በፍትህ ሚኒስቴር ስር ያሉ ተቋማትን የ2016 በጀት የእቅድ አፈጻጸማቸውን በመገምገም የሚሰጡትን አገልግሎቶች በይበልጥ ለመረዳት እና ተቋማት ከሚኒስቴር መስሪያቤቱም ሆነ ከሌሎች ተቋማት የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ ለማድረግ ፕሮግራሙ መዘጋጀቱን ሚኒስትር ዴኤታው ገልጸዋል፡: አያይዘውም ሚኒስትር መስሪያቤቱ በስሩ ተጠሪ ለሆኑ ተቋማት አስፈላጊ ክትትልና ድጋፍ ለማድረግ ሚኒስቴር ዴኤታዎቹ ተቋማቱን ተከፋፍለው እየደገፉ መሆኑን አንስተው በዚህ ተቋም የተጀመረው የድጋፍ ስራም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡ የባለስልጣን መስሪያቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ ለእንግዶቹ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ካደረጉ በኋላ ለተቋሙ የተሻለ አፈጻጸም ሚኒስትር መስሪያቤቱ ለድጋፍ በመምጣቱ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ የተቋሙ የ2016 አፈጻጸም በዝርዝር ከቀረበ በኋላ በተነሱ ርዕሠ ጉዳዬች ላይ ምላሽና በቀጣይ ለተቋሙ በሚያስፈልጉ ድጋፎች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል፡፡




