11ኛው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን እና የፌዴራልና የክልል የመንግስት ባለድርሻ አካላት መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡:
11ኛው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን እና የፌዴራልና የክልል የመንግስት ባለድርሻ አካላት መድረክ ተካሂዷል፡: በጉባኤው ላይ የአዲሰ አበባ ከተማ አሰተዳደር ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይን ጨምሮ የፌደራል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ የክልል ፋይናንስና ፍትህ ቢሮ ተወካዮችና ሃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው ተሳታፊዎች በተገኙበት ተካሂዷል፡፡

ኤጌሬፍ የበጎ አድራጎት ድርጅት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች የ1 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ፡፡
ኤጌሬፍ የበጎ አድራጎት ድርጅት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች የ1 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ፡፡ በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ስር ተመዝግቦ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኘው ኤጌሬፍ የበጎ አድራጎት ድርጅት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች የሚውል የ1 ሚሊየን ብር ድጋፍ ለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን አስረክቧል።

የኢፌደሪ የፍትህ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ኤርሚያስ የማነብርሃን እና በም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ የተመራ ልዑካን ቡድን ድርጅቶችን ጎበኙ፡፡

በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በድንገተኛ አደጋ ለተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች ከ 10 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የእለት ደራሽ ድጋፍ ተደረገ።
በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በድንገተኛ አደጋ ለተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች ከ 10 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የእለት ደራሽ ድጋፍ ተደረገ። በፍትህ ሚኒስቴርና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን አስተባባሪነት የሰዎች ለሰዎች ድርጅት (Menschen fűr Menschen) ከ 10 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጓል። የኢፌደሪ የፍትህ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ኤርሚያስ የማነብርሃን በአከባቢው በደረሰው ድንገተኛ የተፈጥሮ አደጋ ህይወታቸውን ባጡ ወገኖች የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን በመግለፅ በአከባቢው የተጎዱ የማህበረሰብ ክፍሎችን በዘላቂነት ለመደገፍ ከሲቪል ማህበረሰቦች ጋር በትብብር እንደሚሠሩ ተናግረዋል።

የፍትህ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት በጋምቤላ ክልል የክረምት በጎ ፍቃድ መርሃ ግብር አካሄዱ።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትህ ሚኒስቴር እና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን አመራሮችና ሰራተኞች የደም ልገሳ አካሄድ።

4ኛ ዙር የሰራተኞች ስልጠና ተሰጠ፡፡

የፍትህ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር በመሆን የዘንድሮውን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በአዳማ ከተማ አካሄዱ፡፡
በመርሃ ግብሩ የፍትህ ሚኒስቴር ሚኒስትሩ ዶ/ር ጌዲዬን ጢሞቲዎስ ፣መለሰ ዓለሙ የዲሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ሚኒስትር ፣የኢፌዴሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ ፣ የአዳማ ከንቲባ አቶ ሃይሉ ጀልጌ ፣የተለያዩ ተቋማት ሃላፊዎች፣የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችና እና የአከባቢው ማህበረሰብ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በሃገር አቀፍ ደረጃ ‹‹የምትተክል ሃገር የሚያጸና ትውልድ ›› በሚል መሪ ቃል የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር እየተካሄደ ይገኛል፡፡ በዚሁ መሰረት በኢፌዴሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን አስተባባሪነት የፍትህ ዘርፍ ከሲቪል ማበረሰብ ድርጅቶች ጋር በጋራ በመሆን በአዳማ ከተማ ለምግብነት የሚውሉ ከሁለት ሺህ በላይ ችግኞችን ተክለዋል፡፡

በሰዎች ለሰዎች ድርጅት ስር የሚተዳደርው የሐረር አግሮ-ቴክኒክና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ ተማሪዎችን አስመረቀ::

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የተቋም ግንባታና ሪፎርም ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኤርሚያስ የማነብርሀን የተመራ ልዑካን ቡድን የተቋሙን የ2016 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ገመገሙ፡፡














