ይህ የተባለው በተቋሙ የ2016 የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት እቅድ አፈጻጸም እና የቀጣይ ስድስት ወራት እቅድ ላይ ከአጠቃላይ ሰራተኛው ጋር ውይይት በተደረገበት ወቅት ነው፡፡ በመድረኩ ተቋሙ በባለፉት ስድስት ወራት ያከናወናቸውን ዋና ዋና ጉዳዬች ፣ያጋጠሙ ችግሮችና የተወሰዱ የመፍትሄ አቅጣጫዎች እና የቀጣይ ስድስት ወራት እቅድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ በውይይቱ ማጠቃለያ የተቋሙ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ እንደገለጹት በባለፉት ስድስት ወራት ተቋሙ ያከናወናቸው ተግባራት ውጤታማ መሆኑን በመግለጽ በተለይም የተገልጋይ እርካታ አፈጻጸም ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የተሻለ መሆኑን አንስተዋል፡፡May be an image of 4 people, table, dais and text

ዲጂታል ተቋም መገንባት፣በተሰማራንበት የስራ መደብ ስፔሻላይይዝድ ማድረግ፣የውስጥ የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻል ላይ የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ አድርገን እንሰራለንም ብለዋል፡፡ በመጨረሻም የጀመርናቸው ውጤታማ ስራዎች በማጠናከር፣በቁርጠኝነትና በትጋት አጠናክሮ በማስቀጠል የማህበረሰቡን የላቀ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንሰራለን ሲሉ ገልጸዋል፡፡