በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን አዘጋጅነት ከሩስያ የመጡ የሲቪል ብሪክስ ፎረም ሰብሳቢዎች ከባለስልጣኑ ተወካዮችና ከኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ተወካዮች ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን የብሪክስ ሲቪል ፎረም ዓላማና አሰራርን እንዲሁም በኢትዮጵያ ተሳትፎ ዙሪያ ግንዛቤ የሚፈጠሩ ጉዳዮች ዙሪያ ሃሳቦች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
May be an image of 9 people, dais and textበፎረሙ ላይ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ፣ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ዶ/ር ንጉሱ ለገሰ እንዲሁም በጤናና አካባቢ ጥበቃ ላይ የሚሰሩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ተወካዮች የተገኙ ሲሆን ከብሪክስ ሲቪል ፎረም በኩል የፎረሙ ሰብሳቢ ዶ/ር ቪክቶሪያ ፓኖቫ እና ልዑካቸው ተሳታፊ ሆነዋል:: የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል ከመሆኗ ጋር ተያይዞ በሁሉም ዘርፎች የሀገሪቱን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ በንቃት ተሳትፎ እያደረገች መሆኑን ገልፀው በብሪክስ ሲቪል ፎረምም በንቃት ተሳትፎ በማድረግ የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን በማጠናከር የሀገሪቱን ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማሳደግ የሚያስችሉ ስራዎች እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡ አቶ ፋሲካው ሞላ በፎረሙ ላይ በኢትዮጵያ ያለውን የሲቪል ማህበራት አስተዳደር በተመለከተ ዝርዝር ማብራሪያ ለልዑኩ ያቀረቡ ሲሆን ብሪክስ ሲቪል ፎረም ለኢትዮጵያ ሲቪል ማህበራት አዲስና ተደማሪ/ተጨማሪ አጋር እንዲያገኙ በማድረግ፤ በመንግስት፣ በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እና በግሉ ዘርፍ ያለውን ትስስር በማጠናከር፤ የተለያዩ የልምድ ልውውጥ እድሎች በመፍጠር ዘርፉን በማሳደግ፤ የብሪክስ ዋና ዓላማ ውስጥ አንዱ የሆነውን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን በማጎልበት፤ እና ፕሮጀክቶችን በጋራ በመተግበር የአገርና የህዝብን ተጠቃሚነትን ለማሳደግ ጉልህ ጠቀሜታ ያለው መሆኑን በመጠቆም በብሪክስ ማዕቀፍ ውስጥ  በትኩረት መንቀሳቀስ እንደሚገባ አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡
በፎረሙ የብሪክስ ከፍተኛ ባለሙያዎች ካውንስል ሃላፊ እና የብሪከስ ሲቪል ፎረም ሰብሳቢ ዶ/ር ቪክቶሪያ ፓኖቫ ብሪክስን በሚመለከት በሰጡት ማብራሪያ በተለይም ብሪክስ ቅድሚያ በሚሰጣቸው የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ትኩረት ሰጥተው አብራርተዋል፡፡ ዶ/ር ቪክቶሪያ ፓኖቫ ብሪክስ ሲቪል ፎረም በኢትዮጵያና በብሪክስ አባል አገራት መካከል አዲስ የትብብር ምእራፍ የሚከፍት መሆኑን በማንሳት ወፊትም በቅርበት ከኢትዮጵያ ጋር የሚሰሩ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በፎረሙ ተሳታፊ የሆኑ የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበራት አመራሮች ስላከናዎኗቸው ተግባራትና በቀጣይ መኖር ስለሚገባው የትብብር ማዕቀፎች በሚመለከት ገለፆዎችን ያቀረቡ ሲሆን ፎረሙ ከብሪክስ አባል አገራት ድርጅቶችና አጋሮች ጋር ትስስር ለመፍጠር እድል የሚሰጥ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡