረታ አካሄዷል። በመድረኩ የተገኙት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ም/ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ አዝመራ አንደሞ ሙስና እና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል የሚዲያ ተቋማትና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሚናቸው የጎላ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ የተከበሩ አቶ አዝመራ አንደሞ አክለውም ሀገራችን ኢኮኖሚያዊ እድገቷና ሰላሟ የተረጋጋ እንዲሆን ሌብነት ላይ ትኩረት አድርገን ልሰራ ይገባላ ብለዋል፡፡ ለዚህም የሚዲያ ተቋማትና የሲቭል ማህበረሰብ ድርጅቶች የማህበረሰብ ግንዛቤ መፍጠር ላይ በትኩረት መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል። የፌዴራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የሙስና መከላከል ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር እሸቴ አስፋው በበኩላቸው ኢትዮጵያን የአፍሪካ የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ ሙስናና እና ብልሹ አሰራር ላይ ትኩረት አድርገን መስራት አለብን ብለዋል።

May be an image of 3 people, dais and text

ሙስና እና ብልሹ አሰራርን ከምንጊዜውም በላይ መዋጋት የሚያስፈልግበት ወቅት ላይ እንገኛለን ያሉ ሲሆን፥ ለዚህም ያግዝ ዘንድ ኮሚሽኑ የመንግስት አሰራሮችን በማሻሻል ረገድ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራበት እንደሚገኝ አመላክተዋል። ይሁን እንጂ የሙስና ወንጀል እያደረሰ ካለው ጉዳት አኳያ በአንድ ተቋም ብቻ መቆጣጠርና መከላከል በቂ ሆኖ ባለመገኘቱ ከተባባሪ አካላት ጋር በቅርበት ለመስራት ፎረም ማቋቋም አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል። በዛሬው እለት የተመሰረተው ፎረምም ተቀራርቦ በጋራ ከመስራት አንፃር እንዲሁም ሙስና እና ብልሹ አሰራርን ነቅሶ ከማውጣት አኳያ ሚናው የጎላ ይሆናል ብለዋል። መገናኛ ብዙሃን ያላቸውን አቅም በመጠቀም ሙስናን በመከላከልና ወንጀለኞችን በማጋለጥ ረገድ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ የፎረሙ ሚና የጎላ መሆኑንም ገልጸዋል። ሙስና እና ብልሹ አሰራርን ለመዋጋት የጋራ ጥረትን ይጠይቃል ያሉት ምክትል ኮሚሽነሩ፥ በዚህ ሂደት ውስጥም የሲቪክ ማኅበረሰብ ድርጅቶችና የሚዲያ ተቋማት ከፍተኛ አበርክቶ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል። ፎረሙ እንደ ሀገር ሙስናን ለመከላከልና ተጠያቂነትን ለማስፈን እየተደረገ ያለውን ጥረት ከማጠናከር ባሻገር የምርመራ ጋዜጠኝነትን ውጤታማ ለማድረግ ታልሞ የተቋቋመ ስለመሆኑም ገልፀዋል። የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወ/ሮ የሺወርቅ ግርማ በበኩላቸው መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን በአዋጅ ከተሰጣቸው ተግባራት መካከል በሥነምግባር የታነጸ፣ ሙስና እና ብልሹ አሰራርን የሚፀየፍ ዜጋ ማፍራት ነው ብለዋል፡፡
ወ/ሮ የሺወርቅ ግርማ አክለውም የሚዲያ ተቋማት በሙስና መከላከል ትግል ውስጥ ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል ያሉ ሲሆን፥ ባለስልጣኑ ይህ ፎረም ሲቋቋምም ተቋማቱ በፀረ-ሙስና ትግል ሂደት ውስጥ የበኩላቸውን እንዲወጡ የማስተባበርና የማቀናጀት ተግባር ይፈፅማልም ብለዋል። በመድረኩ የተገኙት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሳምሶን ቢራቶ እንደገለፁት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከተቋቋመበት አላማ አንዱ ሙስና እና ብልሹ አሰራርን መከላከል መሆኑን ገልፀው፣ መስሪያ ቤታችንም ችግር የሚፈጥሩ ግለሰቦችን እርምጃ እየወሰደም፣ እያስወሰደም እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ የሀገራችን እድገትና ብልፅግና ጉዞ ውጤታማ ለማድረግ ሙስና እና ብልሹ አሰራር ላይ ኃላፊነት በመውሰድ በቁርጠኝነት መታግል ይኖርብናል ብለዋል፡፡ የኮሚሽኑ የሥነምግባር ግንባታና የፀረ-ሙስና ባለድርሻ አካላት ተጠባባቂ መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ከፍያለው አለሙ ለውይይት መድረኩ የሚሆን የሥነምግባር ግንባታና የፀረ-ሙስና ፎረም ፕሮቶኮል ሰነድ አቅረበው ውይይት ተደርጎበታል፡፡ በፎረሙ ማቋቋሚያ መርሀ ግብር ላይም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አዝመራ አንደሞን ጨምሮ የፌዴራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን አመራሮች፣ የሚዲያ ተቋማትና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አመራሮችና ተወካዮች ተገኝተዋል።
ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ላይ የነበራቸው ሚናና የቀጣይ እቅዶች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፡፡

 

May be an image of 8 people

በኢፌዲሪ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን እና በታላቁ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ማስተባበሪያ/ጽ/ቤት አዘጋጅነት የተካሄደ ውይይት ሲሆን በፕሮግራሙ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እና ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ተወክለው የተገኙ ሙሁራን ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ የታላቁ ህዝባዊ ግድብ ማስተባበሪያ ጽቤት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አረጋዊ በርሄ በመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለጹት የታላቁ ህዳሴ ግድብ የኢኮኖሚና የሉዐላዊነት መገለጫ በመሆኑ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በቀሪ ስራዎች ላይ ተሳትፎ ማድረግ አለባቸው በማለት በተለይም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በዚህ ረገድ ትልቅ ሃላፊነት አለባቸው ሲሉ ተናግረዋል፡፡ በታላቁ ህዳሴ ግድቡ ላይ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሚና እና በቀጣይ ሊኖራቸው ስለሚገቡ ጉዳዬች እንዲሁም ጥናትን መሰረት ያደረገ ሁለት ሰነዶች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በክረምት የበጎ ፈቃድ ንቅናቄ ዙሪያ ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር ውይይት አደረገ፡፡

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በ2016 ዓ.ም የክረምት ወራት በጋምቤላ ብሄራዊ ክልል ለሚያደርገው የበጎ ፈቃድ ንቅናቄ ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል ውይይት በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ አድርጓል፡፡ በውይይቱ ላይ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች አቶ ፋሲካው ሞላ እና አቶ መስፍን ሙሉነህ የተገኙ ሲሆን ከተለያዩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እና ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት የተውጣጡ ተወካዮችም የስብሰባው ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

May be an image of 7 people and newsroom

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በሀገር አቀፍ ደረጃ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስተባባሪነት ለሚደረገው የክረምት የበጎ ፈቃድ ንቅናቄ ከፍትህ ሚንስቴር ጋር በመተባበር በጋምቤላ ክልል በርካታ የበጎ ፈቃድ ስራዎችን ለመስራት ከወዲሁ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡ ይህንኑ የበጎ ፈቃድ ንቅናቄ ለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በማስተዋወቅ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የበጎ ፈቃድ ንቅናቄው አካል እንዲሆኑ ለማድረግ የተደረገ ውይይት ነው፡፡ በክረምቱ መርኃ ግብር የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ፣ በችግኝ ተከላ፣ በደም ልገሳ እና የአቅመ ደካሞችን ቤት በማደስ የንቅናቄው አካል እንደሚሆኑ የሚጠበቅ ሲሆን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የበጎ ፈቃድ ንቅናቄውን እንዲቀላቀሉ በማስተባበር ላይ ይገኛል፡፡ በውይይቱ ላይ ተሳታፊ የሆኑ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በንቅናቄው ላይ የበኩላቸውን አስተዋጽዖ በማድረግ በክረምቱ የበጎ ፈቃድ ንቅናቄ ላይ ተሳታፊ እንደሚሆኑ ጠቁመው ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጋርም በትብብር እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

በዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ የተመራ ልዑካን ቡድን በኦሮሚያ ልማት ማህበር የተሰሩ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል፡፡

 

May be an image of 9 people

በኦሮሚያ ልማት ማህበር በምስራቅ ሐረርጌ በቀርሳ ወረዳ የተሠሩ የተለያዩ የመሠረተ ልማት ስራዎች ተጎበኘተዋል፡፡ ድርጅቱ የመስኖና የመጠጥ ውሃ ፣የትምህት መሰረተ ልማት እና ማህበረሰቡን በኢኮኖሚ ተጠቃሚ ከማድረግ አንጻር የተሰሩ ስራዎች በድርጅቱ ዳይሬክተር አቶ ደጀኔ ኢቲቻ ገለጻ ተደርጓል፡፡ በጉብኝቱ ወቅት በልማቱ ተጠቃሚ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች፣የዞንና የወረዳ አስተዳዳሪዎች የተገኙ ሲሆን የልማት ማህበሩ እየሰራው ያለው ስራ እጅግ በጣም ጥሩ አና ማህበረሰቡን ተጠቃሚ እያደረገ ነው ማለታቸው ተገልል፡፡

4ኛው ዙር የሚዲያ አካላት የመስክ ጉብኝት በስኬት ተጠናቀቀ፡፡

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የሲቪል ማህበረሰብ ዘርፉን ሚና ለሚዲያ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች በማስተዋወቅ ዘርፉን ከሚዲያ ጋር ለማስተሳሰርና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በሚሰሩት ስራ ማህበረሰቡ ተጠቃሚ አንዲሆን ለማስቻል እንዲሁም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣንን ተግባርና ኃላፊነት ማስተዋወቅን አላማ አድርጎ በየዓመቱ የሚካሄደው የሚዲያ አካላት የመስክ ጉብኝት ተጠናቋል፡፡May be an image of 6 people
በጉብኝቱ በጤና፣ በትምህርት፣ በአቅም ግንባታ፣ በግብርና፣ በውኃ እንዲሁም በተቀናጀ የልማት ስራዎች ላይ የተሰማሩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ስራዎቻቸውን ያስጎበኙ ሲሆን ድርጀቶቹ ከተቋቋሙበት ጊዜ አንስቶ የተቋቋሙባቸውን ዓላማዎች ለማሳካት እና የህብረተሰቡን የላቀ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያደረጉትን ጥረት እና የየድርጅቶቻቸውን ታሪካዊ ዳራ ለተሳታፊዎቹ አብራርተዋል፡፡
ጉብኝቱ ለተከታታይ አምስት ቀናት የተከናወነ ሲሆን በጉብኝቱ ላይ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱን ከፍተኛ ስራ ኃላፊዎችን ጨምሮ ከተለያዩ የሚዲያ ተቋማት የተውጣጡ የሚዲያ ተቋማት ኃላፊዎች እንዲሁም ከድርጅቶቹ ጋር በትብብር የሚሰሩ የመንግስት ቢሮ ኃላፊዎች እና የዞንና የወረዳ ኃላፊዎችና ተወካዮች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
በመጀመሪያው ቀን ጉብኝት በሲዳማ ብሄራዊ ክልል በሀዋሳ ከተማ አዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል ውስጥ በጤናው ዘርፍ MSH የተባለው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ከቲቪ ጋር በተያያዘ ያከናወናቸውን ጉልህ ስራዎችን በሚመለከት ገለጻ አድርገዋል፡፡ ድርጅቱ ለቲቢ ህሙማን በቂ ክትትል እንዲያገኙና የቲቢ ስርጭት እንዲቀንስ ከፍተኛ ጥረት ከማድረጉም ባለፈ ለጤና ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በመስጠትና የህክምና ቁሳቁሶችን በማሟላት ማህበረሰቡ ተጠቃሚ እንዲሆን ትልቅ አስተዋጽዖ አበርክቷል፡፡
በዚያው ሀዋሳ ላይ በተደረገው ጉብኝት FH Ethiopia በተለይ በትምህርት ላይ ያከናወናቸውን ዋና ዋና ተግባራት ፕሮጀክቶቹ በሚገኙበት ሸበዲኖ ወረዳ በትምህርት መሰረተ ልማትና በቅድመ መደበኛ ትምህርት እንዲሁም በጤና አጠባበቅ ሰርቶ ማሳያ ማዕከል ለጎብኝዎች አሳይተዋል፡፡
May be an image of 11 peopleበሁለተኛው ቀን በተደረገው ጉብኝት በዎላይታ ሶዶ ዙሪያ ሄሊቪታስ (Heli Vitas) እና አግሪቴራ (Agri tera) የተባሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በድልድይ መሰረተ ልማት እና በኢኮኖሚ አቅም ግንባታ ላይ የሰሯቸውን ስራዎች አስጎብኝተዋል፡፡ በአርባ ምንጭ ከተማ በተደረገው ጉብኝትም በተለይ በህጻናት ቃጠሎ ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራው ችልድረን በርን ኤንድ ውንድድ ኬር ፋውንዴሽን(children burn and wounded care foundation) እና በግብርና እና ስራ እድል ፈጠራ ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራው ኤስ ኤን ቪ ስዊዝ ኮርፖሬት SNV Swiss corporate) የሰሯቸውን ስራዎቻቸውን አስጎብኝተዋል፡፡ በኮንሶ ዞን ካራት ከተማ ዙሪያ እና ኬና ወረዳዎች የእናቶችና ህጻናት ዘርፈ ብዙ ልማት ድርጅት የተባለው ሀገር በቀል ድርጅት በውኃ እና በግብርና ላይ የሰራቸውን ስራዎች ያስጎበኘ ሲሆን በእለቱም በኬና ወረዳ ለማህበረሰቡ አገልግሎት ክፍት ያደረጋቸውን የውኃ ቦኖዎች በምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ መስፍን ሙሉነህና በዞኑ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች አስመርቋል፡፡
በተለይም በኮንሶ እና በቦረና ዞኖች ከድርቅ ጋር በተያያዘ ያጋጠመውን የውኃ እጥረት ለመቅረፍ የእናቶችና ህጻናት ዘርፈ ብዙ ልማት ድርጅት፣ እስላሚክ ሪሊፍ፣ ጀርመን አግሮ አክሽን እና ኬር ኢትዮጵያ የውኃ ማስፋፊያዎችን በመገንባት፣ የሶላር ኃይልን በመጠቀም ውኃን ለማህበረሰቡ በማዳረስ እንዲሁም የአየር ንብረቱን የሚቋቋሙ የሰብል ምርቶችን በማስተዋወቅና ምርታማነትን በማሳደግ ረገድ ያከናወኗቸው ተግባራት በጉብኝቱ ወቅት ትኩረት የተሰጣቸው ናቸው፡፡
ጉብኝቱ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የማህበረሰቡን የላቀ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሚያደርገው ጥረት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምን ያህል አስተዋጽዖ እያደረጉ እንደሚገኙ ያስተዋወቀ እና ከመገናኛ ብዙኃንም ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል መንገድ የጠረገ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡

 


የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በየዓመቱ የሚያዘጋጀው የሚዲያ ኃላፊዎች የመስክ ምልከታ ሚዲያ ቱር ፕሮግራም እየተካሄደ ይገኛል፡፡

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የተቋሙን ተግባርና ሃላፊነት ማስተዋወቅንና የድርጅቶቹን አንቅስቃሴ በአካል ለሚዲያዎች በማሳየት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ለማህበረሰቡ ብሎም ለባለድርሻ አካላት ስራዎቻቸውን በመገናኛ ብዙኃን አማካኝነት እንዲያስተዋውቁ በማድረግ የዘርፉ ሚና የማጎልበት እና የማህበረሰቡን የላቀ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ዓላማ አድርጎ የተጀመረው የሚዲያ አካላት የመስክ ጉብኝት ለ4ኛ ጊዜ ከተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ኃላፊዎች በተገኙበት መካሄድ ጀምሯል፡፡ በፕሮግራሙ ላይ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ እና ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ መስፍን ሙሉነህን ጨምሮ ከተለያዩ የሚዲያ ተቋማት የተውጣጡ የሚዲያ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
May be an image of 9 people and textበጉብኝቱ ላይ የተገኙት የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ ባደረጉት ንግግር አዲሱ አዋጅ ከወጣበት 2011 ዓ.ም ወዲህ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ህግን መሰረት አድርገው በነጻነት መንቀሳቀስ እንዲችሉ ሰፊ እድል የሰጠ መሆኑን ጠቅሰው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ፤ ሚዲያና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች መቀናጀታቸው ህዝብ ተጠቃሚ እንዲሆን የሚያስችል በመሆኑ ይህ ቅንጅት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አንስተዋል፡፡ በመጀመሪያው ቀን ጉብኝት MSH እና FH Ethiopia የተባሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በሀዋሳ ከተማ በጤናና በትምህርት ዘርፎች ላይ በሀዋሳ ከተማ የሰሯቸውን ስራዎች ያስጎበኙ ሲሆን ድርጅቶቹ የሚሰሩበትን ዓላማ እንዲሁም ድርጅቶቹ ከተቋቋሙበት ጊዜ አንስቶ ከመንግስትና ከማህበረሰቡ ጋር በመቀናጀት በትምህርትና በጤና እንዲሁም በአቅም ግንባታና መሰል ተግባራት ላይ ያከናወኗቸውን ተግባራት አቅርበዋል፡፡ በሁለተኛው የጉብኝቱ ቀን በዎላይታ ሶዶ በውኃ፣ ምግብና አየር ንብረት፤ በስራ እድል ፈጠራና አሳታፊነት ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራው ሄልቪታስ የተባለው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት የሰራውን የባንበላ በዴሳ ተንጠልጣይ ድልድይ በመስክ የታየ ሲሆን ድርጅቱ በተቋቋመባቸው ዓላማዎች መሰረት ያከናወናቸውን ዋና ዋና ተግባራት አስተዋውቋል፡፡
በተጨማሪም በዚሁ በዎላይታ ሶዶ ዞን በኢኮኖሚ አቅም ግንባታ ላይ ትኩረቱን አድርጎ የሚሰራው አግሪ ቴራ የተባለው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት በዞኑ ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ በሄምቤቾ ገበሬዎች ሁለገብ መሰረታዊ የህብረት ስራ ማህበር ያደረጋቸውን የአቅም ግንባታ ስራዎችን በመስክ ጉብኝት የታዪ ሲሆን ድርጅቱን የስራ እንቅስቃሴ በተመለከተ የድርጅቱ የስራ ኃላፊዎች ገለጻ አድርርዋል፡፡ ጉብኝቱ በአርባ ምንጭ ከተማ የሚቀጥል ሲሆን በግብርና በጤና መሰረተ ልማት ላይ የተሰሩ ስራዎች በጉብኝቱ የሚዳሰሱ ይሆናል፡፡

 


ሀገር በቀል የፋይናንስ ተስፋ ሰጪ ምንጮች ለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በሚል የፓናል ውይይት ተካሄደ፡:

May be an image of 1 person, dais and text that says 'វ MSI REPRODUCTIVE CHOICES MECHANISMS OF A PANEL DISCUSSION ΟΝ PROMISING SUSTAINABILITY DOMESTIC FINANCING FOR THE OF CIVIC SOCIETY ORGANIZATIONS ሀገር በቀል የፋይናንስ ተስፋ ሰጪ の円 ለሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች ቀጣይ ፋይዳ -የዉይይት መ MAY20,20 MAY 20 203 ADDIS መስበስት'የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ 1113/2011 ለሀገር በቀል ድርጅቶች የገቢ ማስገኛ ስራዎችን እንዲሰሩ ፍቃድ የሰጠ በመሆኑ በርካታ ድርጅቶች በገቢ ማስገኛ ስራ ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ፡፡ በውይይቱ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ም/ ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ እንዳሉት አዲሱ አዋጅ ለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ከፍተኛ የሆነ የስራ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ ሰፊ ምዕዳር የፈጠረ መሆኑን በማንሳት ሀገር በቀል ድርጅቶች ከውጭ እርዳታ ጥገኝነት ተላቀው በሀገር ሀብት መንቀሳቀስ እንዳለባቸው ገልፀዋል፡፡ አያይዘውም በባለስልጣኑ ተመዝግበው ከሚገኙ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ውስጥ ከ3000 በላይ አዲስ የተመዘገቡ ድርጅቶች መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
ሌላው ያነሱት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ታይቶ መጥፋት ሳይሆን ንቁ፣ ዓላማውን ያወቀ፣ በማህበረሰቡ ተቀባይነት ያለው፣ ለሀገር የሚጠቅሙ መሆን አለባቸው ያሉት ም/ዋና ዳይሬክተሩ አገር የሚጠቅም ትልልቅ ስራዎችን ማለትም በሰብዓዊ ድጋፍ፣በልማት እና በዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ላይ መስራታቸውን አንስተዋል፡፡ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ያላቸውን ጥሩ ተሞክሮዎችን በመለዋወጥ በአገር ላይ ጉልህ አሻራ ማሳረፍ እንዳለባቸውም/ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡ የማሪስቶፐስ ኢንተርናሽናል ካንትሪ ዳይሬክተር ዶ/ር አበበ ሽብሩ ባደረጉት ንግግር የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ትልቁ ሚናቸው የሀገራችንን እድገትና ኢኮኖሚ መደገፍ ነው ሲሉ በተለይ መንግስት በማይሸፍናቸው የልማት ስራዎችን በመስራት በህብረተሰቡ ዘንድ ዘለቄታ ያለው ስራ መስራት እንዳለባቸው አንስተዋል፡፡
ሌላው ያነሱት አዲሱ አዋጅ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በገቢ ማስገኛ ስራ ላይ እንዲሰማሩ የሚፈቅድ መሆኑን በመግለፅ በደንብ ከተተገበረ በሀገር ደረጃ ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር አንስተዋል፡፡ በመድረኩ ላይ በገቢ ማስገኛ ስራ ላይ ከተሰማሩ ድርጅቶች ሜሪስቶፐስ ኢንተርናሽናል እና ተስፋ ድርጅት ተሞክሯቸውን አቅርበዋል፡፡ የባለስልጣኑ ድጋፍና አገልግሎት መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ብርሀኑ አባተ የገቢ ማስገኛ መመሪያ ቁጥር 937/2015 ገለፃ አድርገዋል፡፡