በቀጣይ ስድስት ወራት የማህበረሰቡን የላቀ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንሰራለን ተባለ፡፡
ይህ የተባለው በተቋሙ የ2016 የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት እቅድ አፈጻጸም እና የቀጣይ ስድስት ወራት እቅድ ላይ ከአጠቃላይ ሰራተኛው ጋር ውይይት በተደረገበት ወቅት ነው፡፡ በመድረኩ ተቋሙ በባለፉት ስድስት ወራት ያከናወናቸውን ዋና ዋና ጉዳዬች ፣ያጋጠሙ ችግሮችና የተወሰዱ የመፍትሄ አቅጣጫዎች እና የቀጣይ ስድስት ወራት እቅድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ በውይይቱ ማጠቃለያ የተቋሙ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ እንደገለጹት በባለፉት ስድስት ወራት ተቋሙ ያከናወናቸው ተግባራት ውጤታማ መሆኑን በመግለጽ በተለይም የተገልጋይ እርካታ አፈጻጸም ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የተሻለ መሆኑን አንስተዋል፡፡
ለተቋሙ ሰራተኞች ከዕዳ ወደ ምንዳ በሚል ርዕስ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
የስልጠናው ዓላማ የመንግስት ሰራተኛው ከዕዳ ወደ ምንዳ ለመሸጋገር የሚያችለው ወቅታዊ፣ ሃገራዊ፣ ህዝባዊና መንግስታዊ አጀንዳዎች ላይ በመወያየትና በመመካከር የተሻለ ግንዛቤ መፍጠር፤ሁሉም ዜጋ የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ማስቻልና የሃገራችንን አንድነት ለማስቀጠል ህዝባችንን ወደ ላቀ የዕድገት ደረጃ ለማሻገር ያለመ ነው፡፡ የመወያያ ርዕሰ ጉዳዮቹ ትኩረት ያደረጉት ሃብት ለመፍጠር ያሉ እድሎች እና የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎች፣ በኢትዮጵያ አገልጋይና ስልጡን ሲቪል ሰርቪስ ለመገንባት በተደረገው ጥረት የተስተዋሉ ስኬቶች፣ ፈተናዎችና የቀጣይ ትኩረት አጀንዳዎች ላይ ሲሆን በቀረበው ሰነድ ላይም ሰፊ ውይይት ተደርጎ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ በኢትዮጵያ የጀርመን አምሳደር የሆኑትን ስቴፈን ኦየር (Stephan Auer) በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

በተቋሙ ስትራቴጂክ ዕቅድ አፈፃጸምና ትግበራ ዙርያ የማኔጅመንት አባላት ውይይት አደረጉ፡፡

የመደራጀት መብትን ለማረጋገጥ የምዝገባና ሰነድ ማረጋገጥ መሪ ስራ አስፈጻሚ ከፍተኛ ሚና አለበት ተባለ፡፡

በዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ የተመራ ልዑካን ቡድን የማሪስቶፕስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ (MSI) የስራ እንቅስቃሴ ተመልክተዋል፡፡

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ለተቋሙ ሰራተኞች የተቋሙን ስትራቴጂያዊ ትራንስፎርሜሽን እቅድ በሚመለከት ስልጠና ሰጠ፡፡

6ተኛው ዙር ተቋማዊ የንባብ ቀን በቢሾፍቱ ከተማ ኢየሩሳሌም የህፃናት እና ማህበረሰብ ልማት ድርጅት ከቤተ መፅሃፍት ጋር ተያይዞ የሰራቸውን ስራዎች በመመልከት ተካሂዷል::

ምክር ቤቱ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የእርስ በእርስ የቁጥጥር ስርዓትን (Self-regulation scheme) ማጠናከር ላይ ትኩረት አድርጎ እንዲሰራ ምክረ ሃሳብ ቀረበ፡፡

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በቢሾፍቱ ከተማ የሚገኘውን የኮርያ ዓለም ዓቀፍ በጎ ፈቃደኞች ድርጅት (Korean International volunteer’s organization (KVO International) ጎበኙ፡፡













