የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በወጣቶች ሰላም ግንባታ እና በስሜታዊ ብልህነት (Emotional Intelligence) ላይ ያተኮረ ስለጠና ሰጠ።
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከSOS Children’s village ጋር በመተባበር በወጣቶች ሰላም ግንባታ እና በስሜታዊ ብልህነት (Imotional Intelligence) ላይ ትኩረት ያደረገ የሁለት ዙር ስልጠና ለተቋሙ ወጣት ሰራተኞች ሰጥቷል።
ስልጠናው ወጣቶች በሰላም ግንባታ ላይ ያላቸውን ግንዛቤ እንዲያሳድጉና ከሰላም ግንባታ ጋር በተያያዘ እንደወጣት የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት መወጣት እንዲችሉ በማለም የተዘጋጀ ስልጠና ነው፡፡በተጨማሪም ከስሜታዊ ብልህነት (Emotional Intelligence) ጋር በተያያዘ ወጣቶች በምን መልኩ ማዳበር እንዳለባቸውና ለሰላም ግንባታ ያለውን ሚና በሚመለከት ገለጻ ተደርጓል፡፡
ስልጠናው በሁለት ዙር ለተከታታይ አራት ቀናት የተሰጠ ሲሆን በስልጠናው ላይ የSOS childrens village Location program manager በረከት ማቴዎስ ድርጅቱን በሚመለከት ገለጻ አድርገዋል፡፡ ወ/ሮ ትዕግስት አቡዬ በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ስራ አስፈፃሚ እንዲሁም ወ/ሮ ቤተልሄም ጌታቸው የLeave No Youth Behind Project አስተባባሪ የስልጠናውን ዓላማ በተመለከተ ገለፃና ማብራሪያ አድርገዋል፡፡።

