ባለስልጣኑ በኅብረተሰቡ ዘንድ የበጎ አድራጎት እና በጎ ፈቃደኝነት ባሕል እንዲዳብር ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በአዋጅ ቁጥር 1113/2011 ከተቋቋመበት ዓላማዎች መካከል በኅብረተሰቡ ዘንድ የበጎ አድራጎት እና በጎ ፈቃደኝነት ባሕል እንዲዳብር ማድረግ አንዱ ነው፡፡ ይህንኑ ዓላማ ከግብ ለማድረስ ከተለያዩ አጋር ተቋማትና ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በትብብር እና በቅንጅት እየሰራ ይገኛል፡፡
ባለስልጣኑ CrossRoad International ከተባለ ድርጅት ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለሚገኙ ተማሪዎች በበጎ ፈቃድ እና በጎ አድራጎት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል፡፡
በስልጠናው ላይ የዩኒቨርሲቲውን ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሰለሞን ጥሩነህን ጨምሮ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የበጎ ፈቃድና ትብብር መሪ ስራ አስፈጻሚ እንዲሁም የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
ሥልጠናው የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በበጎ ፈቃድና በጎ አድራጎት ተግባራት ላይ ተሳታፊ እንዲሆኑ ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር መሆኑን የባለስልጣኑ የበጎ ፍቃድ ማጎልበትና ትብብር መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ደጀኔ ጌታቸው የገለጹ ሲሆን ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ለበጎ ፈቃደኞችና በጎ ፈቃድ ፈላጊዎች ያበለጸጋቸውን Volunteerism management information system ድህረ ገጽ እና ቅን ልብ-We volunteer የሞባይል መተግበሪያን በሚመለከት ማብራሪያና የአጠቃቀም ዘዴውን በሚመለከት ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡


