የሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ደይሬክቶሬት

ተግባርና ኃላፊነት

 • በኤጀንሲው ውስጥ የሴቶችና ወጣቶች እኩል ተሳታፊነትና ተጠቃሚነትለማረጋገጥ፣ እንዲሁም የህጻናት መብትና ደህንነትን ለማስጠበቅ የአሰራር ሥርዓትመዘርጋት፤
 • የተለያዩ ሰነዶችን ከሴቶችና ወጣቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት፣ እንዲሁም ከህጻናት መብትና ደህንነት አጠባባቅ አኳያ በመገምገምና ተገቢውን ግብአት በመስጠት ተግባራዊ እንዲሆን ማድረግ፣ ማስተባበር፤
 • ከመ/ቤቱ ተግባርና ኃላፊነት አኳያ በሴቶችና ወጣቶች ተጠቃሚነት እና ከሕጻናት መብትና ደህንነት በማስጠበቅ ዙሪያ የተለያዩ ጥናቶችና ምርምር ሥራዎችን ማካሄድ፣ ከሌሎች የሥራ ክፍሎች ጋር በጋራ በሚከናወኑ ጥናቶችም ላይ በባለቤትነት ማሳተፍ፤
 • ሴቶችና ወጣት ሰራተኞች በስራ ቦታ ከአደጋና ከጉልበት ብዝበዛ የሚጠበቁበት ሁኔታ እያጠና ተግባራዊ ማድረግ፤
 • ሴቶች፣ ህፃናት እና ወጣቶች ላይ የሚፈጸሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን መደገፍ፣ ማስተባበር፤
 • በመ/ቤቱ በተቋቋመው የህጻናት ማቆያ የሚገኙ ህጻናት በተዘጋጀው ስታንደርድ መሰረት ህጻናቱ ጤናቸውና ስብእናቸው ተጠብቆ በማቆያው ውስጥ እንዲቆዩ ለማድረግ የተመደቡ ባለሙያዎችን ማስተባበር፣ አስፈላጊ ባለሙያዎችና ቁሳቁሶች እንዲሟሉ ክትትል ማድረግ፣ እንዲሁም ባለሙያዎቹ ተገቢውን ስልጠና እንዲያገኙ ማድረግ፣
 • በመስሪያ ቤቱ ያሉ የሴት አደረጃጀቶችን አቅም ለማጐልበትና በቅንጅት ለመስራት የሚያስችል ስልት መቀየስ፣ ሲፈቀድም ተግባራዊ ማድረግ፣
 • ለሴት ሠራተኞች ፍላጐትን መሠረት ያደረገ የአጭርና የረጅም ጊዜ ሥልጠና በሴክተሩአመታዊ እቅድ ውስጥ እንዲካተት ማድረግ፤
 • ሴቶች፣ ህፃናት እና ወጣቶችን አስመልክቶ የተዘጋጁ ህጐች፣ ፖሊሲዎች፣ የአፈፃፀም ማኑዋሎች፣ የሥራ መመሪያዎች፣ ሀገራችን ስምምነት የገባችባቸው ዓለም አቀፍና አህጉራዊ ስምምነቶች ላይ ተከታታይ የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎች በመስሪያ ቤቱ ለሚገኙ አመራሮችና ባለሙያዎች ስልጠና መስጠት እንዲሁም ያስገኘውን ፋይዳ መገምገም፤
 • ሴቶች፣ ህፃናት እና ወጣቶች ጉዳይ ዙሪያ የግንዘቤ ማስጨበጫና የንቅናቄ ስራዎችን ማስተባበር፤
 • በፍላጐት ላይ የተመሰረተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ኘሮግራም ተከታታይነት ባለው መልኩ ለመሥራት እንዲቻል የዳሰሳ ጥናት ያካሂዳል፣በጥናቱ ግኝት መሰረት የአመለካከት ለውጥ ለማምጣት የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልቶችን ይቀይሳል፣ ሲፈቀድም ተግባራዊ እንዲሆን ማድረግ፤
 • በመ/ቤቱ ባሉ ዳይሬክቶሬቶች እና ስራ ክፍሎች የሚዘጋጁና የሚተገበሩ እቅድና ሪፖርት የሴቶችን፣ የህጻናትን እና ወጣቶች ጉዳይ ማካተታቸውን በመገምገም ደረጃውን የጠበቀ ወቅታዊ ግብረ-መልስ ማስተባበር እና
 • ሴቶች፣ ህፃናት እና ወጣቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማጐልበት፣ እንዲሁም የህጻናትን መብትና ደህንነት ለማስጠበቅ በመስሪያቤቱ የሚደረገውን ክትትል፣ ድጋፍና ሱፐርቪዥን ማስተባበር፡፡


የጥናት፣ ምርምርና ስርፀት ዳይሬክቶሬት

ተግባርና ኃላፊነት

 • የጥናት አካባቢዎች መለየት፣ ዕቅድ ማቀድ፣ ክትትል ማድረግ፤
 • በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ ውስጥ ያለውን አሰራር ለማዘመን የአገልግሎት አሰጣጥ ፈጣን እና ቀልጣፋ እንዲሆን ለማድረግ የሚያስችል ጥናት ማካሄድ፤
 • በጥናትና ምርምር በተገኙ ውጤቶች መሰረት የተለያዩ የአሰራር ለውጦችን ተከትሎ ማሻሻያዎች እንዲደረጉ ግብዓት ማቅረብ፤
 • የሲቪል ማሀበረሰብ ድርጅቶች አላማና የህብረተሰቡን ጥቅም የሚጎዳ የስጋት ምንጮችን በጥናት መለየት፤
 • የኤጀንሲውን ክፍተቶች በጥናት በመለየት የአሰራር ስርዓቱ እንዲሻሻል የጥናት ውጤት ለሚመለከተው ክፍል ማቅረብ፤
 • በፖሊሲ አፈጻጸም ላይ ያሉ የአሰራርና የአደረጃጀት ማነቆዎች ተለይተው እንዲጠኑና መፍትሄዎች እንዲቀርቡ ማድረግ፤
 • የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች እሴት ግንባታ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች መሰረታዊ ለውጥ በሚያመጣ፣ በተደራጀ ሁኔታ ለማስፈጸም የሚያስችል ጥናት ማድረግ፣
 • በኤጀንሲው፣ በክልል መንግስታት፣ በዘርፍ አስተዳደር እና በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ግንኙነትን የሚያጠናክሩ ጥናቶችን ያካሂዳል፣ የተገኙ ግኝቶች በስራ ላይ የሚውሉበትን መንገድ ማመቻቸት፤
 • የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የሚያፈሩት ሀብትና ንብረት (ፈንድ) ለማህበረሰቡ በተገቢው መንገድ ጥቅም ላይ መዋሉንና ተደራሽ መሆኑን የሚያመላክቱ ምርምርና ጥናታዊ ጽሁፎችን ማከናወን፤
 • በፌዴራልና በክልል የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች አስፈላጊነትና አወቃቀር ላይ የጋራ መግባባት ሊፈጥሩ የሚያስችሉ ሁኔታዎችን በጥናት መለየት፣
 • በሀገሪቷ ውሰጥ የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች ቁጥር፣ የሚንቀሳቀሱባቸው ክልሎችና የስራ ዘርፎች፣ የተጠቃሚው የህብረተሰብ ብዛት እና የአባሎቻቸው ቁጥር፣ የሚያንቀሳቅሱትን ሀብት፣ የድርጅቶች ፕሮጀክት ስርጭት እና ተያያዥ ጉዳዮችን ማጥናት፤
 • በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በየአካባቢው የሚሰሩ የልማት ስራዎች እንደየዘርፋቸው በጥናት መለየት፤
 • ኅብረተሰቡን ወደ ተጠቃሚነት የሚያመራ የመፍትሄ አቅጣጫዎች የሚያመለክት ጥናት ማቅረብ፤
 • በኤጀንሲው ስር የተካሄዱ ፕሮጀክቶች/ፕሮግራሞች ያስገኙት ጠቀሜታ /impact/ እንዲገመገም ማድረግ፤
 • የፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች አፈጻጸም የውጤታማነት ትንተና በማድረግ ለፖሊሲ ግብዓት የሚሆኑ ጉዳዮችን ይለያል፣ የውሳኔ ሀሳብ ማቅረብ፤
 • ለፖሊሲ አፈጻጸም ግምገማ ጥናት የሚያስፈልጉ መረጃዎች እንዲሰበሰቡና እንዲደራጁ ማድረግ፤
 • ለፖሊሲ ቀረጻና ምርምር የሚያስፈልጉ ጽሁፎች ተለይተው እንዲጠኑ መረጃዎች እንዲሰበሰቡና እንዲደራጁ ማድረግ፤
 • ለሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የሚሰጡ ልዩ ልዩ ድጋፎች ውጤታማ እንዲሆኑ ክፍተቶቹን ጥናት ማድረግ፤
 • ድርጅቶች የሚያከናውኗቸው የልማት ስራዎች መንግሰት ከሚያወጣቸው የልማት ዕቅዶች ጋር የተጣጣሙ እንዲሆኑ የሚያግዙ ጥናቶችን ማከሄድ፤
 • ድርጅቶቹ በሀገሪቷ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ፣ ሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ እና የልማት እንቅስቃሴ ያላቸውን ሚና አስመልከቶ ተገቢውን ጥናት የማድረግ ስራ መስራት፤
 • ከሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ጋር በተያያዘ ያሉ የኢኮኖሚ ሻጥሮችንና የሀብት ስወራዎች በሀገር ደረጃ ያላቸው ሥፋት፤ ጥልቀት እና ያስከተሉት ጉዳት ላይ ጥናት ማካሄድ እና
 • የተለዩ ዘርፎች በየትኛው የህበረተሰብ ክፍል ወይም ተቋም (መንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት) ሊከናወኑ/ሊደገፉ እንደሚገባ ማጥናት/መለየት፡፡


የምዝገባ፣ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት

ተግባርና ኃላፊነት

 • የሀገር በቀል ድርጅቶችን ለመመዝገብ የወጣውን አዋጅ፤ ደንብእና መመሪያዎች ላይ ያሉትን መስፈርቶች አሟልተው ሲቀርቡ መመዝገብና የምዝገባ ሰርተፍኬት መስጠት፤
 • የውጭ ድርጅቶችን ለመመዝገብ የወጣውን አዋጅ፤ ደንብ እና መመሪያዎች ላይ ያሉትን መስፈርቶች አሟልተው ሲቀርቡ የሲቪል ማህበሰብ ድርጅቶችን መመዝገብ እና የምዝገባ ሰርተፍኬት መስጠት፤
 • ህብረቶችን ለመመዝገብ በወጣው አዋጅ፤ ደንብ እና መመሪያዎች ላይ ያሉትን መስፈርቶች አሟልተው ሲቀርቡ መመዝገብ እና የምዝገባ ሰርተፍኬት መስጠት፤
 • የህብረቶች ህብረትን ለመመዝገብ የወጣውን አዋጅ፤ ደንብ እና መመሪያዎች ላይ ያሉትን መስፈርቶች አሟልተው ሲቀርቡ መመዝገብ እና የምዝገባ ሰርተፍኬት መስጠት፤
 • ለዘለቄታ በጎ አድራጎት እና አደራ በጎ አድራጎት ድርጅት አላማ የሚውል ንብረትና ሀብት መመዝገብ፣ ማረጋገጥ፣ የምስክር ወረቀት መስጠት፤
 • የበጎ አድራጎት ኮሚቴ ምዝገባን በተመለከተ አስፈላጊ መረጃዎች እንዲሟሉ በማድረግና እንዲፀድቅ ለሚመለከተው የበላይ አካል ማቅረብ፤
 • የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ሲዋሃዱ ወይም ሲከፋፈሉ ወይም ሲለወጡ ለመመዝገብ የወጣውን አዋጅ፤ ደንብ እና መመሪያዎች ላይ ያሉትን መስፈርቶች አሟልተው ሲቀርቡ መመዝገብ እና የምዝገባ ሰርተፍኬት መስጠት፤
 • የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች አስፈላጊውን መስፈርት አሟልተው ለምዝገባ ሲቀርቡ ስያሜያቸውንና ዓርማቸውን በጋዜጣ እንዲታወጅ ለፕሬስ ድርጅት ደብዳቤ መፃፍ፤
 • ለሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች አስፈላጊውን መስፈርቶች አሟልተው ሲቀርቡ የተለያዩ የድጋፍ ደብዳቤዎች መስጠት ማለትም /የቀረጥነፃ፣ የቫት ተመላሽ፣ የውጭ ዜጋ ስራ ፍቃድ፣ኮድ 35፣ የስራ አስኪያጅና ስራ አመራሮች ማረጋገጫ ደብዳቤ መስጠት፣ የባንክ ሂሳብ ቁጥር እንዲከፍቱ እና እንዲያንቀሳቅሱ ፍቃድ መስጠት እና እንደአስፈላገነቱ የገቢ ማስገኛና የህዝባዊ መዋጮ ድጋፍ ደብዳቤ መጻፍ፤
 • ለሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በአዋጅ፣ ደንብ እና መመሪያዎች ዙሪያ የህግ ምክር አገልግሎት መስጠት፤
 • የተሻለ አፈፃፀም ያላቸውን የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች መለየት፣ ማበረታታትና መሸለም፤
 • ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች መለየት እና እንደአስፈላጊነቱ ለበላይ አመራሩ ማቅረብ፤
 • ለሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በአዋጅ፣ ደንብ እና መመሪያዎች መሰረት ስልጠናዎችን መስጠት፤
 • የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የምዝገባ ሰርተፍኬት፣ መተዳደሪያ ደንብ እና ሌሎች ተያያዥ ሰነዶችን ማረጋገጥ፤
 • ከህግ ውጭ ለወንጀል ድርጊት አስበው የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ በማቅረብና ለሽብርተኝነት ዓላማ ለማዋል ተብሎ የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶችን በቅርበት በመከታተል የገንዘብ እና የንብረት ምንጩን የማጣራት ስራ መስራት፤
 • በማጣራት ሂደት የተገኙ መረጃዎችን መሰረት በማድረግ ህግ ተላልፈው በተገኙ አካላት ላይ ተገቢው እርምጃ እንዲወሰድ ከሚመለታቸው የመንግሰት አካላት ጋር በትብብር መስራት፤
 • የተለያዩ ሚዲያዎችንና ሌሎች ዘዴዎችን በመጠቀም ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ለሰብዓዊ ዕርዳታ ተብሎ የመጣ ገንዘብ ለሽብርተኝነት ተግባር እንዳይውል የግንዛቤ ማስጨበጫ መስራት፤
 • ማንኛውም የሲቪል ማኅበረሰ ብድርጅት ከየትኛውም ምንጭ የሚያገኘውን ገንዘብ ለኤጀንሲው እንዲያሳውቅ የማድረግ ስራ መስራት፤
 • ድርጅቶች በተፈራረሙበት የፕሮጀክት ስምምነት መሰረት ያቀዱትን ገንዘብ ስራ ላይ ማዋላቸውን ክትትል ማድረግ፤
 • ማንኛውም የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት የበጀት ዓመቱ ሲጠናቀቅ በውጭ ኦዲተር አስመርምሮ የሚያቀርበውን የየዓመቱን የኦዲት እና አመታዊ የስራ ክንውን ሪፖርት መገምገም፤
 • በኦዲት እና የስራ ክንውን ሪፖርት ላይ ያሉ አጠቃላይ ሂደቶች ዙሪያ ለድርጅቶች አጠቃላይ ግብረ መልስ መስጠት፤
 • በቀረቡት የኦዲት እና የስራ ክንውን ሪፖርት ላይ የህግ ጥሰቶች ሲያጋጥሙ እንደችግሩ ክብደት ከሚመለከተው የዘርፍ አስተዳደር ጋር በመነጋገር የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ ለሚመለከተው የበላይ ኃላፊ ከተገቢው መረጃ ጋር የውሳኔ ሀሳብ ማቅረብ፤
 • የሂሳብ ሰነዶቹ የሂሳብ አመቱ ካለቀ በኋላ ቢያንስ ለ5 ዓመት ተጠብቀው መቆየታቸውን ክትትል ማድረግ፤
 • የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የውስጥ አሰራራቸው ግልፀኝነትና ተጠያቂነት ባለ ውሁኔታ እያከናወኑ መሆናቸውን የራስ-በራስ አስተዳደር ስርዓትን በህጉ መሰረት ተግባራዊ ማድረጋቸውን ተገቢውን ክትትል ማድረግ፤
 • የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የሚያደርጓቸውን ለውጦች (የአድራሻ፣ የአመራር፣ የስያሜ…) ማሳወቃቸውን መከታተልና መመዝገብ፤
 • የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቱ መደበኛ ሪፖርት ማድረጊያ ጊዜው ከ 3 ወር በላይ ከቆየ የሲቪል ማህበረሰቡ ድርጅቱን በጋዜጣ ጥሪ በማድረግ የህልውና ማረጋገጥ ስራ መስራት፤
 • የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በአዋጅ፣ ደንብእና መመሪያዎች መሰረት ህጋዊ የባንክ ሂሳብ መክፈታቸውንና የገንዘብ እንቅስቃሴያቸውም በተከፈተው ህጋዊ የባንክ ሂሳብ መሆኑን ማረጋገጥ፤
 • ማንኛውም ድርጅት አግባብ ባለው ህግ መሰረት ከተገቢ የስራ ፍቃድ ውጭ የውጭ ሀገር ዜጎችን አለመቅጠራቸውን መከታተል፣ ማረጋገጥ፤
 • በድርጅቶቹ መደበኛ ደመወዝ ሳይከፈላቸው በሙያቸው በበጎ ፍቃደኝነት ከአንድ አመት ላልበለጠ ጊዜ ለማገልገል የሚመጡ የውጭ ሀገር ዜጎችን የድርጅቱን አላማ ለመደገፍ መምጣታቸውን ማረጋገጥ፤
 • ድርጅቶች በተቋቋሙበት አላማ መሰረት እየሰሩ መሆኑን ክትትልና  ቁጥጥርማድረግ፤
 • የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የገንዘብ እንቅስቃሴ የሚያሳይ ተቀባይነት ባለው የሂሳብ አሰራር በተዘጋጀ የሒሳብ መዝገብ እንዲይዙ መከታተል፤
 • የሂሳብ ሰነዶቹ የድርጅቱን ገቢና ወጪ፣ የወጪው ምክንያት፣ ሀብትና እዳ፣ የለጋሾችን ማንነትና የገቢውን ምንጭ ያካተተ ስለመሆኑ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፤
 • ኤጀንሲው ከመንግስት አካላት፣ ከለጋሽ ድርጅቶች ወይም ከህዝብ ከሚቀርብ ጥቆማዎች ወይም ኤጀንሲው ስራውን በሚያከናውንበት ወቅት ከሚገኙ መረጃዎች በመነሳት የህግ ጥሰቶች የማጣራት እና የመቆጣጠር ተግባር መስራት፣
 • የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ግልፀኝነትና ተጠያቂነትን ሊያረጋግጥ በሚችል መልኩ ብሎም የራስ አስተዳደር ስርዓት እንዲኖራቸው ክትትል በማድረግ ምቹ ሁኔታዎች እዲፈጠሩ ቡድኖችን ማደራጀት፤
 • የራስ አስተዳደር ስርዓታቸውን ለማጠናከር እንዲያስችል ለተቋቋመው የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ምክርቤት አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ፤
 • ከዘርፍ አስተዳደሮች ጋር ኤጀንሲው ኃላፊነቱን ለመወጣት ድርጅቶች ፕሮጀክት መፈራረማቸውን በመከታተል፣ በተፈረመው ፕሮጀክት መሰረት ስለመተግበራቸው ማረጋገጥ፣ ፕሮጀክቶቹ ሲጠናቀቁ ወይም ሲቋረጡ ሴክተሩን አስመልከቶ እንዴት ማስቀጠል እንዳለበት ሂደቱን ማመቻቸት፣ ተያያዥ ንብረቶችን በተመለከተ ተባብሮ መወሰን፣ የተለያዩ ተያያዥ ድጋፎችን መስጠት እንዲሁም የፕሮጀክቶች ጊዜ ሲጠናቀቅ የማጠቃለያ ግምገማ መደረጉን የማረጋገጥ ስራ መስራት፤
 • በዘርፉ ያሉ ምርጥ ተሞክሮዎችን መቀመር እንዲሁም የማስፋት ተግባራትን ማከናወን፤
 • የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በራሳቸው ፈቃድ እንዲሰረዙ ጥያቄ ሲያቀርቡ ወይም በህጉ መሰረት ለመሰረዝ የሚያበቁ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ የምዝገባ ሰርተፍኬታቸው እንዲሰረዝ የውሳኔ ኃሳብ ለበላይ አመራሩ ማቅረብ፤
 • የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የአፈፃፀም ደረጃ ለማወቅና ያጋጠማቸውን ችግሮች ለመፍታት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት ይሰራል፣ በወርክሾፕ፣ በሴሚናሮችና ተመሳሳይ ዝግጅቶች ላይ በመሳተፍ ተገቢውን ድጋፍ ማድረግ፡፡


የንብረት አስተዳዳርና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት

ተግባርና ሀላፊነት

 • የተቋሙን ንብረት ማስተዳደር፣ መምራት፣ ማስተባበር፣ መከታተልና ንብረቱ በአግባቡ ሥራ ላይ መዋሉን ማረጋገጥ፤
 • በተሸከርካሪ ስምሪት ወቅት ለሚደርሱ አደጋዎች በኢንሹራንስ ህጉ መሰረት ተፈጻሚ እንዲሆኑ ክትትል ማድረግ፤
 • የተሽከርካሪዎች አመታዊ የቴክኒክ ምርመራ እንዲደረግላችው ማድረግ፣ አስፈላጊው ሂደት ያላለፉትንም ተገቢው ጥገና ተደርጎላቸው ለምርመራ ብቁ እንዲሆኑ በበላይነት መምራት፣
 • አመታዊ የንብረት ቆጠራ ተግባራት መመርመር፣ መከታተል፣ መቆጣጠር፤
 • ንብረት የማስወገድ ተግባራትን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን እንዲከናወን ማድረግ፤
 • ጥገና ለሚያስፈልጋቸው የተቋሙ ቋሚ ንብረቶች ቅድመ ጥናት ማድረግ፤
 • ጥገና የሚያስፈልጋቸው የቢሮ መገልገያ ወንበሮች፣ ጠረጴዛዎች፣ የፎቶ ኮፒ ማሽኖች፣ የውሃና ኤሌትሪክ ብልሽቶች ወዘተ በቀረቡ የጥገና ጥያቄ መሰረት አስፈላጊው ጥገና መደረጉን መከታተል፤
 • ጥገና ለተከናወነባቸው የክፍያ ጥያቄዎች ሲቀርቡ አጣርቶ ለፋይናንስ የሥራ ክፍል ማቅረብ፤
 • በውል ሰነዱ መሠረት ጨረታ እንዲወጣ በማድረግ የውል ስምምነት እንዲዘጋጅ ማድረግ፤
 • የስልክ፣ የመብራትና የውሃ አገልግሎቶች በትክክል እየተሰጡ መሆኑንና ብልሽት ሲያጋጥም አስፈላጊው ጥገና ማድረግ፤
 • በመንግስት ተሸከርካሪዎች አጠቃቀም ደንብና መመሪያ መሠረት ለተሸከርካሪዎች የነዳጅ የኢንሹራንስና የተለያየ መኪና መለዋወጫ እቃዎች ግዥ የሚሆን በጀት እንዲያዝ ማድረግ፤
 • በተሸከርካሪዎች ስምሪት ወቅት ለሚደርሱ አደጋዎች በኢንሹራንስ ህጉ መሰረት ተፈጻሚ እንዲሆኑ ክትትል ማድረግ፤
 • በተያዘው በጀት መሰረት ግዥ እንዲፈፀም ክትትል ማድረግ፣ ንብረቶች በአግባቡ ስራ ላይ መዋላቸውን መቆጣጠር፤
 • የተሽከርካሪዎች አመታዊ የቴክኒክ ምርመራ እንዲደረግላችው ማድረግ፣ አስፈላጊው ሂደት ያላላፉትንም ተገቢው ጥገና ተደርጎላቸው ለምርመራ ብቁ እንዲሆኑ ማድረግ፤
 • በመ/ቤቱ የሚገኙ ተሸከርካሪዎች ከየስራ ክፍሎች የሚቀርቡ ጥያቄዎች መሰረት በማድረግ በአግባቡ የሥምሪት ሥራዎች መከናወናቸውን መቆጣጠር፤
 • የነዳጅና ቅባት ዕደላዎችና አጠቃቀም በመመሪያው መሰረት መፈጻማቸውን ማረጋገጥ፤
 • የመኪና ጥገና ውሎችን ከሚመለከት የሥራ ክፍሎች ጋር በመሆን የጥገናና ዕድሳት የውል ሰነድ ማዘጋጀት፤
 • የጥበቃ፣ የጽዳትና ውበት ሠራተኞች የሥራ ስምሪት ማድረግ፤
 • የጥበቃ፣ የጽዳትና ውበት ስራዎችን በአግባቡ መከናወናቸውን መከታተል እና
 • በበጀት አመቱ ለክፍሉ የሚያስፈልጉትን የደንብ ልብስ፣ የጽዳት እቃዎች በጀት መያዝ፣ አፈጻጸሙን መከታተል፣ በአግባቡ ስራ ላይ መዋላቸውን መቆጣጠር፡፡


የግዥ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት

ተግባርና ኃላፊነት

 • ከመስሪያ ቤቱ ስትራቴጂክ ዕቅድ በመነሳት የዳይሬክቶሬቱን እቅድ በወቅቱ አዘጋጅቶ ማቅረብ፣ ሲጸድቅም ስራዎችን ለቡድኖችና ለባለሙያዎች በማከፋፈል ተግባራዊ ማድረግ፤
 • የዳይሬክቶሬቱን ዓመታዊ በጀትና የሥራ መርሀ -ግብረ ማዘጋጀት፣ ማስተባበር፣ በስሩ የሚገኙ ባለሙያዎችንና ሠራተኞችን ማስተባበር፣ የሥራ አፈጻጸም መሙላት፣ ይገመግማል፣ የስልጠናና የቴክኒክ ድጋፍ ማድረግ፤
 • ተግባራት በታቀደላቸው ጊዜና ጥራት መከናወናቸውን መከታተል፣
 • አስፈላጊ የሆኑ የስራ መገልገያ መሳሪያዎችና የሰው ሀይል እንዲሟላማድረግ፣ ችግር ሲያጋጥም መፍትሄ መስጠት፤
 • ለውስጥና ለውጭ ተገልጋዮች የሚያስፈልጉት አገልግሎቶች በአግባቡ መሰጠታቸውን እና ቅሬታም እንዳይከሰት መከታተል፤
 • ከሚመለከታቸው የመንግስት አስፈጻሚ መ/ቤቶች በየጊዜው የሚተላለፉ መመሪያዎች ተፈጻሚነት እንዲያገኙ መከታተል፤
 • ለሂሣብ ስራ የተዘጋጁ ልዩ ልዩ ፎርማቶች፣ መዛግብቶችና ቼኮች በአግባቡ መያዛቸውንና ስራ ላይ መዋላቸውን ለማረጋገጥ የሚያስችል መቆጣጠሪያ ስልት መቀየስ፣ በትክክል በሥራ ላይ እንዲውሉ ማድረግ፣ መከታተል፣
 • የሂሳብ እንቅስቃሴ ምዝገባ በአግባቡ መከናወኑን መከታተል፣ ማረጋገጥ፤
 • በመንግስት ፣ በብድርና እርዳታ ገንዘብ የሚሸፈኑ ፕሮጅክቶችን ሂሳብ መከታተል፣መቆጣጠር፤
 • በተሰጠው የስልጣን ውክልና መሠረት የደመወዝና የሥራ ማስኬጃ ልዩ ልዩ የክፍያ ጥያቄዎች አስፈላጊነት በመመርመር እና ትክክለኛነት በማረጋገጥ የክፍያ ቼክና ማዘዣዎች በፊርማ ማጽደቅ፤
 • መ/ቤቱ በህግ በተሰጠው ኃላፊነት መሠረት የሚሰበሰቡ የምዝገባ፤ የፈቃድ እድሳት፤ የቅጣት እና ሌሎች ገቢዎች በአግባቡ መሰብሰባቸውንና በየዕለቱ ወደ ባንክ መተላለፋቸውን መከታተል፣ ማረጋገጥ፣
 • ሂሳብ በወቅቱ እንዲዘጋና በውስጥና በውጭ ኦዲተሮች እንዲመረመር ማድረግ፣ በኦዲት ሪፖርት ግኝት መሠረት መርሃ ግብር በማዘጋጀት የማስተካከያ እርምጃ መዉሰድ፤
 • በውጭ ኦዲተር የተመረመረውን ሂሣብ ከተሰብሳቢ እና ተከፋይ ሂሳብ መግለጫዎች ጋር በማያያዝ ለሚመለከተው አካል እንዲላክ ማድረግ፤
 • ለሥራ ማስኬጃ በሣጥን ሊያድር የሚገባውን ygNzB m-N bመመሪያው መሰረት መሆኑን መከታተል፤
 • በጥሬ ገንዘብና በባንክ ያለውን ሂሳብ በየጊዜው እየተከታተለ የመ/ቤቱን የገንዘብ አቅም እንዲታወቅ ማድረግ፤
 • ለመ/ቤቱ የሚቀርቡ የክፍያና የበጀት ጥያቄዎችን አግባብነት በማጣራት ለሚመለከተው ቡድን መሪ ወይም ባለሙያ መመምራት፣ አፈጻጸሙንም መቆጣጠር፤
 • በመ/ቤቱ ስም የሚገኙ የእርዳታና ብድር ገንዘቦች በሚደረጉ ስምምነቶችና የአሠራር ማንዋሎች መሠረት ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የሥራ ክፍሎች ጋር በመተባበር በሥራ ላይ እንዲውሉ ማድረግ፣ የአፈጻጸም ሪፖርት ማዘጋጀት፣ የምክር አገልግሎቶችን መስጠት፤
 • ግዥን ለመፈጸም የወጡ አዋጆች ደንቦችና መመሪያዎች በአግባቡ ስራ ላይ መዋላቸውን ማረጋገጥ፣
 • ለግዥ አገልግሎት የሚፈለገውን ተግባር በብቃት ለማከናወን የሚቻልበትን ከአድልኦ ነጻ የሆነ ግልጽና ተጠያቂነት ያለበት የአሰራር ስርዓት መዘርጋት፣ተፈጻሚ እንዲሆን ማድረግ፣
 • ከየስራ ክፍሉ የሚቀርቡ አስቸኳይ ግዢዎች በደንብና መመሪያ መሰረት እንዲገዙ ማድረግ፣
 • ለሚገዙ እቃዎች ተፈላጊው ዓይነት፣ የጥራት ደረጃና መጠን ዝርዝር መግለጫ እንዲወጣ፣ ማድረግ፣ የተገዛውም እቃ ትክክለኛና በወጣው ዝርዝር መግለጫ መሰረት መሆኑን መከታተል፤ ማረጋገጥ፣
 • በቡድን መሪው የተረጋገጠ የጨረታ ሰነዶችን በመመርመር በፊርማው አረጋግጦ ለአጽዳቂ ኮሚቴ መላክ፣
 • የግዢ ውል ሂደት በሚገባ መካሄዱን መቆጣጠር፣ ኮንትራታቸውን በአግባቡ የማይወጡትን በመመሪያ መሰረት እርምጃ እንዲወሰድ ማድረግ፣
 • በበላይ ኃላፊው በተሰጠው የገንዘብ ውክልና መጠን መሰረት ውል መፈጸም፣
 • የግዢ ጥያቄዎች ተሟልተው መቅረባቸውን በማረጋገጥ መፈረም፣
 • የግዢና የትራንዚት ስራዎች አስተማማኝ የመንግስት ግዥ አፈጻጸም መመሪያን ተከትሎ መከናወኑን መከታተል፣ ማስተባበር፣ መምራት፣
 • ልዩ ልዩ የሚያስፈልጉ እቃዎችና አገልግሎቶች በጥራትና በተመጣጣኝ ዋጋ በወቅቱ እንዲገዙ በበላይነት መምራት፣ ማስተባበር፣ መከታተል፣
 • በተለያየ ምክንያት ከታገዱ ተጫራቾች ግዢ እንዳይፈፀም መረጃ መያዝ፤ ስለ ግዢ እንቅስቃሴዎች የሚቀርቡትን የተለያዩ ዘገባዎችንና ስታትስቲካዊ የሪፖርት መግለጫዎች ማረጋገጥ፣
 • መ/ቤቱ የሚሰበስባቸውን ልዩ ልዩ ገቢዎች በወቅቱ መሰብሰባቸውንና ለሚመለከተው አካል ፈሰስ መሆናቸውን መከታተል፣ አረጋግጦ ማፀደቅ፡፡
 • የተለያዩ የመንግስት ግብርና ታክስ እና ሌሎች በተከፋይ የሚቀነሱ ሂሳቦችን ለሚመለከተው አካል በወቅቱ ገቢ መደረጋቸውን መከታተል፤
 • ከድጋፍ ሰጪ አካላት የሚገኙ ገቢዎች በወቅቱ መሰብሰባቸውን መከታተል፣ በመስሪያ ቤቱ የባንክ ሂሳብ ገቢ መደረጋቸውን ማረጋገጥ፤
 • መግለጫ የሚያስፈልጋቸው የሂሣብ ትራንዛክሽን መግለጫዎችን፣ ሂሳብ ሚዛንና ትንታኔ ማረጋገጥ፤
 • የመ/ቤቱን የሂሳብ ሪፖርት በየወሩ እንዲዘጋጅ በማድረግ አጣርቶ ለሚመለከተው የመንግስት አካል ማቅረብ፤
 • ሊሰበሰቡ የማይችሉ የተሰብሰቢ ሂሳቦች መረጃ ለበላይ አካል ማቅረብ፣ የውሳኔ ሃሳብ ሲደርሰውም ምዝገባ እንዲካሄድ ማድረግ፤
 • የባለመብቶች ክፍያ ሳይፈፅሙ የሚዘጉ ድርጅቶችን የሚገባቸውን ኪራይ፤የቤት እድሳት ወጪ፤ ደመወዝ፤ ጥቅማጥቅምና ሌሎች ክፍያዎችን የፋይናንስ ህግን ተከትሎ መዘጋጀቱን ማረጋገጥና ወጪ በማፅደቅ ክፍያ መፈፀሙን መከታተል፤
 • ድርጅቶች ሲዘጉ ንብረታቸውን ወደ መጋዘን ሲዘዋወር አስፈላጊ የሆኑ የአገልግሎት ግዥዎችን በህጉ መሰረት መፈፀማቸውን መከታተል፤
 • የተዘጉ ድርጅቶች ንብረቶች ሲሸጡ የጨረታ ሰነድ መሸጥና ገንዘቡን ለሚመለከተው አካል ገቢ ማድረግ፤
 • ከተዘጉ ድርጅቶች ንብረት በሽያጭ የተገኙ ገቢዎች ወደ ባንክ ገቢ መደረጋቸውን መከታተል
 • ከተዘጉ ድርጅቶች ጋር ተፈፅመው የነበሩ ውሎች ላይ ያሉ ግዥዎችና ክፍያዎችን መከታተል፤ ትክክለኛነቱን እና ህጋዊነቱን በማረጋገጥ ክፍያ እንዲፈፀም ማድረግ፤
 • በተዘጉ ድርጅቶች ስም በባንክ የነበሩ ገንዘቦች ወደ ኤጀንሲው የአደራ ሂሳብ ገቢ መደረጉን መከታተል፤
 • በተዘጉ ድርጅቶች ገንዘብ ወደ ኤጀንሲው የአደራ ሂሳብ ገቢ የተደረጉትን ስራ ላይ እንዲውል በበላይ አመራር እንዲከፈል ሲወሰን በውሳኔው መሰረት እዲፈፀም ማድረግ፡፡


የዕቅድ ዝግጅት፣ ክትትልና ግምገማ ደይሬክቶሬት

ተግባርና ኃላፊነት

 • የሥራ ክፍሉን የተለያዩ የሥራ ቡድኖችን ሥራ ማቀድ፣ ማስተባበር፣ መምራት፣ ውሳኔ በሚያሥፈልጋቸው ጉዳዮች ላይ ውሳኔ መስጠት፣
 • የሥራ ክፍሉን ወይም የሥራ ቡድኖችን የሥራ ውጤት መከታተል፣ መገምገም፣ የእርምት እርምጃ መዉሰድ፣ ግብረ መልስ መስጠት፤ የእቅድ አፈጸጻም ሪፖርት ለመሥሪያቤቱ የበላይ ኃላፊ ማቅረብ፣
 • የሥራ ቡድኖችንና ባለሙያዎችን የአቅም ክፍተት በማጥናት አቅማቸው የሚገነባበትን ሁኔታ ማመቻቸት፣
 • ለዳይሬክቶረቱና ለሥራ ቡድኖቹ የሚያስፈልጉ ግብአቶች እንዲሟሉ ማድረግ፣
 • የፖሊሲ ስትራቴጂና የፕሮግራም የፓኬጆችና የፕሮጀክቶች ሀሳቦች ማመንጨት፤ የዶክመንት ዝግጅትና ማሻሻል ሥራውን በመምራት የጸደቀ ዶክመንት ለሚመለከታቸው አካላት እንዲሰራጭ ማድረግ፣
 • ለዘርፉ ሥራ የሚያግዙ የህግ ማእቀፎችን፣ የሥራ መመሪያዎችን፣ ማንዋሎችን፣ ስነ-ስርዓቶችን እና መግለጫዎችን በአዲስ መልክ እንዲወጡና እንዲሻሻሉ ማድረግ፣ የሚዘጋጁትን ሰነዶች ለሚመለከታቸው አካላት እንዲሰራጩ ማድረግ፣
 • የሥራ ዘርፉንና የመሥሪያቤቱን ዕቅድ ዝግጅት፣ አፈጻጸምና የክትትልና ግምገማ ሥራዎች ሊያሻሽሉና ውጤታማ ሊያደርጉ የሚችሉ የጥናትና የምርምር ሥራዎች እንዲካሄዱ ሀሳብ ማመንጨት፤ማስተባበር፤ የጥናቱን ውጤት ተግባራዊ እንዲሆን ማድረግ፤ ፋይዳውን በመገምገም ሪፖርት ማቅረብ፣
 • የመሥሪያቤቱን ስትራቴጂክና አመታዊ እቅድ ማዘጋጀት፤ እንዲዘጋጅ ማድረግ፤ የክትትልና ድጋፍ፣ የግምገማና ግብረ መልስ ሥራዎችን በኃላፊነት መምራት፣ ማስተባበር፣ በበላይ ኃላፊው እያፀደቀ ሥራ ላይ እንዲውል ማድረግ፣
 • የእቅድ ዝግጅትና ሪፖርት፣ የበጀት ዝግጅት፤ የግምገማና እንዲሁም የለዉጥና መልካም አስተዳደር ግብረመልስ ሥራዎች ውጤታማና ቀልጣፋ እንዲሆኑ የአሠራር ስርዓቶችን መዘርጋት፣
 • የጸደቀው በጀት ለሥራ ክፍሎች በአግባቡ እንዲደለደል በማድረግ ያሳውቃል አፈጻጸሙን መከታተል፣ መገምገም፣ ግብረ-መልስ መስጠት፣
 • የተቋሙንና የዘርፉን የሥራ እቅድና አፈጻጸም የተሳካ ለማድረግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በሚደረገው ውይይትና አውደ ጥናቶች ላይ በመገኘት አስፈላጊ ግብአት መዉሰድ፤ ሥራ ላይ እንዲውል ማድረግ፣
 • የመሥሪያቤቱን የተለያዩ የሥራ ክፍሎች የእቅድ ዝግጅት ሥራን እና አፈፃፀምን መከታተል፣ መደገፍ፣ መገምገም፣ ግብረ መልስ መስጠት፤
 • የበጀት ዝውውር ጥያቄ ሲቀርብ አግባብነቱን በመመርመር የውሳኔ ሃሳብ ለበላይ ሃላፊው ማቅረብ ሲወሰንም ተግባራዊ እንዲሆን ማድረግ፤
 • የሥራ ክፍሉን ሥራ በተመለከተ ከመንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች የሥራ ግንኙነት  ማድረግ፣
 • ለበላይ አመራሩና ለተጠሪ ተቋማት ሥራውን በሚመለከት ሙያዊ የምክርና የድጋፍ አገልግሎት መስጠት፣
 • መሥሪያቤቱን በእቅድ አፈጻጸምና በጀት አጠቃቀም ላይ ለሚያጋጥሙ ችግሮች አማራጭ የመፍትሄ ሀሳብ በማመንጨት ለበላይ ኃላፊው ማቅረብ፣ ሲወሰን ተግባራዊ ማድረግ፣
 • የበጀት የዕቅድ ዝግጅትና ግምገማን እንዲሁም የለዉጥና መልካም አስተዳደር ስራዎችን የሚመለከቱ ምርጥ ተሞክሮዎችን መቀመር፤ ወደ ሌሎችም እንዲስፋፋ ማድረግ፤


የውስጥ ኦዲት ዳይክቶሬት

ተግባርና ኃላፊነት

 • የውስጥ ፋይናንስና ንብረት የኦዲት ሥራዎችን በአግባቡ መስራት፤
 • የውስጥ ክዋኔ ኦዲት መስራት፤
 • የኤጀንሲው ንብረት በአግባቡ መያዙን እና በቁጠባ ለተገቢው ስራ መዋሉን ማረጋገጥ፤
 • የተቋሙ የበጀት እንቅስቃሴ ህግን ተከትሎ በታቀደው መሰረት መፈጸሙን ማረጋገጥ፤
 • ለኤጀንሲው የተመደበው በጀት በፋይናንስ ህግ መሠረት ሥራ ላይ መዋሉን ማረጋገጥ፤
 • በንብረት አያያዝና በፋይናንስ አጠቃቀም ላይ የምክር አገልግሎት መስጠት፤
 • በመንግስት ሀብትና ንብረት ላይ ብክነት ሲደርስ እርምጃ እንዲወሰድ ማድረግ፤
 • የመስሪያቤቱ ሀብትና ንብረት ከማንኛውም ተገቢ ካልሆነ አሰራር፣ ማጭበርበርና ከሙስና ጋር ተያይዞ ከሚመጣ ጉድለት መጠበቅ፤ መከላከል፤
 • መስሪያቤቱ የዘረጋውን የውስጥ ቁጥጥር ስርአት ተግባራዊነት ይፈትሻል ያረጋግጣል፣ የማሻሻያ ሀሳብ ለበላይ አመራሩ ማቅረብ፤
 • ማንኛውም የሰነድና የሂሳብ ማስረጃዎች አስተማማኝና ወጥ የሆነ ሂሳብ አያያዝ ስርአት መኖሩን ማረጋገጥ እና
 • አፈጻጸሙን ለኤጀንሲውና ለገንዘብ ሚኒስቴር ሪፖርት ማቅረብ፡፡


የሰው ሀብት ልማትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት

 ተግባርና ኃላፊነት

 • በመንግሥት ሠራተኞች መመሪያዎችና ደንቦች መሠረት አደረጃጀት ላለው ተቋም  ልዩ ልዩ የቅጥር፣ የደረጃ ዕድገት፣ ዝውውር፣ የዲስፕሊን፣ የቅሬታ ማስተናገጃና ሌሎች አግባብነት ያላቸው  ኮሚቴዎች እንዲቋቋሙና ተግባራዊ እንዲሆኑ መከታተል፤
 • አዲስ ለሚቀጠሩ ሠራተኞች ስለ መንግሥት መመሪያዎችና ደንቦች እንዲሁም ተቋሙ ስለተቋቋመበትና ስለሚጠበቅበት ውጤት ስለ መሥሪያ ቤቱ ልዩ ልዩ የሥራ ክፍሎች ኃላፊነት የማስተዋወቂያ ስልጠና (`Induction) እንዲሰጥ በማድረግ ወደ ሥራ እንዲሰማሩ ማድረግ፤
 • ለዳይሬክቶሬቱ የሚያስፈልጉ ለአቅም ግንባታ ስራዎች፤ለትምህርት፤ ለህትመት፤ለግዥና ተያያዥ ተገቢውን በጀት በማስፍቀድ ተግባራዊ ማድረግ፤
 • የዳይሬክቶሬቱን ወቅታዊ የሥራ አፈጻጸም ለበላይ አካል ሪፖርት ማቅረብ፤
 • አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ አደረጃጀት ላለው ተቋም የሰው ሀብት ሥራ አመራርን የተመለከቱ የውስጥ መመሪያዎች እንዲወጡ፤ እንዲከለሱና አዳዲስ ጥናት እንዲጠኑ ማድረግ፣ የጥናት ውጤቶችን መገምገም፤
 • አደረጃጀት ላለው ተቋም ለሥራ መደቦች የሥራ ትንተና ተከናውኖ የሥራ ዝርዝር መግለጫ እንዲዘጋጅ ማድረግ፤
 • አደረጃጀት ላለው ተቋም ደረጃውን የጠበቀ የሰው ሃብት የሥራ አካባቢ ደህንነትና ጤንነት ጥበቃ ጥናቶች እንዲጠኑ ማድረግ፣ የተጠኑትን መገምገም፣ ለሚመለከተው አካል ማቅረብ፤
 • የኤንሲው ሰራተኞች ስራዎቻቸውን በአግባቡ ማከናወናቸውን መከታተልና ተገቢውን ጥናት ማካሄድ፤
 • መልካም ተሞክሮዎችን በመቀመር ዳይሬክቶሬቱ የሚመራበትን አዳዲስ አሰራሮች በመቀየስና በመገምገም የአሰራር ስርዓት መዘርጋት፤
 • የሰው ሀብት ሥራ አመራር የስምሪት ሥራዎች በደንብ እና መመሪያ መሠረት እንዲተገበሩ ማድረግ፤
 • የመንግሥት ሠራተኞች አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ ሰርኩላሮች እና አግባብነት ያላቸው መመሪያዎችን ተፈጻሚነታቸውን መከታተል፤
 • አደረጃጀት ላለው ተቋም ሜሪቲን የተከተለ የሰው ሀብት ምልመላና መረጣ እንዲከናወን ማድረግ፤
 • የኤጀንሲውን ሰራተኞች ልዩ ልዩ ጥቅማጥቅሞችና አገልግሎቶች አሰጣጥ ሳይዛቡ ሥራ ላይ እንዲውሉና በወቅቱ ተግባራዊ እንዲሆን ማድረግ፤
 • የሠራተኛ የግል ማህደሮችና ማንኛውንም ሰራተኛን የሚመለከቱ መረጃ ተሟልተውና ዘመናዊ ሆነው እንዲያዙ ክትትል ማድረግ፤
 • የሰው ኃይል እቅድ መረጃዎች እንዲሰበሰቡ፣ እንዲደራጁ ተተንትነው እንዲጠናቀሩ ያደርጋል፣ የመረጃዎችን ትክክለኝነት ያረጋግጣል፣ ለሚመለከተው አካል ያስተላልፋል፤
 • በደረጃው ለተፈቀዱ የስራ መደቦች የሰው ኃይል ስምሪት ፈተናዎችን ያዘጋጃል፣ በሚመለከታቸው የስራ ክፍሎችም እንዲዘጋጁ ያደርጋል፣ ይፈትናል፣ እንዲፈተኑ ያደርጋል፣ ያርማል፣ እንዲታረሙ ማድረግ፣መረጃዎቹን በዘመናዊ የመረጃ ዘዴ /በሃርድና በሶፍት ኮፒ/ ተደራጅተው እንዲያዙ ማድረግ፤
 • በዳይሬክቶሬቱ ስር የሚገኙ ሰራተኞች በባለቤትነት ስሜት እንዲሰሩና ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት እንዲሰጡ ያለባቸውን የአፈጻጸም ክፍተት ይለያል፣ እንዲበቁ ማድረግ፤
 • ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች በሰው ሃብት ሥራ አመራር ዙሪያ ለሚቀርቡ ማብራሪያዎች ህጉን መሠረት በማድረግ ማብራሪያና ምላሽ ይሰጣል ተገቢውን ሙያዎ ድጋፍ ማድረግ፤
 • በስነ-ምግባር ጉድለት ምክንያት በተከሰቱ ችግሮች ላይ የተወሰዱ ዕርምጃዎችን መከታተል፤
 • ለመ/ቤቱ ተስማሚ የሆኑ ዘመናዊ የለውጥ ሥራ አመራርና የአሠራር ማሻሻያ ስልቶች ተለይተው እንዲቀርቡ ማድረግ፤
 • የለውጥና መልካም አስተዳደር ሥራዎች ቀጣይነትን የሚያረጋግጡ አዳዲስ የአሠራር ስርዓቶች በማጥናት፣ ምርጥ ተሞክሮዎችን በመቀመር ለመ/ቤቱ ጠቃሚ የሆኑትን ተግባራዊ ማድረግ፤
 • የሥራ ዘርፉን የአሰራር ችግሮች በመለየትና በማጥናት ምቹ የአሰራር ሂደት እንዲኖር ማድረግ፤
 • በተግባር ላይ እንዲውሉ የተመረጡ የለውጥና መልካም አስተዳደር ሥራዎች አተገባበር ከሁኔታዎች ጋር ተጣጥመው እንዲሰራባቸው ማድረግ እንዲሁም ስራ ላይ ማዋል፤
 • በመ/ቤቱ የሚገኙ የሥራ ዘርፎች በአስቀመጡት የለውጥና መልካም አስተዳደር ሥራዎች ግቦች እና እቅድ መሠረት መፈጸማቸውን ክትትል በማድረግ ለዳይሬክቶሬቱ ማቅረብ፤
 • በመ/ቤቱ የመልካም አስተዳደር ሥርዓት መስፈኑን መከታተል፤
 • በለውጥ አፈጻጸም ላይ የሚያጋጥሙ የአሠራር ችግሮችን በመለየት ማቅረብ፤
 • በመ/ቤቱ ተግባራዊ የሆኑ የለውጥና መልካም አስተዳደር ሥራዎች ያስገኙት ፋይዳ መከታተል፤
 • በሥራ ላይ እንዲውሉ ውሳኔ ያገኙ ልዩ ልዩ የጥናት ሰነዶች ተግባራዊ እንዲሆኑ ለተጠቃሚ ክፍሎች ማስተላለፍ፤
 • የለውጥና መልካም አስተዳደር ሥራዎች ከአፈጻጸም አኳያ ለመገምገም በተዘጋጀ ሪፖርት አቀራረብ ስርዓት ስለመቅረቡ መከታተል እና
 • የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ስለለውጥ 1. ዓላማዎች እንዲገነዘቡና የህዝብ አገልጋይነት ስሜት እንዲያዳብሩ የአመለካከት ለውጥ እንዲያመጡ ተከታታይነት ያላቸው የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች እንዲዘጋጁ ማድረግ፡፡


የለዉጥና መልካም አስተዳደር ቡድን

ተግባርና ኃላፊነት

 • የቡድኑን ዓመታዊ እቅድ ያዘጋጃል፣ አፈጻጸሙን ይገመግማል፣ ቡድኑን መምራት፤
 • ቡድኑን በአስፈላጊ ግብአቶች ያደራጃል፣ ምቹ የሥራ ሁኔታዎችን እንዲፈጥሩ ማድረግ፣
 • በስሩ ያሉ ሠራተኞችን መምራት፣ መቆጣጠር፣ ማስተባበር፣
 • የሠራተኞችን የሥራ አፈጻጸም መገምገም፣ ውጤታማ የሆኑ ሠራተኞችን ማበረታታት፣ የአቅም ክፍተት ያለባቸውን ሰራተኞች በመለየት ልዩ ድጋፍ እንዲያገኙ ማድረግ፣
 • የቡድኑን የአሠራር ችግሮች በመለየትና በማጥናት ምቹ የአሰራር ሂደት እንዲኖር ማድረግ፣ ተፈጻሚነቱን ማረጋገጥ፣
 • ወቅታዊ የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ማዘጋጀት፣ ለኃላፊው ማቅረብ፣
 • ሊተገበሩ በእቅድ የተያዙ የለውጥ መሳሪያዎችን ተግባራዊ ለማድረግ የሚረዳና ውጤታማነትን የሚያሰፍኑ የአፈጻጸም መመሪያዎችን ማዘጋጀት፣ ማስተባበር፣ መርሆዎችንና ንድፈሃሳቦችን የተከተሉ መሆኑን ማረጋገጥ፣ ለኃላፊው ማቅረብ፣
 • በተግባር ላይ እንዲውሉ የተመረጡ የለውጥ መሳሪያዎች አተገባበር ከሁኔታዎች ጋር ተጣጥመው ስለሚሄዱበት ማጥናት፣ ለኃላፊው ማቅረብ፣
 • ለሥራ ዘርፎች ግብአት የሚሆኑ የለውጥ ሃሳቦችን በማመንጨት ለመ/ቤቱ ተስማሚ የሆኑ ዘመናዊ የለውጥ ሥራ አመራርና የአሠራር ማሻሻያ ጥናቶችን ማጥናት፣ ለኃላፊው ማቅረብ፣
 • ልዩ ልዩ የማሻሻያ ሃሳብ ጥያቄዎች ሲቀርቡ አግባብነታቸውን እያጠና ለውሳኔ ለኃላፊው ማቅረብ፣
 • የመልካም አስተዳደር ስርዓት እንዲሰፍን ተቋማዊ የለውጥ ምርጥ ተሞክሮዎችመቀመር፣
 • ከሁኔታዎች ጋር በማገናዘብ እንዲስፋፋ ማድረግ፤
 • የሥራ ውጤታማነትን የሚያሻሽሉ የለውጥ መሳሪያዎች፣ ስታንዳርዶች፣ የአሰራር ዘዴዎች፣ ልዩ ልዩ ጥናቶች ውሳኔ ሲያገኙ በመ/ቤቱ በተገቢው ሁኔታ ስለመተግበራቸው ክትትል ማድረግ፣ አፈጻጸሙን እየገመገመ ለኃላፊው ማቅረብ፣
 • በመ/ቤቱ ተግባራዊ የሆኑ የለውጥ መሣሪያዎች ያስገኙትን ፋይዳ በመገምገም ለኃላፊው ማቅረብ፣
 • የለውጥ ሥራዎች ዕቅድና ፕሮግራሞች አተገባበር ላይ ያጋጠሙ ችግሮችን በማጥናትና በመገምገም የመፍትሄ ሃሳብ ማቅረብ፣
 • የለውጥ መሳሪያዎችን በመጠቀም የሚካሄዱ ለውጦች ላይ ሙያዊ ምክር፣ እገዛና ድጋፍ ለስራ ዘርፎች መስጠት ወይም እንዲያገኙ ማድረግ፣
 • ተቋማዊ ለውጥን በቀጣይነት ለመተግበር እንዲቻል የክህሎት፣ የአቅርቦት የአመለካከት ክፍተቶችን መለየት፣ መከታተል፣
 • የሥራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ስለለውጥ ዓላማዎች እንዲገነዘቡና የህዝብ አገልጋነት ስሜት እንዲያዳብሩ ተከታታይነት ያላቸውን የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች በማዘጋጀት የፈጻሚዎችን አቅም እንዲጎለብት ማድረግ፣
 • በአፈጻጸም ላይ የሚያጋጥሙ/ የሚታዩ ጥንካሬና የአሰራር ክፍተቶችን እያጠና የማሻሻያእርምጃ እንዲወሰድ በጥናት የተደገፈ ሃሳብ ለኃላፊው ማቅረብ፣ ስለአፈጻጸሙ ክትትል እና ድጋፍ ማድረግ፣
 • ከመሥሪያ ቤቱ አጠቃላይ ዕቅድ በመነሳት የስራ ዘርፎች ተቋማዊ የለውጥ ሂደትን በየስራ ዘርፋቸው የሚተገብሩበትና የተገኘውን ውጤት የሚገመግሙበት የአሰራር ባህል እንዲሰርጽ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፣
 • የለውጥ ስራዎች በወጣ እቅድን የሥራ መርሃ ግብር መሰረት መከናወኑን መቆጣጠር፤ ማረጋገጥ፣


የስነ-ምግባር መከታተያ ቡድን

ተግባርና ኃላፊነት

 • በተቋሙ ውስጥ ለሙስናና ብልሹ አሰራር ክፍተት የሚፈጥሩ ጉዳዮችን ለመለየት የሚያስችሉ ጥናቶችን ማካሄድ፤ መለየት፤
 • ከሌሎች የሥራ ክፍሎች ጋር ያለውን ቅንጅት እና ትስስር በማጥናት የተጠናከረና ተመጋጋቢነት ያለው የስራ ግንኙነት እንዲፈጠር ሁኔታዎችን ማመቻቸት፤ አፈጻጸሙን መከታተል መደገፍ፤
 • የአሰራር ክፍተቶችን ሊያሟላ የሚችል ተቋማዊ ረቂቅ የስነ-ምግባርና የብልሹ አሰራር ማንዋል ማዘጋጀት፤
 • ከስነ-ምግባር ጉድለትና ከሙስና ጋር በተያያዘ የጥቆማ የአቅራቢዎች ሚስጢራዊነት ሊያረጋግጥ የሚችል የአሰራር ስርዓት ማዘጋጀት፤
 • የስነ-ምግባር ተግባራትን የሚያጎለብቱ አሰራሮችን ሊያሻሽሉ የሚችሉ ጉዳዮች ላይ በየወቅቱ ጥናት ማካሄድ፤ ለሚመለከተው አካል ማቅረብ፤
 • የተቋሙን ሰራተኞች የስነምግባር አስተሳሰባቸውን ሊያጎለብቱ የሚችሉ የስልጠና ሰነዶችን ማዘጋጀት፤ ስልጠና መስጠት፤
 • በተቋሙ የስነ-ምግባርና የጸረ-ሙስና የአሰራር ማንዋልና የመተዳደሪያ ደንብ(Code of Conduct) ማዘጋጀት፤ ስልጠና መስጠት፤
 • ሀገር አቀፍ የስነ-ምግባርና የጸረ-ሙስና ፖሊሲዎች፣ ደንቦች እና መመሪያዎች ዙሪያ ለተቋሙ ሰራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን መስጠት፤
 • በተቋሙ ውስጥ ሃብታቸውንና የገንዘብ ጥቅማቸውን እንዲያስመዘግቡ የህግ ግዴታ ለተጣለባቸው ሰራተኞችና ሃላፊዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በመስጠት ሀብታቸውን በአግባቡ እንዲያስመዘግቡ ማድረግ፤ በአግባቡ መመዝገብ፤
 • የስነ-ምግባር ተግባራትን የሚያጎለብቱ ተሞክሮዎችን መቀመር፤ ማስፋፋት፤ አሰራሮችን በየወቅቱ ማሻሻል፤
 • የተቋሙ የስነ-ምግባርና የጸረ-ሙስና የአሰራር ማንዋልና የመተዳደሪያ ደንብ(Code of Conduct) እንዲሁም የሀገሪቱ የስነ-ምግባር የጸረ-ሙስና ህጎችና መመሪያዎች በተቋሙ ውስጥ መከበራቸውን መከታተል፤
 • በክትትል ወቅት የተገኙ የአሰራር ክፍተቶች በመለየት የመፍትሄ ሃሳብ ለሃላፊው ማቅረብ፤
 • በስነ-ምግባርናበጸረ-ሙስና ፖሊሲዎች፣ ደንቦችና መመሪያዎች ዙሪያ የተሰጡ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎች ያመጡትን ለውጥ መከታተል፤
 • ሠራተኞች የሚያቀርቧቸውን የስነ-ምግባር ችግሮችና ማንኛውም ደንብና መመሪያ ጥሰት ጥቆማዎችን ተቀብሎ ምርመራ ማድረግ፤ የማስተካከያ እርምጃ በመለየት ለውሳኔ ሃላፊው ማቅረብ እና
 • በስነ-ምግባር ጉድለት ምክንያት በተከሰቱ ችግሮች ላይ የተወሰዱ ዕርምጃዎችን መከታተል፡፡