May be an image of 7 people

በዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ የተመራ ልዑካን ቡድን የማሪስቶፕስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ (MSI) የስራ እንቅስቃሴ ተመልክተዋል፡፡
ድርጅቱ ከተመሰረተ 30 ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን የእናቶች ጤና እና አማራጭ የስነ ተዋልዶ አገልግሎት ላይ ለበርካታ የማህበረሰብ ክፍሎች አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡
ዶ/ር አበበ ሽብሩ የድርጅቱ ካንትሪ ዳይሬክተር ተደራሽነት፣የድርጅቱን ተልዕኮ ማጠናከር እና ጥራት ላይ ስትራቴጂ ጉዳይ አድርጎ እየሰራ መሆኑን በማብራሪያቸው ወቅት ገልጸዋል፡፡
አያይዘውም አዲሱ አዋጅ 1113/2011 መሰረት አድርጎ የተዘጋጀው የገቢ ማስገኛ መመሪያ ቁጥር 937/2015 ድርጀቱ ቀጣይነት እንዲኖረው እና የውስጥ ሃብትን ለመጠቀም ትልቅ እገዛ እንዳደረገላቸው ገልጸዋል፡፡
የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ ከጉብኝቱ በኋላ በሰጡት አስተያየት የሃገሪቱ የጤና ፖሊሲ እና ጤና ሚኒስቴር ያወጣውን አሰራር እየደገፋችሁ መሆኑን በመመልከታችን ደስተኞች ነን በማለት በቅንጅት ከመንግስት እና ከማህበረሰቡ ጋር የሚሰራውን ስራ እንዲሁም የሃገር ውስጥ ሃብት መጠቀም መቻላችሁ ለሌሎች አስተማሪ ተግባር ነው ብለዋል፡፡