ተቋሙ የ2014 በጀት ዓመት አፈጻጸሙን እና የ2015 በጀት ዓመት እቅድ በማኔጅመንት ደረጃ እንዲሁም ከአጠቃላይ ሰራተኛ ጋር እየገመገመ ይገኛል፡፡ በበጀት አመቱ 587 አዲስ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች መመዝገባቸው፣ከክልሎችና ባለድርሻ አካላት ጋር ሞዴል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች መነሻ ህግ ተዘጋጅቶ ውይይት መደረጉና ክልሎች ህግ እንዲያመጡ ድጋፍ መደረጉ፣የሚሰጡ አገልግሎቶችን በመለየትና ሰራተኞችን በማሰልጠን የኢ-ሰርቪስ አገልግሎት መጀመሩ፣የዴስክ ኦዲት በማድረግ መረጃዎችን መያዝ መቻሉ፣በበጎ ፈቃድ አተገባበር ማንዋል መዘጋጀቱና ለሲ.ማ.ድ ድርጅቶች የማስተዋወቂያ መድረኮች መካሄዳቸው፣አገልግሎት አሰጣጣችንን ሊመዝን የሚችል ስታንዳርድ ተዘጋጅቶ ስራ ላይ መዋሉ በተጨማሪም አገልግሎት አሰጣጣችን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መሆኑ፣አገልግሎት አሰጣጣችንን ለማሻሻል እንዲቻል የመማክርት ጉባኤ በማቋቋም ስራ መጀመሩ፣ አቅምን ሊያሳድጉ የሚችሉ ስልጠናዎች ለሰራተኞች መሰጠቱ፣በፀደቁ መመሪያዎች ለሲቪል ማህበረሰሰብ ድርጅቶች ስልጠና መሰጠ፤በጎ ፈቃደኛንና በጎ ፈቃድ ፈላጊ ድርጅቶችን ሊያገናኝ የሚችል ሲስተም (VMIS) በልፅጎ ስራ ላይ መዋሉ፣ሁለተኛው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ቀን በደማቅ ሁኔታ መከበሩ፣የተለያዩ የበጎ ፍቃድ አገልግሎቶች የማስተባበርና የማከናወን ስራ መሰራቱ፣ የመማክርት ጉባኤ መቋቋሙ፣የአቅም ግንባታ ስራ ትኩረት አድርጎ መሰራቱ፣ ክልሎችን ያካተተ በዘርፉ የውጭ ሃገር ልምድ መወሰዱ እንዲሁም በሃገሪቱ በተከሰተው ጦርነትና ድርቅ ለተጎዱ ዜጎች የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን በማስተባበር ምላሽ መሰጠቱ በበጀት ዓመቱ ከተከናወኑ ተግባራት መካከል መሆናቸውን ወ/ሮ ቃልኪዳን መንግስቴ የእቅድ፣በጀትና ክትትል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ገልጸዋል፡፡
የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ በንግግራቸው እንደገለጹት በ2014 በጀት ዓመት እንደ ሃገር ብዙ ፈተናዎች የነበሩ መሆኑን አስታውሰው በዚሁ ሂደት በርካታ ተግባራትን በማከናወን ስኬት ያስመዘገብንበት ነው ብለዋል፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም አገልግሎት ሰጪ ተቋም እንደመሆናችን መጠን ስታንዳርድና ማንዋል፣የአሰራር ስርዓቶች ያስፈልጋሉ ይህንን ተግባራዊ አድርገናል ከዚህ በተጨማሪ እንደሃገር የተጀመረውን አዲስ መዋቅር አደረጃጀት መፈጸም፣የበጎ ፍቃድ ፖሊሲ እና ረቂቅ መመሪያዎችን የማጸደቅ፣የተጀመሩ ቋሚ መድረኮቻችን ማስቀጠል ትኩረት ሰጥተን የምንሰራቸው ጉዳዬች ይሆናሉ ሲሉ ተናግረዋል ፡፡ የተቋሙ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ በበኩላቸው በተቋሙ የተጀመረው የኦላይን አገልግሎት አጠናክሮ መቀጠል እና በተቋሙ Digitalization transformation ማረጋገጥ ቁልፍ ስራ ሆኖ መሰራት አለበት ብለዋል፡፡ ሌላው የዳግም ምዝገባ ሂደትን ማጠናቀቅ፣የእርስ በእርስ ቁጥጥርን ማጎልበት፣ለወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳይ በሁለተኛ ዙር ቃል የገቡ ድርጅቶችን በማስተባበር ጉዳቱ ለደረሰበት አከባቢ ተደራሽ እንዲሆን ማስቻል ትኩረት ሰጥን የምንሰራቸው ጉዳዬች ይሆናሉ ሲሉ ገልጸዋል፡፡
በተቋሙ የተከናወኑ ስራዎችን በተመለከተም በተለያዩ መንገዶች ለማህበረሰቡ ተደራሽ የማድረግ ስራ ተሰርቷል፡: በዚሁ ልክ ደግሞ የተወሰኑ ተግባራ ሳይከናወኑ የቀሩ በመኖራቸው እሱን በ2015 ዓ.ም አካተን መፈጸም አለብን ሲሉ መ፤ልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡