የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህግ ማንዋል
የሲቪል ማህበረሰብ
ድርጅቶች የህግ ማንዋል
ጥቅምት 2012
አገራችን ኢትዮጵያ ሀገር ዐቀፍ እና መጠነ ሰፊ የሆነ የለውጥ ሂደት የጀመረች ሲሆን ይህም ለውጥ በሕብረተሰቡ ማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ህይወት ላይ እንዲሁም በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ላይ አዎንታዊ የሆነ ለውጥን አምጥቷል፡፡ ለዚህም እንደ ማሳያ ሊጠቀስ የሚገባው መንግስት በለውጡ ማግስት ጊዜ ሳያጠፋ ኢትዮጵያባለፉት አመታት ካፀደቀቻቸው አሳሪ ህጎች መካከል አንዱ የሆነውን የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት አዋጅ 621/2001 በመሻር አዲስ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ 1113/2011 ማውጣቱ ነው፡፡ አዲሱ ህግ ሲቀረፅም በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ሥር በተደራጀው የህግና ፍትህ ጉዳዮች አማካሪ ም/ቤት ሥር በተደራጀው ገለልተኛ የህግ ባለሙያዎች ቡድን አማካኝነት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላትን በሰፊው ያሳተፈና አዋጁ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጥር 28 ቀን 2011 ከመፅደቁ በፊት ጥልቅ ውይይት የተደረገበት ነበር፡፡
የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር ፩ ሺ ፩፻፲፫/፪ ሺ ፲፩
ፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ
አዋጅ ቁጥር ፩ሺ፩፻፲፫/፪ሺ ፲፩ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ
የካቲት ፳፰ ቀን ፪ሺ፲፩
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት እንዲሁም ኢትዮጵያ በተቀበለቻቸው ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ስምምነቶች የተረጋገጠውን የመደራጀት መብት በተሟላ መልኩ ተግባራዊ ለማድረግ ሕግ ማውጣት በማስፈለጉ ፤ የመደራጀት መብት በሕገመንግሥቱ የተረጋገጡ ሌሎች መብቶችን ለማስከበር ያለውን ፋይዳ በመገንዘብ፤
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ ኢኮ ኮርፖሬሽን ኢትዮጵያ (ICCO corporation Ethiopia) ከተባለ ግብረሰናይ ድርጅት ጋር የፕሮጀክት ስምምነት ተፈራረመ ፡፡
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ ኢኮ ኮርፖሬሽን ኢትዮጵያ (ICCO corporation Ethiopia) ከተባለ ግብረሰናይ ድርጅት ጋር የፕሮጀክት ስምምነት ተፈራረመ ፡፡
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ መሰረቱን ኔዘርላድ ካደረገው ኢኮ ኮርፖሬሽን ኢትዮጵያ (ICCO corporation Ethiopia) ከተባለው ግብረሰናይ ድርጅት ጋር በአምስት ክልሎች ለሚተገበሩ ስምንት ፕሮጀክቶች የመግባቢያ ስምምነት የተፈራረመ ሲሆን ፕሮጀክቶቹ በአማራ ፣ኦሮሚያ፣ በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች፣ በሶማሌ እና በአፋር ክልሎች የሚተገበሩ ናቸው፡፡
በፊርማ ስነስርዓቱ ላይ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ ለተቋሙ እንዲህ ያለ ስምምነት የመጀመሪያ መሆኑን አንስተው ኤጀንሲው ፕሮጀክቱ ሲጠነሰስ ጀምሮ አሁን እሲኪደርስ የበኩሉን ተሳትፎ ያደረገ መሆኑን አንስተዋል፡፡
አያይዘውም ምንም እንኳን መጀመሪያ ላይ ፕሮጀክቱ በሌላ አካል እንዲመራ ፍላጎት የነበረ ቢሆንም ለሀገር ከሚሰጠው ጥቅምና በተለያዩ ክልሎች የሚተገበር ከመሆኑ የተነሳ እንዲሁም እሳቤው የሚያነሳሳና አካታች ከመሆኑ አንጻር በፕሮጀክቶቹ ላይ ኤጀንሲው የበኩሉን አስተዋጽኦ ቢያደርግ ለሀገር የበኩሉን ያበረክታል በሚል ይህን ስምምነት ልናደርግ ችለናል ብለዋል፡፡
በመጨረሻም ድርጅቱ ከኤጀንሲው ጋር ለመስራት በመፍቀዱ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
የኢኮ ኮርፖሬሽን ኢትዮጵያ (ICCO corporation Ethiopia) ካንትሪ ዳይሬክተር አቶ ደስታ ዳመነ በበኩላቸው ተቋማቸው በድርቅና በተለያዩ የተፈጥሮ አደጋዎች ለሚጠቁና የምግብ ዋስትናቸው በጣም ችግር ውስጥ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችን ለመርዳት የሚንቀሳቀስ መሆኑን ጠቁመው ድርጅታቸው በቀጥታ ፕሮጀክቶችን ፈጻሚ ሳይሆን በስሩ ላሉት ከ13 በላይ ፈጻሚ ለሆኑ ድርጅቶች ፈንድ የሚያደርግ ድርጅት መሆኑን ገልፀዋል፡፡
አያይዘውም ይህ ፈንድ ሪሴት ፕላስ ኢኖቬሽን ፈንድ (RESET PLUS INNOVATION FUND) ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ከአውሮፓ ህበረት የተገኘ ፈንድ መሆኑን ጠቁመው አዳዲስ የአሰራር ስርዓቶችን በመዘርጋት የተፈጥሮ አደጋዎችን ለመቋቋም የሚያስችል ፕሮጀክት ነው ብለዋል፡፡
ኤጀንሲው በርካታ ባለድርሻ አካላትን ያቀፈ በመሆኑና ፈንዱ ድጋፍ የሚያደርጋቸው ፕሮጀክቶች ስኬታማነታቸው ታይቶ በሀገር አቀፍ ደረጃ ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ በመሆናቸው ኤጀንሲው ድጋፍና ክትትል እያደረገ በመንግስትም ሆነ በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እየተወሰደ ለሰፊው የማህበረሰብ ክፍል በተለይም በተፈጥሮ አደጋዎች ለተጎዱ የማህበረሰብ ክፍሎች ተደራሽ እንዲሆን ይረዳል የሚል እምነት እንዳላቸው ካንትሪ ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡
ኢኮ ኮርፖሬሽን (ICCO corporation Ethiopia) በኔዘርላንድ ሀገር መሰረቱን ያደረገና እ.ኤ.አ ከ1964 እ.ኢ.አ ጀምሮ የሰብዓዊ ድጋፍ አየሰጠ የቆየ ድርጅት ሲሆን በኢትዮጵያ ላለፉት 35 አመታት በምግብ ዋስትና፣ በጤናና በትምህርት ሴክተሮች ላይ ተሳትፎ አያደረገ ያለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ነው፡፡
ከ2015 እ.ኢ.አ ጀምሮ በኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ቢሮ ከፍቶ እየተንቀሳቀሰ የሚገኝ መሆኑን ከድርጅቱ የኢትዮጵያ ተወካይ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡


