ተቋሙ የ9 ወራት እቅድ አፈጻጸሙን በማኔጅመንት ደረጃ ገምግሟል፡፡

በአፈጻጸሙም የዴስክ ክትትል፣ ግብረመልስ አሰጣጥ ፣ የደንበኞች እርካታ ፣የፋይናንስና የኦዲት አፈጻጸም መሻሻሉ ተገልጷል፡፡
አንድ መቶ ስልሳ ሰባት አዲስ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች መመዝገባቸውን፣ ለ 2462 የሲማድ ሰነድ ምርመራ ማካሄድ መቻሉን፣2352 ግብረ መልስ መስጠት፣የበጎ ፈቃደኝነትን እና የበጎ አድራጎት ባህልን ከማሳደግ አንጻር በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ መሰራቱ፤የንብረትና የፈንድ አስተዳድር ስራ በተመለከተ በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን እና ህግን ተላልፈው በተገኙ 55 የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ላይ በባለፉት ዘጠኝ ወራት ማስጠንቀቂያ ደብዳቤ መሰጠቱን የተቋሙ ስትራቴጂክ ጉዳዬች ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ካልኪዳን መንግስቴ ገልጸዋል፡፡ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ የተጀመሩ መልካም ስራዎችን ማስቀጠል ተገቢ መሆኑን አንስተው ተቋማዊ ለውጥ ስራ ግልጽነትና ተጠያቂነት አሰራርን ለማጎልበት አስፈላጊ በመሆኑ ሁሉም ስራ አስፈጻሚ በትኩረት ተፈጻሚ ማድረግ ይጠበቅበታል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
አያይዘውም ዲጂታላይዜሽን ስራ፣የሃብት አጠቃቀምን ማሻሻል እና በዘጠኝ ወራት ያልተከናወኑ ተግባራትን በቀሪ ወራት ትኩረት ተሰጥቶት መፈጸም ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡ ከዘጠኝ ወራት አፈጻጸም በተጨማሪ ተቋማዊ የለውጥ ስራ ሪፖርት ቀርቦ ዝርዝር ውይይት ተደርጎበታል፡፡