ምን እንርዳዎት?

ዓላማችን የህዝቡን የላቀ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እና የሲ.ማ.ድ በነፃነት መንቀሳቀስ ይችሉ ዘንድ ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር ነው ፡፡

የሲ.ማ. ድ. ከመጀመርዎ በፊት መከተል ያለብዎትን አግባብነት ያላቸውን ህጎች እና ቅደም ተከተሎች ይመልከቱ፡፡

ምን ዓይነት እንቅስቃሴዎች ሕገ-ወጥ እንደሆኑ ፣ ልንመረምራቸው የምንችላቸውን የስጋት ዓይነቶች እና በተመዘገቡ ሲ ማ ድርጅቶች ላይ እንዴት ሪፖርት ማድረግ እንደሚቻል ይወቁ፡፡

የሲ ማ ድ ኤ በኢትዮጵያ ህገመንግስት በተሰጠው ተልእኮ ውስጥ በሲ ማ ድርጅቶች ዙሪያ በርካታ አገልግሎቶችን ያከናውናል፡፡

ስለ ኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን

ሲ.ማ.ድ.ባ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱትን የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ለመመዝገብ ፣ ለመደገፍ እና ለመከታተል የተቋቋመ መንግስታዊ ተቋም ነው ፡፡

ተግባራችን

ድርጅቶችን መመዝገብ ፣ መደገፍ ፣ መቆጣጠር እና መከታተል ሲሆን በተጨማሪም በአዋጅ 1113/2011 ዓ.ም ተገዢ በመሆን ተግባራቸውን ማከናወናቸውን ያረጋግጣል፡፡

ርዕያችን

የሕብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ያረጋገጠ፤ የዳበረ የሲቪል ማህበረሰብ ተፈጥሮ ማየት፤

ስለ ባለስልጣኑ

የዋና ዳይሬክተር መልእክት

ክቡር አቶ ሳምሶን ቢራቱ

የመደራጀት መብትን የሚያስከብር፣ ዲሞክራሲያዊ ማህበረሰብን ለመፍጠር ወሳኝ የሆነና፣ የሲቪል ማህበራት በአገር ልማትና ዕድገት ውስጥ ያላቸውን ሚና ለማጎልበት የሚያስችል አዲስ ሕግ /አዋጅ ቁጥር 1113/2011/ ወጥቶ ተግባራዊ ከሆነ ወዲህ ተቋማችን የሲቪል ማኅበረሰብ ዘርፉን ለማጠናከርና በልማትና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ውስጥ ሚናቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ለማድረግ በሚያስችል መልኩ እየሰራ የሚገኝና ከዚህ በፊት የነበሩትን ችግሮች በመቅረፍ ሴክተሩ ከመንግሥት ጋር የነበረውን የሻከረ ግንኙነት በመለወጥ በአጋርነት መርህ ላይ የተመሠረተ እንዲሆን በማድረግ፤ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በተለይም ግልጽነትን፣ ተጠያቂነትንና አሳታፊነትን ለማረጋገጥ የተደራጀ የሲቪል ማህበረሰብ መኖር አስፈላጊ እንደሆነ በመገንዘብ፤ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች እራሳቸውን በራሳቸው የሚያስተዳድሩበት ጠንካራ ስርዓት እንዲዘረጋ ጥረቶች ሲደረጉ ቆይቷል፡፡ በዚህም አበረታች ውጤቶች ተመዘግበዋል፡፡

የኢ.ፌ.ድ.ሪ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችን በመመዝገብና እውቅና በመስጠት እንዲሁም ድጋፋዊ ክትትል በማድረግ፤ ህግን ተከትለው እንዲሠሩ በማብቃት በሀገሪቱ ሁለንተናዊ እድገት ውስጥ የሚኖራቸውን ሚና በአግባቡ እንዲወጡ በማድረግ የህብረተሰቡን የላቀ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና በሀገራችን የበጎ አድራጊነትና የበጎ ፍቃደኛነት ባህልን ለማጎልበትና ለማስረጽ እየሰራ ይገኛል፡፡ ኤጀንሲው በአዋጅ የተሰጡትን ሥልጣንና ተግባራት በብቃት መወጣት እንዲያስችለው አዲስ መዋቅር በመቅረጽና በሚመለከተው አካል በማጸደቅ ወደ ሥራ ገባ ሲሆን የሲቪል ማኅበረሰብ ዘርፉም በትምህርት፣ በጤና፣ በምግብ ዋስትና፣ በአካባቢ ጥበቃ ወዘተ. መንግሥትን በማገዝ ከፍተኛ ለውጦች በማስመዝገብ ላይ ይገኛሉ፡፡ በዚሁ መሰረት የአዋጁን መውጣት ተከትሎ ዳግም እና አዲስ ምዝገባ ከተጀመረበት ከሚያዚያ 2011 ዓ.ም ጀምሮ በቀድሞ አዋጅ ቁጥር 621/2001 ተመዝግበው ከነበሩ ድርጅቶች መካከል 1805 ድርጅቶች ዳግም የተመዘገቡ ሲሆን ከ1300 በላይ አዳዲስ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ለመመዝገብም ተችሏል፤ የአዳዲስ ድርጅቶች ምዝገባ ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እንዲጨምር ያስቻለው የምዝገባ ሥርዓቱ ቀላል፣ቀልጣፋ፣ተደራሽና ተገማች ማድረግ በመቻሉ ነው፡፡ ይህንን ከፍተኛ የስራ አፈፃፀም ለማስመዝገብ የተቻለው የተቋሙ አመራር ቁርጠኝነትና ሠራተኞቻችን ያሳዩት ከፍተኛ የስራ ተነሳሽነት በመሆኑ በዚሁ አጋጣሚ ላቅ ያለ ምስጋናዬን አቀርባለሁ፡፡

እንደሚታወቀው በሀገራችን ተመዝግበው ያሉት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ቁጥር ከጎረቤት አገራት ጋር ሲታይ አነስተኛ ቢሆንም በቀጠይ 10 ዓመት ውስጥ ቁጥሩን በአራት እጥፍ ለማሳደግ ግብ ተቀምጧል፡፡ ለዚህም ባለስልጣኑ በቀጣይ 10 ዓመት የሚመራበት ስትራቴጂክ ረቂቅ እቅድ አዘጋጅቷል፤ ከትኩረት መስኮችም ዋናው የላቀ አገልግሎት አሰጣጥ በመሆኑ ይህንን እውን ለማድረግ የባለስልጣኑን አገልግሎት አሰጣጥ ተደራሽ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑና ተገልጋዩ ኅብረተሰብ መረጃዎችን በቀላሉ ለማግኘት እንዲቻል የባለስልጣኑን ድረ-ገፅ ለማበልፀግ አበረታች ስራዎች የተጀመሩ ቢሆንም በያዝነው ዓመት የበለጠ ለማሻሻልና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ አገልግሎት አሰጣጥ በስፋት ተግባራዊ ለማድረግ፤ ከአጋር ድርጅቶች ጋር ስራዎች ተጀምሯል፤ እንዲሁም ቀደም ሲል ከሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ጋር የተጀመሩትም የውይይት መድረኮች ቀጣይነት የሚኖራቸው ሲሆን በኤጀንሲውና በድርጅቶቹ መካከል የተፈጠረው መተማመን የበለጠ እንዲጎለብት የሚያደርግ መሆኑ በባለፉት ሁለት ዓመታት የተደረጉት ውጤታማ ውይይቶች ማሳያ ናቸው፡፡ የአዲሱ አዋጅ መውጣት ተከትሎ የአዋጁ ማስፈፀሚያ ረቂቅ ደንብ ተዘጋጅቶ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ከተደረገና ግብዓት ከተሰበሰበ በኋላ ለሚመለከተው አካል ቀርቦ በመጽደቅ ሂደት ላይ ይገኛል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ አዋጁንና ደንቡን ለማስፈጸም የሚረዱ መመሪያዎች በተመለከተ በርካታ ውይይቶች ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር የተደረገበት መሆኑ ይታወቃል፤ይሁን እንጂ መመሪያዎቹ ላይ ቀጣይ የውይይት መድረኮችን በማዘጋጀት በፅሁፍና በየውይይት መድረኮች የሚሰጡትን ግብዓቶች በመውሰድ በኤጀንሲው ቦርድ ፀድቀው በአጭር ጊዜ ውስጥ ተግባራዊ ይሆናሉ፡፡ በመሆኑም ባለስልጣናችን ከመቼውም ጊዜ በላይ በከፍተኛ ቁርጠኝነት የሀገራችንን የብልፅግና ጉዞ እውን ለማድረግ የተጀመረውን ፈርጀ ብዙ ተግባራት በመደገፍ ረገድ ሆነ በመንግስትና ህዝብ የተጣለብን ኃላፊነት በተገቢው ለመወጣት በፍፁም የአገልጋይነት መንፈስና በከፍተኛ የስራ ተነሳሽነት ተግባራዊ ለማድረግ ይሠራል፡፡ በመጨረሻም እስከ አሁን ባስመዘገብናቸው ድሎች ሳንዘናጋ በግልጽ ያስቀመጣቸውን እሴቶቻችንን በመላበስ ተገልጋዩን ህብረተሰብ በቅንነት፣በታማኝነት፣በግልጽነትና ተጠያቂነት፤ ብልሹ አሰራርና ሙስናን በመጸየፍ፤ ሙያዊ ብቃትና ስነምግባር በተላበሰ መልኩ፤ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት ተገቢ መሆኑን በመገንዘብ በከፍተኛ የኃፊነት ስሜት ሥራችንን የምንወጣ ይሆናል፡፡

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እና ተገልጋዮቻችን ይህንኑ በመገንዘብ ችግሮች ሲኖሩ በዘረጋናቸው የቅሬታ ማቅረቢያ ስርዓቶች በመታገዝ ቅሬታችሁን በማቅረብ እርምት በሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ላይ ሕጸጾቻችንን በማሳወቅ ለስራችን መቃናት ድጋፍ እንድታደርጉ በትህትና እጠይቃለሁ፡፡

አመሰግናለሁ!!!

አዳዲስ ዜናዎች


አንዳንድ መረጃዎች ስለ ኢ.ፌ.ድ.ሪ. የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን

2669

ባለስልጣኑ በ 2011 ዓም እንደገና ከተደራጀበት ጊዜ አንስቶ ከ2669  በላይ አዲስ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን መዝግቧል። ከነዚህ ውስጥ 2455 ሀገር በቀል እንዲሁም 214 የውጪ ድርጅቶች ናቸው፡፡

4568

ከተመዘገቡት መካከል ከ1899 በላይ የሚሆኑት በአዋጅ ቁጥር 1113/2011 ዳግም የተመዘገቡ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ናቸው።


አዋጅ ቁጥር 1113/2011

በኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን የሚገዛው ሕግ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር 1113/2011 ዓ.ም ነው ፡፡

ራስን በራስ ማስተዳደር

በአዲሱ አዋጅ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ራሳቸውን በራሳቸው እንዲያስተዳድሩ በተደነገገው መሠረት በሁሉም ድርጅቶች ተሳትፎ እና በኤጀንሲው ድጋፍ ለመጀመሪያ ጊዜ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ተመስርቷል ፡፡

ገዥ ህጎች

ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሕገ-መንግሥቱን ፣ የሲ.ማ.ድን አዋጅ ፣ የወንጀልና የፍትሐ ብሔር ሕጎችን እና ሌሎች አግባብነት ያላቸው ደንቦች እና መመሪያዎችን አክብረው መንቀሳቀስ ይኖርባቸዋል ፡፡

አጋሮቻችን


[mailpoet_form id="1"]