Feya integrated development organization በጅማ ከተማ HIV ቫይረስ በደማቸው ውስጥ ላለ የማህበረሰብ ክፍሎች ለምግብነት የሚውሉ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡
Feya integrated development organization በጅማ ከተማ HIV ቫይረስ በደማቸው ውስጥ ላለ የማህበረሰብ ክፍሎች ለምግብነት የሚውሉ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡
ቤተሰብ ላይ ያተኮረ ኤችአይቪ ኤድስ መከላከል እንክብካቤና ህክምና አገልግሎት ፕሮጀክት/ Family focused HIV prevention care and treatment activities/ ስር ለሚገኙ 15 ሺህ ህጻናት እና 2414 ቤተሰቦች ድጋፍና እንክብካቤ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ የኦሮሚያ ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ፍጽም ደሳለኝ ገልጸዋል፡፡
በ2017 በጀት ዓመት 729 ለሚሆኑ ማህበረሰብ ክፍሎች ተደራሽ የሆኑ ሲሆን በትላንትናው ዕለትም በጅማ ከተማ ለሚኖሩ 424 ተማሪዎች ዩኒፎርም እና የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ፣ ለ200 ሴት ተማሪዎች የንጽህና መጠበቂያ እና ለ 258 ቤተሰቦች ለምግብነት እና ለገቢ ማስገኛነት የሚውሉ የቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡


የድርጅቱ መስራችና ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አንበሱ ቶላ በንግራቸው እንደገለጹት የዛሬ ሃያ አንድ ዓመት በትንሽ አገልግሎት የተጀመረው የሰብዓዊነት ስራ አሁን ላይ ተቋም ሆኖ በብዙ የሃገሪቱ ክፍሎች ላይ ተደራሽ እየሆኑ መምጣታቸውን ገልጸዋል፡፡
በክብር እንግድነት የተገኙት ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ፣ የተቋማችን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ፣ም/ዋና ዳይሬክተሮች አቶ ፋሲካው ሞላ እና አቶ መስፍን ሙሉነህ ፣ የድርጅቱ መስራች ዶ/ር አንበሱ እና ሌሎች የክብር እንግዶች በጋራ በመሆን ስጦታውን አበርክተዋል፡፡Feya integrated development organization በልማት እና አስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ላይ የሚሰራ ሃገር በቀል ድርጅት ነው፡፡
የኢፌደሪ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን አመራርና ሰራተኞች 18ኛውን የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን “ሰንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብስራት፤ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለሕዳሴያችን!!!” በሚል መሪ ቃል አከበሩ፡፡

የበዓሉ ዋና ዓላማ ስለ ሰንደቅ ዓላማ ምንነት፣ ክብርና ትርጓሜ በተገቢው መንገድ ዜጎች አንዲረዱ በማድረግ ለሀገራችን ሉዓላዊነት፤ለነጻነት እና ለሰንደቃችን ክብር የተደረገውንና እየተደረገ ያለውን ተጋድሎ ተገቢውን እውቅና በመስጠት የጋራ ሀገራዊ መግባባት እና ሕብረብሔራዊ ወንድማማችነትንና እህትማማችነት በማጠናከር ብሔራዊ አንድነትን ማፅናት መሆኑን የባለስልጣን መስሪያቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ ባስተላለፉት መልዕክት ገልጸዋል፡፡
ይህንን ቀን ስናከብር ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ምርቃት፣ በሶማሌ ክልል 111 ሚሊዮን ሊትር ማምረት የሚችለውን የኦጋዴን ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክት የመጀመሪያ ዙር ምርቃትና ከሁሉ በላይ የመንግስት ሰራተኞች ደሞዝ በተጨመረበት ወቅት መሆኑ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል፡፡
ቃል በተግባር መርሁ የሆነው መንግስታችን የመንግስትን አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም በላቀ ደረጃ ለማስፈጸም ለመንግስት ሰራተኞች እና አመራሮች የደሞዝ አስኬል ማሻሻያ ያደረገ ሲሆን በዛሬዉ እለትም የባንዲራ ቀንን ስናከብር ማህበረሰቡን ከተከፈለን በላይ ለማገልገል ቃል በመግባት እና የሃገራችንን የከፍታ ጉዞ በማሳብ ሊሆን ይገባል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
መንግስት ሰራተኛው ላይ ያደረገውን ከፍተኛ ለውጥ በመረዳት፤የሀገራችንን ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ የመንግስትን ህግና ደንብ በማክበር፤ የተሰጠንን የመንግስት ስራ በቁርጠኝነት በመፈጸም የኢትዮጵያን ከፍታ ለማረጋገጥ መስራት ይጠበቅባችኋል ሲሉም ተናግረዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ህዝብ መዝሙር መዘመር እና በጋራ ቃለ መሃላ የመፈጸም ስራ ተሰርቷል፡፡

ካሊድ ፋውንዴሽን ከኢፌዲሪ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ጋር በመተባበር ለሶስት ሆስፒታሎች የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡

በደቡብ ፈረንሳይ ሰላም ኢትዮጵያ መረዳጃ ማህበር ከወንድም ካሊድ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር በኢፌደሪ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ትብብር ለጎንደር ዩኒቨርስቲ ጠቅላላ ሆስፒታል፣ ለወልዲያ አጠቃይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እና ለኮንቦልቻ ጠቅላላ ሆስፒታል 30 ሚሊየን ብር የሚገመት የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ፡፡
በርክክብ ስነ ስርዓቱ ላይ የኢፌዲሪ ጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ፣የባለስልጣን መስሪያቤቱ ም/ዋና ዳይሬክተሮች አቶ ፋሲካው ሞላ እና አቶ መስፍን ሙሉነህ፣የፋውንዴሽኑ ም/የቦርድ ሰብሳቢ አርቲስት ሰራዊት ፍቅሬ ፣የሶስቱ ሆስፒታሎች ተወካይ እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
ክብርት ሚኒስትሯ ባደረጉት ንግግር የበጎ ፍቃድ ስራ አስኪለመድ ግዜ ይወስዳል ነገር ግን ከተጀመረ በኋላ ባህል መሆን እንደሚችል ካሊድ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡
በኮቪድ ወቅት በራሳቸው ፍቃድ በራቸውን ከፍተው ማዕድ ያጋሩበትና ለሰው የደረሱበት ተግባር ዘር ሆኖ እዚህ ደርሷል በማለት አሁንም ግለሰብ፣ቤተሰብ እና ማህበረሰብ የሚገነባበት ቤት በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የኢፌዲሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ ባስተላለፉት መልዕክት በፋውንዴሽኑ በርካታ ከጎዳና ላይ የሚኖሩ ወጣቶችና ሴቶችን ስልጠና በመስጠትና እራሳቸውን እንዲችሉ ማድረጉን እና በሃገራዊ ጉዳዬች ላይ የችግኝ ተከላ፣ የህዳሴ ግድብ ግንባታ፣የአቅመ ደካማ ቤቶች ግንባታ ስራ ላይ እየተሳተፉ መሆኑን ተመልክተናል ብለዋል፡:
አምራች ዜጋ እንዲፈጠር ህጻናት በመጠለያ እንዲያድጉ የተደረገውን ስራ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ትልቅ ክብር አለው ያሉት ም/ዋና ዳይሬክተሩ ወንድም ካሊድ ፋውንዴሽንን የመሰሉ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን የመመዝገብ ብቻ ሳይሆን ድጋፍ የማድረግም ሃላፊነት ባለስልጣን መስሪያቤቱ ስላለበት ለሌሎችም ሞዴል እንዲሆን እንሰራለን ብለዋል፡፡
ፋውንዴሽኑ ከዚህ ቀደም በአጭር ጊዜ ጥሪ ሰብዓዊ ድጋፍ ላይ መሳተፋን ገልጸው የዛሬው ድጋፍም ከዚህ ቀደም በገቡት ቃል መሰረት የፈጸሙት መሆኑን በመግለጽ ለዚህ ሁሉ ድጋፍ መነሻ የሆኑትን በደቡብ ፈረንሳይ ሰላም ኢትዮጵያ መረዳጃ ማህበርን አመስግነዋል ፡፡
ወንድም ካሊድ በሰጠው ማብራሪያ አሁን ላይ በፋውንዴሽኑ 120 እናቶች ከነልጆቻቸው እና ከ400 በላይ ወጣቶች መኖራቸውን ገልጸው የዛሬው ድጋፋ ከዛሬ ሁለት ዓመት በፊት በሰሜኑ የሃገራችን ክፍል በተፈጠረው ችግር ምክንያት ድጋፍ ለማድረግ የተሰራ ስራ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
ፋውንዴሽናቸው ከተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በቅንጅት የሚሰራ ሲሆን በልዩ ሁኔታ የኢትዮጵያ አየር መንገድን እና ET ፋውንዴሽንን አመስግነዋል፡፡ በመጨረሻም ድርጅቱን የመጎብኘት እና ማዕድ የማጋራት ስራ ተሰርቷል፡፡

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር 1113/2011 ረቂቅ ማሻሻያ ላይ ውይይት ተደረገ፡፡
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር 1113/2011 ረቂቅ ማሻሻያ ላይ ውይይት ተደረገ፡፡
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከባለድርሻ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር 1113/2011 ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ላይ በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ ለግማሽ ቀን የቆየ ውይይት አካሂዷል፡፡
በውይይቱ ላይ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ተወካዮችና የተለያዩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ተወካዮች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
ውይይቱ የተደረገው ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን ቀደም ሲል በነበረው ውይይት ተሰጥተው የነበሩ ሃሳብና አስተያየቶችን በማከል ተጨማሪ ግብዓት ለማሰባሰብ የተደረገ የውይይት መድረክ ነው፡፡
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ የውይይት መድረኩን በንግግር ያስጀመሩ ሲሆን ረቂቅ ማሻሻያውን በሚመለከት ሰነድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ ለውይይቶቹ ምላሽና ማብራሪያ በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ እንዲሁም አቶ አዲስ ጌትነት በፍትህ ሚኒስቴር የህግ ማርቀቅ ዳይሬክቶሬት ጀነራል ተሰጥቷል፡፡

የበጎ ፍቃድ የሞባይል አፕልኬሽን ተዘጋጅቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደረገበት ፡፡

የበጎ ፍቃድ የሞባይል አፕልኬሽን ተዘጋጅቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደረገበት ፡፡
የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከኮርያ ኢንተርናሽናል ቮለንተርስ ኦርጋናይዜሽን ጋር በመተባበር የበጎ ፍቃድን ከማዘመን ጋር በተያያዘ እየበለፀገ ባለ የሞባይል እፕልኬሽን ዙርያ የግብዓት ማሰባሰብያ ውይይት ተደረገ::
በውይይቱ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች ፣ የተለያዩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ተወካዮች እና ከተለያዩ የመንግስት ተቋማትና ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል ፡፡
የኮርያ ኢንተርናሽናል ቮለንተርስ ኦርጋናይዜሽን ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ ወ/ሪት ማክዳ ተክለሃና እንደተናገሩት በሀገራችን በብዙ መልኩ የበጎ ፍቃደኝነት ያለ መሆኑን በመናገር በማህበረሰቡ ውስጥ ያለውን የበጎ ፍቃደኝነት ማሳደግ ምንችልበት የሞባይል አፕሊኬሽን ከዚህ ቀደም ባለመኖሩ ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጋር በመነጋገር መዘጋጀቱን ገልጸዋል፡፡
በውይይቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ ባስተላለፉት መልዕክት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በአዋጅ ከተሰጡት ተግባርና ሃላፊነቶች መካከል አንዱ የበጎ ፍቃደኝነትን እና በጎ አድራጊነትን ባህል በማኅበረሰቡ ውስጥ ማጎልበት መሆኑን በመግለጽ ይህም ፕሮጀክት በሁለተኛው ተቋማዊ ሪፎርም ዲጂታል ተቋም የመገንባት አካል ነው ብለዋል፡፡
ተቋሙ ከኮርያ ኢንተርናሽናል ቮለንተርስ ኦርጋናይዜሽን ጋር በመተባበር የበጎፍቃድ የሞባይል አፕሊኬሽን ማበልጸጉን ገልጸው የዛሬውን መድረክ ጨምሮ በተለያዩ መድረኮች ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት በማድረግ ግብዓት እየተወሰደ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን አመራሮችና ሰራተኞች ለ14ኛ ጊዜ የደም ልገሳ መርኃ ግብር አካሄዱ፡፡

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን አመራሮችና ሰራተኞች ለ14ኛ ጊዜ የደም ልገሳ መርኃ ግብር አካሄዱ፡፡
በሕብረተሰቡ ዘንድ የበጎ አድራጎትና በጎ ፈቃደኝነት ባህል እንዲዳብር ለማድረግ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከሚሰራቸው ተቋማዊ ስራዎች ባለፈ በበጎ ፈቃድ ተግባራት ላይ አመራሩና ሰራተኞቹ እያ አ ቸሳተፉ ይገኛሉ፡፡
በዚህ ወርም ለ14ኛ ጊዜ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አመራሮችና ሰራተኞች የተሳተፉበት የደም ልገሳ መርኃ ግብር ተካሂዷል፡፡ በደም ልገሳ መርኃ ግብሩ ላይ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በአዋጅ በጎ ፈቃደኝነት በህብረተሰቡ ውስጥ ባህል እንዲሆን ማስቻል ከተሰጡት ተግባራት መካከል መሆኑን ጠቁመው ከሌላው ተቋም በተለየ መንቀሳቀስ የሚጠበቅበት መሆኑን አንስተዋል፡፡
በደም ልገሳ መርኃ ግብሩ ላይ ለተሳተፉ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሰራተኞችና አመራሮች ያለማቋረጥ ሲሳተፉ ለቆዩት ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበው በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የደም ልገሳ ክበብ መቋቋሙን አብስረዋል፡፡
ከደም ልገሳው ባሻገር የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አመራሮችና ሰራተኞች የዓይን ብሌናቸውን ለኢትዮጵያ የዓይን ባንክ የለገሱ ሲሆን መርኃ ግብሩ በቋሚነት የሚቀጥል ይሆናል፡፡
ባለስልጣን መስሪያቤቱ ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የበጎ ፈቃደኝነት ባህልና እሴትን የተላበሱ እንዲሆኑ ለማድረግ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስጠናዎች መሰጠት አስፈላጊ መሆኑ ተገለፀ፡፡

ባለስልጣን መስሪያቤቱ ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የበጎ ፈቃደኝነት ባህልና እሴትን የተላበሱ እንዲሆኑ ለማድረግ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስጠናዎች መሰጠት አስፈላጊ መሆኑ ተገለፀ፡፡
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከማሪ ስቶፕስ ኢንተርናሸናል (MSI-Ethiopia) ጋር በዲጂታላይዜሽን ዘርፍ ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል የስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ፡፡
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከማሪ ስቶፕስ ኢንተርናሸናል (MSI-Ethiopia) ጋር በዲጂታላይዜሽን ዘርፍ ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል የስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ፡፡

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችና የባለድርሻ አካላት የትብብርና ቅንጅት መድረክ የፌደራልና የክልል አመራሮች ፎረም ተካሄደ፡፡
የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችና የባለድርሻ አካላት የትብብርና ቅንጅት መድረክ የፌደራልና የክልል አመራሮች ፎረም ተካሄደ፡፡

በሁለትዮሽ ስምምነት የሚሰሩ አህጉራዊና ክፍለ አህጉራዊ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ወደ ባለስልጣኑ ቀርበው ምዝገባ ካላከናወኑ እርምጃ እንደሚወስድ ተጠቆመ።

በሁለትዮሽ ስምምነት የሚሰሩ አህጉራዊና ክፍለ አህጉራዊ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ወደ ባለስልጣኑ ቀርበው ምዝገባ ካላከናወኑ እርምጃ እንደሚወስድ ተጠቆመ።






