የግዥ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት
ተግባርና ኃላፊነት
- ከመስሪያ ቤቱ ስትራቴጂክ ዕቅድ በመነሳት የዳይሬክቶሬቱን እቅድ በወቅቱ አዘጋጅቶ ማቅረብ፣ ሲጸድቅም ስራዎችን ለቡድኖችና ለባለሙያዎች በማከፋፈል ተግባራዊ ማድረግ፤
- የዳይሬክቶሬቱን ዓመታዊ በጀትና የሥራ መርሀ -ግብረ ማዘጋጀት፣ ማስተባበር፣ በስሩ የሚገኙ ባለሙያዎችንና ሠራተኞችን ማስተባበር፣ የሥራ አፈጻጸም መሙላት፣ ይገመግማል፣ የስልጠናና የቴክኒክ ድጋፍ ማድረግ፤
- ተግባራት በታቀደላቸው ጊዜና ጥራት መከናወናቸውን መከታተል፣
- አስፈላጊ የሆኑ የስራ መገልገያ መሳሪያዎችና የሰው ሀይል እንዲሟላ ማድረግ፣ ችግር ሲያጋጥም መፍትሄ መስጠት፤
- ለውስጥና ለውጭ ተገልጋዮች የሚያስፈልጉት አገልግሎቶች በአግባቡ መሰጠታቸውን እና ቅሬታም እንዳይከሰት መከታተል፤
- ከሚመለከታቸው የመንግስት አስፈጻሚ መ/ቤቶች በየጊዜው የሚተላለፉ መመሪያዎች ተፈጻሚነት እንዲያገኙ መከታተል፤
- ለሂሣብ ስራ የተዘጋጁ ልዩ ልዩ ፎርማቶች፣ መዛግብቶችና ቼኮች በአግባቡ መያዛቸውንና ስራ ላይ መዋላቸውን ለማረጋገጥ የሚያስችል መቆጣጠሪያ ስልት መቀየስ፣ በትክክል በሥራ ላይ እንዲውሉ ማድረግ፣ መከታተል፣
- የሂሳብ እንቅስቃሴ ምዝገባ በአግባቡ መከናወኑን መከታተል፣ ማረጋገጥ፤
- በመንግስት ፣ በብድርና እርዳታ ገንዘብ የሚሸፈኑ ፕሮጅክቶችን ሂሳብ መከታተል፣መቆጣጠር፤
- በተሰጠው የስልጣን ውክልና መሠረት የደመወዝና የሥራ ማስኬጃ ልዩ ልዩ የክፍያ ጥያቄዎች አስፈላጊነት በመመርመር እና ትክክለኛነት በማረጋገጥ የክፍያ ቼክና ማዘዣዎች በፊርማ ማጽደቅ፤
- መ/ቤቱ በህግ በተሰጠው ኃላፊነት መሠረት የሚሰበሰቡ የምዝገባ፤ የፈቃድ እድሳት፤ የቅጣት እና ሌሎች ገቢዎች በአግባቡ መሰብሰባቸውንና በየዕለቱ ወደ ባንክ መተላለፋቸውን መከታተል፣ ማረጋገጥ፣
- ሂሳብ በወቅቱ እንዲዘጋና በውስጥና በውጭ ኦዲተሮች እንዲመረመር ማድረግ፣ በኦዲት ሪፖርት ግኝት መሠረት መርሃ ግብር በማዘጋጀት የማስተካከያ እርምጃ መዉሰድ፤
- በውጭ ኦዲተር የተመረመረውን ሂሣብ ከተሰብሳቢ እና ተከፋይ ሂሳብ መግለጫዎች ጋር በማያያዝ ለሚመለከተው አካል እንዲላክ ማድረግ፤
- ለሥራ ማስኬጃ በሣጥን ሊያድር የሚገባውን ygNzB m-N bመመሪያው መሰረት መሆኑን መከታተል፤
- በጥሬ ገንዘብና በባንክ ያለውን ሂሳብ በየጊዜው እየተከታተለ የመ/ቤቱን የገንዘብ አቅም እንዲታወቅ ማድረግ፤
- ለመ/ቤቱ የሚቀርቡ የክፍያና የበጀት ጥያቄዎችን አግባብነት በማጣራት ለሚመለከተው ቡድን መሪ ወይም ባለሙያ መመምራት፣ አፈጻጸሙንም መቆጣጠር፤
- በመ/ቤቱ ስም የሚገኙ የእርዳታና ብድር ገንዘቦች በሚደረጉ ስምምነቶችና የአሠራር ማንዋሎች መሠረት ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የሥራ ክፍሎች ጋር በመተባበር በሥራ ላይ እንዲውሉ ማድረግ፣ የአፈጻጸም ሪፖርት ማዘጋጀት፣ የምክር አገልግሎቶችን መስጠት፤
- ግዥን ለመፈጸም የወጡ አዋጆች ደንቦችና መመሪያዎች በአግባቡ ስራ ላይ መዋላቸውን ማረጋገጥ፣
- ለግዥ አገልግሎት የሚፈለገውን ተግባር በብቃት ለማከናወን የሚቻልበትን ከአድልኦ ነጻ የሆነ ግልጽና ተጠያቂነት ያለበት የአሰራር ስርዓት መዘርጋት፣ተፈጻሚ እንዲሆን ማድረግ፣
- ከየስራ ክፍሉ የሚቀርቡ አስቸኳይ ግዢዎች በደንብና መመሪያ መሰረት እንዲገዙ ማድረግ፣
- ለሚገዙ እቃዎች ተፈላጊው ዓይነት፣ የጥራት ደረጃና መጠን ዝርዝር መግለጫ እንዲወጣ፣ ማድረግ፣ የተገዛውም እቃ ትክክለኛና በወጣው ዝርዝር መግለጫ መሰረት መሆኑን መከታተል፤ ማረጋገጥ፣
- በቡድን መሪው የተረጋገጠ የጨረታ ሰነዶችን በመመርመር በፊርማው አረጋግጦ ለአጽዳቂ ኮሚቴ መላክ፣
- የግዢ ውል ሂደት በሚገባ መካሄዱን መቆጣጠር፣ ኮንትራታቸውን በአግባቡ የማይወጡትን በመመሪያ መሰረት እርምጃ እንዲወሰድ ማድረግ፣
- በበላይ ኃላፊው በተሰጠው የገንዘብ ውክልና መጠን መሰረት ውል መፈጸም፣
- የግዢ ጥያቄዎች ተሟልተው መቅረባቸውን በማረጋገጥ መፈረም፣
- የግዢና የትራንዚት ስራዎች አስተማማኝ የመንግስት ግዥ አፈጻጸም መመሪያን ተከትሎ መከናወኑን መከታተል፣ ማስተባበር፣ መምራት፣
- ልዩ ልዩ የሚያስፈልጉ እቃዎችና አገልግሎቶች በጥራትና በተመጣጣኝ ዋጋ በወቅቱ እንዲገዙ በበላይነት መምራት፣ ማስተባበር፣ መከታተል፣
- በተለያየ ምክንያት ከታገዱ ተጫራቾች ግዢ እንዳይፈፀም መረጃ መያዝ፤ ስለ ግዢ እንቅስቃሴዎች የሚቀርቡትን የተለያዩ ዘገባዎችንና ስታትስቲካዊ የሪፖርት መግለጫዎች ማረጋገጥ፣
- መ/ቤቱ የሚሰበስባቸውን ልዩ ልዩ ገቢዎች በወቅቱ መሰብሰባቸውንና ለሚመለከተው አካል ፈሰስ መሆናቸውን መከታተል፣ አረጋግጦ ማፀደቅ፡፡
- የተለያዩ የመንግስት ግብርና ታክስ እና ሌሎች በተከፋይ የሚቀነሱ ሂሳቦችን ለሚመለከተው አካል በወቅቱ ገቢ መደረጋቸውን መከታተል፤
- ከድጋፍ ሰጪ አካላት የሚገኙ ገቢዎች በወቅቱ መሰብሰባቸውን መከታተል፣ በመስሪያ ቤቱ የባንክ ሂሳብ ገቢ መደረጋቸውን ማረጋገጥ፤
- መግለጫ የሚያስፈልጋቸው የሂሣብ ትራንዛክሽን መግለጫዎችን፣ ሂሳብ ሚዛንና ትንታኔ ማረጋገጥ፤
- የመ/ቤቱን የሂሳብ ሪፖርት በየወሩ እንዲዘጋጅ በማድረግ አጣርቶ ለሚመለከተው የመንግስት አካል ማቅረብ፤
- ሊሰበሰቡ የማይችሉ የተሰብሰቢ ሂሳቦች መረጃ ለበላይ አካል ማቅረብ፣ የውሳኔ ሃሳብ ሲደርሰውም ምዝገባ እንዲካሄድ ማድረግ፤
- የባለመብቶች ክፍያ ሳይፈፅሙ የሚዘጉ ድርጅቶችን የሚገባቸውን ኪራይ፤የቤት እድሳት ወጪ፤ ደመወዝ፤ ጥቅማጥቅምና ሌሎች ክፍያዎችን የፋይናንስ ህግን ተከትሎ መዘጋጀቱን ማረጋገጥና ወጪ በማፅደቅ ክፍያ መፈፀሙን መከታተል፤
- ድርጅቶች ሲዘጉ ንብረታቸውን ወደ መጋዘን ሲዘዋወር አስፈላጊ የሆኑ የአገልግሎት ግዥዎችን በህጉ መሰረት መፈፀማቸውን መከታተል፤
- የተዘጉ ድርጅቶች ንብረቶች ሲሸጡ የጨረታ ሰነድ መሸጥና ገንዘቡን ለሚመለከተው አካል ገቢ ማድረግ፤
- ከተዘጉ ድርጅቶች ንብረት በሽያጭ የተገኙ ገቢዎች ወደ ባንክ ገቢ መደረጋቸውን መከታተል
- ከተዘጉ ድርጅቶች ጋር ተፈፅመው የነበሩ ውሎች ላይ ያሉ ግዥዎችና ክፍያዎችን መከታተል፤ ትክክለኛነቱን እና ህጋዊነቱን በማረጋገጥ ክፍያ እንዲፈፀም ማድረግ፤
- በተዘጉ ድርጅቶች ስም በባንክ የነበሩ ገንዘቦች ወደ ኤጀንሲው የአደራ ሂሳብ ገቢ መደረጉን መከታተል፤
- በተዘጉ ድርጅቶች ገንዘብ ወደ ኤጀንሲው የአደራ ሂሳብ ገቢ የተደረጉትን ስራ ላይ እንዲውል በበላይ አመራር እንዲከፈል ሲወሰን በውሳኔው መሰረት እዲፈፀም ማድረግ፡፡
የለዉጥና መልካም አስተዳደር ቡድን
ተግባርና ኃላፊነት
- የቡድኑን ዓመታዊ እቅድ ያዘጋጃል፣ አፈጻጸሙን ይገመግማል፣ ቡድኑን መምራት፤
- ቡድኑን በአስፈላጊ ግብአቶች ያደራጃል፣ ምቹ የሥራ ሁኔታዎችን እንዲፈጥሩ ማድረግ፣
- በስሩ ያሉ ሠራተኞችን መምራት፣ መቆጣጠር፣ ማስተባበር፣
- የሠራተኞችን የሥራ አፈጻጸም መገምገም፣ ውጤታማ የሆኑ ሠራተኞችን ማበረታታት፣ የአቅም ክፍተት ያለባቸውን ሰራተኞች በመለየት ልዩ ድጋፍ እንዲያገኙ ማድረግ፣
- የቡድኑን የአሠራር ችግሮች በመለየትና በማጥናት ምቹ የአሰራር ሂደት እንዲኖር ማድረግ፣ ተፈጻሚነቱን ማረጋገጥ፣
- ወቅታዊ የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ማዘጋጀት፣ ለኃላፊው ማቅረብ፣
- ሊተገበሩ በእቅድ የተያዙ የለውጥ መሳሪያዎችን ተግባራዊ ለማድረግ የሚረዳና ውጤታማነትን የሚያሰፍኑ የአፈጻጸም መመሪያዎችን ማዘጋጀት፣ ማስተባበር፣ መርሆዎችንና ንድፈሃሳቦችን የተከተሉ መሆኑን ማረጋገጥ፣ ለኃላፊው ማቅረብ፣
- በተግባር ላይ እንዲውሉ የተመረጡ የለውጥ መሳሪያዎች አተገባበር ከሁኔታዎች ጋር ተጣጥመው ስለሚሄዱበት ማጥናት፣ ለኃላፊው ማቅረብ፣
- ለሥራ ዘርፎች ግብአት የሚሆኑ የለውጥ ሃሳቦችን በማመንጨት ለመ/ቤቱ ተስማሚ የሆኑ ዘመናዊ የለውጥ ሥራ አመራርና የአሠራር ማሻሻያ ጥናቶችን ማጥናት፣ ለኃላፊው ማቅረብ፣
- ልዩ ልዩ የማሻሻያ ሃሳብ ጥያቄዎች ሲቀርቡ አግባብነታቸውን እያጠና ለውሳኔ ለኃላፊው ማቅረብ፣
- የመልካም አስተዳደር ስርዓት እንዲሰፍን ተቋማዊ የለውጥ ምርጥ ተሞክሮዎችን መቀመር፣
- ከሁኔታዎች ጋር በማገናዘብ እንዲስፋፋ ማድረግ፤
- የሥራ ውጤታማነትን የሚያሻሽሉ የለውጥ መሳሪያዎች፣ ስታንዳርዶች፣ የአሰራር ዘዴዎች፣ ልዩ ልዩ ጥናቶች ውሳኔ ሲያገኙ በመ/ቤቱ በተገቢው ሁኔታ ስለመተግበራቸው ክትትል ማድረግ፣ አፈጻጸሙን እየገመገመ ለኃላፊው ማቅረብ፣
- በመ/ቤቱ ተግባራዊ የሆኑ የለውጥ መሣሪያዎች ያስገኙትን ፋይዳ በመገምገም ለኃላፊው ማቅረብ፣
- የለውጥ ሥራዎች ዕቅድና ፕሮግራሞች አተገባበር ላይ ያጋጠሙ ችግሮችን በማጥናትና በመገምገም የመፍትሄ ሃሳብ ማቅረብ፣
- የለውጥ መሳሪያዎችን በመጠቀም የሚካሄዱ ለውጦች ላይ ሙያዊ ምክር፣ እገዛና ድጋፍ ለስራ ዘርፎች መስጠት ወይም እንዲያገኙ ማድረግ፣
- ተቋማዊ ለውጥን በቀጣይነት ለመተግበር እንዲቻል የክህሎት፣ የአቅርቦት የአመለካከት ክፍተቶችን መለየት፣ መከታተል፣
- የሥራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ስለለውጥ ዓላማዎች እንዲገነዘቡና የህዝብ አገልጋነት ስሜት እንዲያዳብሩ ተከታታይነት ያላቸውን የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች በማዘጋጀት የፈጻሚዎችን አቅም እንዲጎለብት ማድረግ፣
- በአፈጻጸም ላይ የሚያጋጥሙ/ የሚታዩ ጥንካሬና የአሰራር ክፍተቶችን እያጠና የማሻሻያ እርምጃ እንዲወሰድ በጥናት የተደገፈ ሃሳብ ለኃላፊው ማቅረብ፣ ስለአፈጻጸሙ ክትትል እና ድጋፍ ማድረግ፣
- ከመሥሪያ ቤቱ አጠቃላይ ዕቅድ በመነሳት የስራ ዘርፎች ተቋማዊ የለውጥ ሂደትን በየስራ ዘርፋቸው የሚተገብሩበትና የተገኘውን ውጤት የሚገመግሙበት የአሰራር ባህል እንዲሰርጽ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፣
- የለውጥ ስራዎች በወጣ እቅድን የሥራ መርሃ ግብር መሰረት መከናወኑን መቆጣጠር፤ ማረጋገጥ፣
የዕቅድ ዝግጅት፣ ክትትልና ግምገማ ደይሬክቶሬት
ተግባርና ኃላፊነት
- የሥራ ክፍሉን የተለያዩ የሥራ ቡድኖችን ሥራ ማቀድ፣ ማስተባበር፣ መምራት፣ ውሳኔ በሚያሥፈልጋቸው ጉዳዮች ላይ ውሳኔ መስጠት፣
- የሥራ ክፍሉን ወይም የሥራ ቡድኖችን የሥራ ውጤት መከታተል፣ መገምገም፣ የእርምት እርምጃ መዉሰድ፣ ግብረ መልስ መስጠት፤ የእቅድ አፈጸጻም ሪፖርት ለመሥሪያቤቱ የበላይ ኃላፊ ማቅረብ፣
- የሥራ ቡድኖችንና ባለሙያዎችን የአቅም ክፍተት በማጥናት አቅማቸው የሚገነባበትን ሁኔታ ማመቻቸት፣
- ለዳይሬክቶረቱና ለሥራ ቡድኖቹ የሚያስፈልጉ ግብአቶች እንዲሟሉ ማድረግ፣
- የፖሊሲ ስትራቴጂና የፕሮግራም የፓኬጆችና የፕሮጀክቶች ሀሳቦች ማመንጨት፤ የዶክመንት ዝግጅትና ማሻሻል ሥራውን በመምራት የጸደቀ ዶክመንት ለሚመለከታቸው አካላት እንዲሰራጭ ማድረግ፣
- ለዘርፉ ሥራ የሚያግዙ የህግ ማእቀፎችን፣ የሥራ መመሪያዎችን፣ ማንዋሎችን፣ ስነ-ስርዓቶችን እና መግለጫዎችን በአዲስ መልክ እንዲወጡና እንዲሻሻሉ ማድረግ፣ የሚዘጋጁትን ሰነዶች ለሚመለከታቸው አካላት እንዲሰራጩ ማድረግ፣
- የሥራ ዘርፉንና የመሥሪያቤቱን ዕቅድ ዝግጅት፣ አፈጻጸምና የክትትልና ግምገማ ሥራዎች ሊያሻሽሉና ውጤታማ ሊያደርጉ የሚችሉ የጥናትና የምርምር ሥራዎች እንዲካሄዱ ሀሳብ ማመንጨት፤ማስተባበር፤ የጥናቱን ውጤት ተግባራዊ እንዲሆን ማድረግ፤ ፋይዳውን በመገምገም ሪፖርት ማቅረብ፣
- የመሥሪያቤቱን ስትራቴጂክና አመታዊ እቅድ ማዘጋጀት፤ እንዲዘጋጅ ማድረግ፤ የክትትልና ድጋፍ፣ የግምገማና ግብረ መልስ ሥራዎችን በኃላፊነት መምራት፣ ማስተባበር፣ በበላይ ኃላፊው እያፀደቀ ሥራ ላይ እንዲውል ማድረግ፣
- የእቅድ ዝግጅትና ሪፖርት፣ የበጀት ዝግጅት፤ የግምገማና እንዲሁም የለዉጥና መልካም አስተዳደር ግብረመልስ ሥራዎች ውጤታማና ቀልጣፋ እንዲሆኑ የአሠራር ስርዓቶችን መዘርጋት፣
- የጸደቀው በጀት ለሥራ ክፍሎች በአግባቡ እንዲደለደል በማድረግ ያሳውቃል አፈጻጸሙን መከታተል፣ መገምገም፣ ግብረ-መልስ መስጠት፣
- የተቋሙንና የዘርፉን የሥራ እቅድና አፈጻጸም የተሳካ ለማድረግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በሚደረገው ውይይትና አውደ ጥናቶች ላይ በመገኘት አስፈላጊ ግብአት መዉሰድ፤ ሥራ ላይ እንዲውል ማድረግ፣
- የመሥሪያቤቱን የተለያዩ የሥራ ክፍሎች የእቅድ ዝግጅት ሥራን እና አፈፃፀምን መከታተል፣ መደገፍ፣ መገምገም፣ ግብረ መልስ መስጠት፤
- የበጀት ዝውውር ጥያቄ ሲቀርብ አግባብነቱን በመመርመር የውሳኔ ሃሳብ ለበላይ ሃላፊው ማቅረብ ሲወሰንም ተግባራዊ እንዲሆን ማድረግ፤
- የሥራ ክፍሉን ሥራ በተመለከተ ከመንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች የሥራ ግንኙነት ማድረግ፣
- ለበላይ አመራሩና ለተጠሪ ተቋማት ሥራውን በሚመለከት ሙያዊ የምክርና የድጋፍ አገልግሎት መስጠት፣
- መሥሪያቤቱን በእቅድ አፈጻጸምና በጀት አጠቃቀም ላይ ለሚያጋጥሙ ችግሮች አማራጭ የመፍትሄ ሀሳብ በማመንጨት ለበላይ ኃላፊው ማቅረብ፣ ሲወሰን ተግባራዊ ማድረግ፣
- የበጀት የዕቅድ ዝግጅትና ግምገማን እንዲሁም የለዉጥና መልካም አስተዳደር ስራዎችን የሚመለከቱ ምርጥ ተሞክሮዎችን መቀመር፤ ወደ ሌሎችም እንዲስፋፋ ማድረግ፤
የህግ አገልግሎት ጉዳይ ዳይሬክቶሬት
ተግባርና ኃላፊነት
- የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችን በተመለከተ የህግ ጥሰቶች ሲኖሩ ለክስ የሚያበቁ መረጃዎች ማሰባሰብ፣ ክስ ማዘጋጀት፣ ፍርድ ቤት ቀርቦ ፋይል ማስከፈት፣ መጥሪያ ማድረስ፣ መጥሪያ መቀበል፣ መልስ ማዘጋጀትና ኤጀንሲውን በመወከል በማናቸውም ጉዳዮች በህግ ፊት ቀርቦ መከራከር፤
- የቃለ መሀላ አቤቱታ ማዘጋጀትና ማቅረብ፤ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችን በሚመለከት የጣልቃ ገብ አቤቱታ ማዘጋጀትና ማቅረብ፤
- የዕግድ አቤቱታ ማዘጋጀትና ማቅረብ፤ የመቃወሚያ አቤቱታ ማዘጋጀትና ማቅረብ፤ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችን በሚመለከት ጣልቃ ገብቶ መከራከር፣ ይግባኝ ክስ እና አቤቱታ ማቅረብ፤
- የህግ ምክር አገልግሎት መስጠት፣ ከሚመለከታቸው የስራ ክፍሎች ጋር መመሪያዎች ማዘጋጀት፣ ፀድቀው ሥራ ላይ እንዲውሉ ማድረግ፣ መመሪያዎች ስራ ላይ መዋላቸውን መከታተል፤
- በአዋጁ ላይ የሚታዩ የህግ ክፍተቶችን በየጊዜው መፈተሽና የህግ አስተያየቶችን ለሚመለከተው አካል ማቅረብ፣ የህግ የማሻሻያ ሃሳቦችን ማቅረብ፤
- ለኤጀንሲው የስራ ክፍሎች በህግ ነክ ጉዳዮች ላይ ስልጠና እንዲሰጥ መከታተል መስጠት፣ ማብራሪያ ወይም የህግ አስተያየት በፅሁፍ ማዘጋጀት፤
- ከኤጀንሲው አዋጅ ጋር የሚዛመዱ አዋጆችን የማሰባሰብ፣ የህግ ግንዛቤ የሚሰጡ ፓምፕሌቶችን ማዘጋጀት እና ማሰራጨት እና
- ከኤጀንሲው ሠራተኞች ጋር በተገናኘ የሚነሱ የህግ ነክ ጉዳዮች ክርክር ኤጄንሲውን በመወከል በማንኛውም ደረጃ በሚገኙ ፍ/ቤቶች ቀርቦ መከራከር፡፡
የስነ-ምግባር መከታተያ ቡድን
ተግባርና ኃላፊነት
- በተቋሙ ውስጥ ለሙስናና ብልሹ አሰራር ክፍተት የሚፈጥሩ ጉዳዮችን ለመለየት የሚያስችሉ ጥናቶችን ማካሄድ፤ መለየት፤
- ከሌሎች የሥራ ክፍሎች ጋር ያለውን ቅንጅት እና ትስስር በማጥናት የተጠናከረና ተመጋጋቢነት ያለው የስራ ግንኙነት እንዲፈጠር ሁኔታዎችን ማመቻቸት፤ አፈጻጸሙን መከታተል መደገፍ፤
- የአሰራር ክፍተቶችን ሊያሟላ የሚችል ተቋማዊ ረቂቅ የስነ-ምግባርና የብልሹ አሰራር ማንዋል ማዘጋጀት፤
- ከስነ-ምግባር ጉድለትና ከሙስና ጋር በተያያዘ የጥቆማ የአቅራቢዎች ሚስጢራዊነት ሊያረጋግጥ የሚችል የአሰራር ስርዓት ማዘጋጀት፤
- የስነ-ምግባር ተግባራትን የሚያጎለብቱ አሰራሮችን ሊያሻሽሉ የሚችሉ ጉዳዮች ላይ በየወቅቱ ጥናት ማካሄድ፤ ለሚመለከተው አካል ማቅረብ፤
- የተቋሙን ሰራተኞች የስነምግባር አስተሳሰባቸውን ሊያጎለብቱ የሚችሉ የስልጠና ሰነዶችን ማዘጋጀት፤ ስልጠና መስጠት፤
- በተቋሙ የስነ-ምግባርና የጸረ-ሙስና የአሰራር ማንዋልና የመተዳደሪያ ደንብ(Code of Conduct) ማዘጋጀት፤ ስልጠና መስጠት፤
- ሀገር አቀፍ የስነ-ምግባርና የጸረ-ሙስና ፖሊሲዎች፣ ደንቦች እና መመሪያዎች ዙሪያ ለተቋሙ ሰራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን መስጠት፤
- በተቋሙ ውስጥ ሃብታቸውንና የገንዘብ ጥቅማቸውን እንዲያስመዘግቡ የህግ ግዴታ ለተጣለባቸው ሰራተኞችና ሃላፊዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በመስጠት ሀብታቸውን በአግባቡ እንዲያስመዘግቡ ማድረግ፤ በአግባቡ መመዝገብ፤
- የስነ-ምግባር ተግባራትን የሚያጎለብቱ ተሞክሮዎችን መቀመር፤ ማስፋፋት፤ አሰራሮችን በየወቅቱ ማሻሻል፤
- የተቋሙ የስነ-ምግባርና የጸረ-ሙስና የአሰራር ማንዋልና የመተዳደሪያ ደንብ(Code of Conduct) እንዲሁም የሀገሪቱ የስነ-ምግባር የጸረ-ሙስና ህጎችና መመሪያዎች በተቋሙ ውስጥ መከበራቸውን መከታተል፤
- በክትትል ወቅት የተገኙ የአሰራር ክፍተቶች በመለየት የመፍትሄ ሃሳብ ለሃላፊው ማቅረብ፤
- በስነ-ምግባርናበጸረ-ሙስና ፖሊሲዎች፣ ደንቦችና መመሪያዎች ዙሪያ የተሰጡ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎች ያመጡትን ለውጥ መከታተል፤
- ሠራተኞች የሚያቀርቧቸውን የስነ-ምግባር ችግሮችና ማንኛውም ደንብና መመሪያ ጥሰት ጥቆማዎችን ተቀብሎ ምርመራ ማድረግ፤ የማስተካከያ እርምጃ በመለየት ለውሳኔ ሃላፊው ማቅረብ እና
- በስነ-ምግባር ጉድለት ምክንያት በተከሰቱ ችግሮች ላይ የተወሰዱ ዕርምጃዎችን መከታተል፡፡
የስትራቴጂክ አጋርነት ቡድን
ተግባርና ኃላፊነት
- የኤጀንሲዉን ተልእኮ ለማሳካት በሀገር አቀፍ እና በአለም አቀፍ ከሚገኙ ባለድርሻ አካላት፣ አጋር አካላት እና የሲቨል ማህበረሰብ ድርጅቶችን መለየት፣ በጋራ የሚሰሩ ተግባራትን ለመፈጸም የሚያስችል የጋራ እቅድ እንዲዘጋጅ ማድረግ፣ አፈጻጸሙን መከታተል፤
- በሀገር አቀፍ እና በአለም አቀፍ ከሚገኙ ባለ ድርሻ አካላት ጋር በእቅድ የተያዙ ተግባራት ለመገምገም የሚያስችል የግምገማ መድረክ ማዘጋጀት፣ አፈጻጸሙም እንዲገመገም ማድረግ፤
- በቅንጅታዊ አሰራር ላይ የሚታዩ የአፈጻጸም ክፍተቶችን መለየት፣ ክፍተቱን ለመፍታት የሚያስችል የመፍትሄ አቅጣጫ ማመላከት፤
- በሀገር አቀፍ እና በአለም አቀፍ ከሚገኙ ባለድርሻና ተባባሪ አካላት ጋር በጋራ የሚሰሩ ተግባራትን የአፈጻጸም ደረጃ በአካል ተገኝቶ መገምገም፣ የታዩ ክፍተቶችን ለይቶ ማቅረብ፣
- በሀገር አቀፍ እና በአለም አቀፍ ከሚገኙ ባለድርሻና ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር ቀጣይነት ያለው የአሰራር ስርአት እንዲዘረጋ ከሚመለከተዉ አካል ጋር ተቀናጅቶ መስራት፤
- በሀገር አቀፍ እና በአለም አቀፍ ከሚገኙ ባለ ድርሻና ተባባሪ አካላት ጋር በሚደረጉ ግንኙነቶች በተለዩ ክፍተቶች ዙሪያ ተቀባይነት ያገኙት የመፍትሄ ሃሳቦች ተግባራዊ እንዲሆኑ ማድረግ፤
- የኤጀንሲዉን ተልእኮ ለማሳካት የሚያስችል ሃብት ማፈላለግና ጥቅም ላይ እንዲዉል ማድረግ፤
- ከአጋር አካላት በተገኙ ሃብቶች ድጋፍ የሚከናወኑ ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች አፈጻጸም መከታተል፣ መገምገም፣ ግብረ-መል ስመስጠት፤
- የማክሮ ኢኮኖሚና ፊዚካል ማዕቀፎችን መሰረት ያደረጉ ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶችን ከዘርፉ ጋር እንዲተሳሰሩ ማድረግ፤
- በሌሎች ሀገራት ያሉ መልካም አሰራሮች እና ልምዶች በማሰባሰብ ለሀገራችንና ለተቋሙ ተልዕኮ በሚስማማ መልኩ መቀመር፤ እንዲቀመር ማድረግ፣ ማረጋገጥ፣ በጥቅም ላይ እንዲውል መከታተል፣
- ኤጀንሲው ከአለም አቀፍ ድርጅቶቸና አገር አቀፍ ድርጅቶችን መልካም የስራ ግንኙነት እና አጋርነት እንዲኖር ሁኔታዎች ማመቻቸት እና
- የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን በተመለከተ ዘርፉ ዘርፈ ብዙና ውስብስብ ከመሆኑ አንፃር እንደ ሀገር ያለው ባለሙያ ውስን ስለሆነ ከአለም አቀፍ ድርጅቶችና ከዘርፉ ከፍተኛ ልምድ ካላቸው ሀገሮች ትምህርት፣ ስልጠና እና ልምድ የሚወሰድበትን መንገድ መዘርጋት፣ ማመቻቸት፡፡
የውስጥ ኦዲት ዳይክቶሬት
ተግባርና ኃላፊነት
- የውስጥ ፋይናንስና ንብረት የኦዲት ሥራዎችን በአግባቡ መስራት፤
- የውስጥ ክዋኔ ኦዲት መስራት፤
- የኤጀንሲው ንብረት በአግባቡ መያዙን እና በቁጠባ ለተገቢው ስራ መዋሉን ማረጋገጥ፤
- የተቋሙ የበጀት እንቅስቃሴ ህግን ተከትሎ በታቀደው መሰረት መፈጸሙን ማረጋገጥ፤
- ለኤጀንሲው የተመደበው በጀት በፋይናንስ ህግ መሠረት ሥራ ላይ መዋሉን ማረጋገጥ፤
- በንብረት አያያዝና በፋይናንስ አጠቃቀም ላይ የምክር አገልግሎት መስጠት፤
- በመንግስት ሀብትና ንብረት ላይ ብክነት ሲደርስ እርምጃ እንዲወሰድ ማድረግ፤
- የመስሪያቤቱ ሀብትና ንብረት ከማንኛውም ተገቢ ካልሆነ አሰራር፣ ማጭበርበርና ከሙስና ጋር ተያይዞ ከሚመጣ ጉድለት መጠበቅ፤ መከላከል፤
- መስሪያቤቱ የዘረጋውን የውስጥ ቁጥጥር ስርአት ተግባራዊነት ይፈትሻል ያረጋግጣል፣ የማሻሻያ ሀሳብ ለበላይ አመራሩ ማቅረብ፤
- ማንኛውም የሰነድና የሂሳብ ማስረጃዎች አስተማማኝና ወጥ የሆነ ሂሳብ አያያዝ ስርአት መኖሩን ማረጋገጥ እና
- አፈጻጸሙን ለኤጀንሲውና ለገንዘብ ሚኒስቴር ሪፖርት ማቅረብ፡፡
በጎ ፍቃድ ማጎልበት እና ፈንድ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
ተግባርና ኃላፊነት
- በየወቅቱ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት የሚሹ ቀዳሚ ዘርፎች መለየት፤
- የተለዩ ዘርፎች በየትኛው የህበረተሰብ ክፍል ወይም ተቋም (መንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት) ሊከናወኑ/ሊደገፉ እንደሚገባ ማጥናት/መለየት፤
- በጥናቱ መሰረት የበጎ ፍቃድ አቅም (Potential)ከሚገኝባቸው ዘርፎች ጋር ትስስር መፍጠር (መደበኛ ዎርክሾፕ መድረኮችን መፍጠር) ፤
- የበጎ ፍቃድ አገልግሎት በማህበረሰቡ፣ በተለያዩ ተቋማት (መንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት) ግንዛቤ የማስጨበጥ፣ ስልጠናዎች መስጠትና የማስረፅ ስራዎችን ማከናወን፤
- የበጎ ፍቃደኛነት ስራን በተመለከተ አገር በቀልና አለም አቀፍ ድርጅቶች የማማከር፣ ነጻ አገልግሎት የመስጠት፣ ምቹ ሁኔታን የመፍጠር ስራዎችን የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ መስራት፤
- ህብረተሰቡ የበጎ ፍቃደኝነት ስራን በተመለከተ ግንዛቤ በመፍጠር የራሱ እሴት እንዲያደርገውና በጎ ፍቃደኝነትን እንደ ባህል አድርጎ መያዝ እንዲችል ማስቻል፤
- በጎ ፍቃደኞችን ማስተባበር፣ ተደራጅተው እንዲሰሩ መደገፍ እንዲሁም ዕውቅና በሰርተፍኬት አዘጋጅቶ መስጠት፤
- በበጎ ፍቃድ ዙሪያ ለመሰማራት ለሚመጡ ግለሰቦች፣ አገር በቀልና አለም አቀፍ አጋር ድርጅቶች ለሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ ጥያቄ ሲያቀርቡ በዘርፉ ተገቢውን መረጃዎች እና አገልግሎቶች መስጠት፤
- በየወቅቱ የበጎ ፍቃድ ስራዎችን መከታተል፣ መገምገም እንዲሁም የተከናወኑ የበጎ ፍቃድ ስራዎችን በየደረጃው ለሚመለከተው አካል ሪፖርት ማቅረብ፤
- በበጎ ፍቃድ ዙሪያ ከግለሰቦች፣ አገር በቀልና አለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር የተከናወኑ ተግባራትን መልካም ተሞክሮዎችን በጋዜጣ፣ በመፅሄት፣ በብሮሸር እና በመገናኛ ብዙሃን እንዲዘጋጅ፣ እንዲታተም እንዲሁም እንዲሰራጭ ማድረግ፤
- ድርጅቶችን በገንዘብ በመደገፍ አቅማቸውን ለመገንባት መንግስት በየዓመቱ ከሚመድበው በጀት በፈንድ አስተዳደር ተፈጻሚ ማድረግ፤
- በሲቪል ማኅበረሰብ ፈንድ ስም የሚመጣውን ሀብት ማስተዳደር፤
- ለሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ድጋፍ የሚውል የተለያዩ የገንዘብ ምንጮቸን የማፈላለግ ስራ መስራት፤ አቅማቸውን ለመገንባት የሚያስችለውን ሁኔታ ማመቻቸት፤
- ከተለያዩ አለም አቀፍ ድርጅቶች፣ ግለሰቦች እና ከመሳሰሉት አካላት ድጋፍ /ፈንድ/ ማፈላለግ፤
- ከሚፈርሱ ድርጅቶች ንብረት ሽያጭ ከሚገኝ ገቢ ወደ ፈንድ አሰተዳደር በማዞር ድጋፍ ለሚገባቸው ድርጅቶች ወይም ማህበራት መደገፍ፤
- ከለጋሽ ድርጅቶች የሀብት ምንጭ ማፈላለግና የሚገኘውን ሀብት በህግ አግባብ ለህበረተሰቡ ጥቅም ላይ ማዋል እና
- ከፈንድ የሚገኝ ሀብት በኤጀንሲው በሚዘጋጅ መመረያ መሰረት ለድርጅቶች ድጋፍ ማድረግ እና ለታለመለት ዓላማ እንዲውል መከታተልና መቆጣጠር፡፡
የጥናት፣ ምርምርና ስርፀት ዳይሬክቶሬት
ተግባርና ኃላፊነት
- የጥናት አካባቢዎች መለየት፣ ዕቅድ ማቀድ፣ ክትትል ማድረግ፤
- በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ ውስጥ ያለውን አሰራር ለማዘመን የአገልግሎት አሰጣጥ ፈጣን እና ቀልጣፋ እንዲሆን ለማድረግ የሚያስችል ጥናት ማካሄድ፤
- በጥናትና ምርምር በተገኙ ውጤቶች መሰረት የተለያዩ የአሰራር ለውጦችን ተከትሎ ማሻሻያዎች እንዲደረጉ ግብዓት ማቅረብ፤
- የሲቪል ማሀበረሰብ ድርጅቶች አላማና የህብረተሰቡን ጥቅም የሚጎዳ የስጋት ምንጮችን በጥናት መለየት፤
- የኤጀንሲውን ክፍተቶች በጥናት በመለየት የአሰራር ስርዓቱ እንዲሻሻል የጥናት ውጤት ለሚመለከተው ክፍል ማቅረብ፤
- በፖሊሲ አፈጻጸም ላይ ያሉ የአሰራርና የአደረጃጀት ማነቆዎች ተለይተው እንዲጠኑና መፍትሄዎች እንዲቀርቡ ማድረግ፤
- የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች እሴት ግንባታ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች መሰረታዊ ለውጥ በሚያመጣ፣ በተደራጀ ሁኔታ ለማስፈጸም የሚያስችል ጥናት ማድረግ፣
- በኤጀንሲው፣ በክልል መንግስታት፣ በዘርፍ አስተዳደር እና በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ግንኙነትን የሚያጠናክሩ ጥናቶችን ያካሂዳል፣ የተገኙ ግኝቶች በስራ ላይ የሚውሉበትን መንገድ ማመቻቸት፤
- የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የሚያፈሩት ሀብትና ንብረት (ፈንድ) ለማህበረሰቡ በተገቢው መንገድ ጥቅም ላይ መዋሉንና ተደራሽ መሆኑን የሚያመላክቱ ምርምርና ጥናታዊ ጽሁፎችን ማከናወን፤
- በፌዴራልና በክልል የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች አስፈላጊነትና አወቃቀር ላይ የጋራ መግባባት ሊፈጥሩ የሚያስችሉ ሁኔታዎችን በጥናት መለየት፣
- በሀገሪቷ ውሰጥ የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች ቁጥር፣ የሚንቀሳቀሱባቸው ክልሎችና የስራ ዘርፎች፣ የተጠቃሚው የህብረተሰብ ብዛት እና የአባሎቻቸው ቁጥር፣ የሚያንቀሳቅሱትን ሀብት፣ የድርጅቶች ፕሮጀክት ስርጭት እና ተያያዥ ጉዳዮችን ማጥናት፤
- በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በየአካባቢው የሚሰሩ የልማት ስራዎች እንደየዘርፋቸው በጥናት መለየት፤
- ኅብረተሰቡን ወደ ተጠቃሚነት የሚያመራ የመፍትሄ አቅጣጫዎች የሚያመለክት ጥናት ማቅረብ፤
- በኤጀንሲው ስር የተካሄዱ ፕሮጀክቶች/ፕሮግራሞች ያስገኙት ጠቀሜታ /impact/ እንዲገመገም ማድረግ፤
- የፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች አፈጻጸም የውጤታማነት ትንተና በማድረግ ለፖሊሲ ግብዓት የሚሆኑ ጉዳዮችን ይለያል፣ የውሳኔ ሀሳብ ማቅረብ፤
- ለፖሊሲ አፈጻጸም ግምገማ ጥናት የሚያስፈልጉ መረጃዎች እንዲሰበሰቡና እንዲደራጁ ማድረግ፤
- ለፖሊሲ ቀረጻና ምርምር የሚያስፈልጉ ጽሁፎች ተለይተው እንዲጠኑ መረጃዎች እንዲሰበሰቡና እንዲደራጁ ማድረግ፤
- ለሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የሚሰጡ ልዩ ልዩ ድጋፎች ውጤታማ እንዲሆኑ ክፍተቶቹን ጥናት ማድረግ፤
- ድርጅቶች የሚያከናውኗቸው የልማት ስራዎች መንግሰት ከሚያወጣቸው የልማት ዕቅዶች ጋር የተጣጣሙ እንዲሆኑ የሚያግዙ ጥናቶችን ማከሄድ፤
- ድርጅቶቹ በሀገሪቷ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ፣ ሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ እና የልማት እንቅስቃሴ ያላቸውን ሚና አስመልከቶ ተገቢውን ጥናት የማድረግ ስራ መስራት፤
- ከሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ጋር በተያያዘ ያሉ የኢኮኖሚ ሻጥሮችንና የሀብት ስወራዎች በሀገር ደረጃ ያላቸው ሥፋት፤ ጥልቀት እና ያስከተሉት ጉዳት ላይ ጥናት ማካሄድ እና
- የተለዩ ዘርፎች በየትኛው የህበረተሰብ ክፍል ወይም ተቋም (መንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት) ሊከናወኑ/ሊደገፉ እንደሚገባ ማጥናት/መለየት፡፡
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
ተግባርና ኃላፊነት
- የኤጀንሲው የበላይ አመራር በሂሳብ አጣሪነት ባለሙያዎችን በሚሾምበት ጊዜ በሂደቱ አስፈላጊ መረጃዎችን የማቅረብና ምክረ ሃሳብ የመስጠት ስራ መስራት፤
- የተዘጉ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ሀብትና ንብረት በህግ አግባብ እንዲጣራ፣ እንዲተላለፍ እንዲወገድ የማድረግ ስራ መስራት፤
- የተጣሩና የሚወገዱ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችን ብረቶች መረጃ በአግባቡ መያዝ፤
- የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የንብረት ይወገድልን ጥያቄ ሲያቀርቡ በህግ አግባብ በበላይ አመራሮቹ ባለሙያዎች ሲሾሙ ንብረቶቹን ቆጠራ እንዲያካሂዱ፣ በዓይነታቸው እና በይዞታቸው ተጣርቶና በኮድ ተደራጅቶ የውሳኔ ሀሳብ እንዲቀርብ ማድረግ፤ ሲወሰን አፈጻጸሙን መከታተል፤
- በማጣራት ሂደት ወቅት ተአማኒነት የሌላቸው የሂሳብ ሰነዶች ሲኖሩ ኦዲተር ተሾሞ እንዲመረመር ያደርጋል፣ የሕግ ጉዳዮች ሲኖሩ ለኤጀንሲው የህግ ክፍል እንዲቀርብ በማድረግ ሂደቱን መጠየቅ፤
- የሚወገዱ ንብረቶች አፈጻጸማቸው በሽያጭ፣ በመቅበር፣ በማቃጠል እንዲወገዱ ማድረግ፤
- ንብረቶቹ ሲወገዱ ልዩ የሙያ እገዛ የሚያሰፈልጋቸው ከሆነ ከሚመለከታቸው ሴክተር መሥሪያቤቶች ጋር በመነጋገር ድጋፍ እንዲገኝ ማድረግ፤
- በሽያጭ የሚወገዱ ንብረቶች ከእዳና እገዳ ነፃ መሆናቸውን ማጣራት፤
- ንብረት በማጣራት እና በማስወገድ ሂደት ላይ የሚነሱ ቅሬታዎችን አጣርቶ ማስተካከያ እርምጃ መውሰድ፣ መልስ መስጠት፣ እንደአስፈላጊነቱ ለበላይ አመራር የውሳኔ ሀሳብ ማቅረብ፤
- የተዘጉ ድርጅቶችን ንብረት እስኪተላለፍ ወይም እስኪወገድ እንዳይባክን በአግባቡ ተጠብቆ እንዲቆይ ማድረግ፣ በቀላሉ የሚበላሹ ንብረቶች በወቅቱ እንዲሸጥ ወይም እንዲተላለፍ ማድረግ፣ መከታተል፤
- የተሸጡ ንብረቶች በአግባቡ ወደ ገዢው አካል የንብረት ባለቤትነት መብት መተላለፉን ማረጋገጥ፤
- በሽያጭ የተገኘ እና በማጣራት ወቅት የተገኘውን ገንዘብ ኤጀንሲው ወደ ከፈተው አካውንት መግባቱን ማረጋገጥ፣ መከታተል፤
- በሰው ስራሽና በተፈጥሮ አደጋ ሙሉ በሙሉ የወደሙ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ተሸከርካሪዎችና ንብረቶች ተጣርቶ የቀረበለትንና በኢንሹራንስ ፖሊሲ ዋጋው ሲተካ ኢንሹራንስ ካምፓኒው ንብረቱን ለሌላ አካል ሲያስተላልፈው የስም ዝውውር እንደአስፈላጊነቱ የድጋፍ ደብዳቤ ይሰጣል፤
- ከሚፈርሱ ድርጅቶች በህጉ መሰረት ንብረት ከመሸጡ በፊት ቆጠራ በማድረግ ማጣራት እና በአግባቡ እንዲጠበቅ ማድረግ፤
- የተበተኑ ንብረቶች ካሉ ከተለያዩ ቦታዎች እንዲሰበሰቡ ማድረግ እንዲሁም ከሂደቱ ጋር ተያያዥነት ያላቸው የመንግሰት አካላት ጋር ተቀናጅቶ መስራት፤
- መተላለፍ ያለባቸውን ንብረቶች በመለየት ለበላይ አካል የውሰኔ ኃሳብ በማቅረብ ተገቢውን ምላሽ ሲያገኝ የማስተላለፍ ተግባር ማከናወን፤
- በሽያጭ ለሚወገዱ ንብረቶች የገበያ ጥናት ማድረግ፣ ጨረታ ማውጣት እና በመሸጥ የተገኘውን ገንዘብ ለዚሁ ወደ ተዘጋጀ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ፈንድ አስተዳደር የባንክ ሂሳብ እንዲገባ ማድረግ፣
- ከሶስተኛ ወገን ተሰብሳቢ ሂሳቦች በማጣራት ገቢ እንዲሆን ማድረግ፤
- የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በገቡት ውል መሰረት ተፈፃሚ ሳያደርጉ በራሳቸው ዘግተው የጠፉና ኤጀንሲው በሚያደርገው የክትትል ስርዓት የድርጅቱን ንብረት ሲቆጣጠር በውሉ መሰረት ለሚጠይቁ 3ኛ ወገን ባለመብቶች ግዴታውን መፈፀም እና
- እዳያለባቸው የተዘጉ እና እንዲሁም ስራ ላይ እያሉ ንብረት ሰብስበው ለሌላ አካል መተላለፍ የማይችሉ ግን ቢሸጡ ዋጋ የሚያወጡ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ንብረት በጨረታ ለመሸጥ የንብረቶቹ የገበያ ዋጋ ጥናት እንዲደረግ ማድረግ፣ የዋጋጥናት ከተደረገ በኋላ የዋጋ ግምት እንዲወጣ ያደርጋል፤ ከአቅም በላይ የሆኑ ወይም ልዩ ሙያ የሚያስፈልጉትን የሙያ እገዛ ጥያቄ ማቅረብ፡፡



