በዓለማቀፍ ደረጃ 113ኛ ግዜ በሃገራችን ለ48ኛ ጊዜ ‹‹ሴቶችን እናብቃ፤ ልማት እና ሰላምን እናረጋግጥ›› በሚል መሪ ቃል ተከብሯል፡፡ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የተቋሙ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ስራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ጸሐይ ሽፈራው እንደተናገሩት በየዓመቱ በተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫና የንቅናቄ ተግባራት የሚከበር መሆኑን ገልጸው የንቅናቄው ዋና ዓላማ በዓለም ላይ ያሉ መንግስታት የሴቶች ጉዳይ የልማት፣ የመልካም አስተዳደርና የዲሞክራሲ ጉዳይ እንደሆነ አምነው በመቀበል በሴቶች ዙሪያ ፖሊሲዎቻቸውን ህጎቻቸውንና አሰራሮቻቸውን በመፈተሸ በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ መድልዎችን እንዲያስወግዱና የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ብሎም ጠቃሚነት እንዲያረጋግጡ ለማነሳሳት፣ሴቶች በኢኮኖሚያዊ፣ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዬች እንዲበቁ እና በሰላም ግንባታና ግጭት አፈታት ጉዳዬች ዙሪያ ጉልህ ሚና እንዲጫወቱ ለማድረግ እና ሌሎች ዓላማዎችን መሰረት ያደረገ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
May be an image of 1 person and dais
አቶ ፍቃዱ ወ/ሰንበት የተቋሙ የጽ/ቤት ሃላፊ በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት የዓለማቀፍ የሴቶች ቀን ሲከበር ለማክበር ብቻ ሳይሆን ሴቶችን በሁለንተናዊ ጉዳዬች ላይ ተሳታፊ እና ተጠቃሚ በማድረግ መሆን ይገባዋል ብለዋል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ በመንግስት የስራ ሃላፊነቶች ላይ እና በተለያዩ ጉዳዬች ዙሪያ የሴቶች ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት እንዲጎለብት መንግስት እየሰራ መሆኑን አንስተው በተቋማችንም ሴቶችን ከማቃት አንጻር የተጀመሩ ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አስረድተዋል፡፡ የሃገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት የሆነው የቤተሰብ መምሪያ ማህበር በመድረኩ ላይ ስለማህጸን በር ካንሰር የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ የሰሩ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ ለባለስልጣን መስሪያቤቱ ሴት ሰራተኞች የወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ በስጦታ አበርክተዋል፡፡