ኤጌሬፍ የበጎ አድራጎት ድርጅት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች የ1 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ፡፡ በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ስር ተመዝግቦ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኘው ኤጌሬፍ የበጎ አድራጎት ድርጅት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች የሚውል የ1 ሚሊየን ብር ድጋፍ ለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን አስረክቧል።

May be an image of 3 people, dais, newsroom and text
ድጋፉን የተቀበሉት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ ድጋፉ እርስ በርስ የመደጋገፍ፣ የመተጋገዝና የመረዳዳት ባህላችንን አጉልቶ የሚሳይ መሆኑን ጠቁመው በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የተመዘገቡ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የሚሰሯቸውን ሰው ተኮር ስራዎች ስንመለከት ከዚህ በላይ በርካታ ስራዎችን መስራት እንደምንችል የሚያመላክቱ ናቸው ብለዋል፡፡ አክለውም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ሀገር በቀል ድርጅቶችን በልዩ ሁኔታ በመደገፍ ውጤታማ ስራ መስራት እንዲችሉ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸው ሀገር በቀል ድርጅቶች ተጠናክረው በጋራ ትልቅ ስራ መስራት እንደሚችሉ ጠቁመዋል፡፡
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልና የኤጌሬፍ የበጎ አድራጎት ድርጅት መስራችና ምክትል የቦርድ ሰብሳቢ ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ በበኩላቸው ድርጅታቸው ኤጌሬፍ የበጎ አድራጎት ድርጅት በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የተለያዩ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች ሲያጋጥሙ በርካታ የሰብዓዊ ድጋፎችን በማድረግ የሚታወቅ ድርጅት መሆኑን ጠቅሰው በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ሁልግዜ እንደሚያደርገው ወገናዊነቱን ለማሳየትና ከጎናቸው መሆኑን ለመጠቆም በባለስልጣን መስሪየ ቤቱ በኩል ድጋፍ ማድረጉን ገልጸዋል፡፡ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በጎፋ ዞን የደረሰውን የመሬት መንሸራተት ተከትሎ ጉዳት ለደረሰባቸው የማህበረሰብ ክፍሎች የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን በማስተባበር ድጋፍ እያደረገ የሚገኝ ሲሆን ቀደም ሲል ሰዎች ለሰዎች ከተባለ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ጋር በመተባበር ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ የእለት ደራሽ ድጋፎችን ቦታው ላይ በመገኘት አስረክቧል፡፡