የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ጋር የኢትዮጵያ ሶሻል ኢንተርፕራይዝ ፖሊሲ ጥናት ለማድረግ የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ።
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከፓሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ጋር በሶሻል ኢንተርፕራይዝ ላይ ትኩረት ያደረገ የፓሊሲ ጥናት ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት የተፈራረመ ሲሆን ከፓሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩቱ ጋር በጋራ በመሆን የሚዘጋጀው የሶሻል ኢንተርፕራይዝ ጥናት ለመንግስት የፖሊሲ ግብዓት የሚውል ይሆናል።
የኢትዮጵያ ሶሻል ኢንተርፕራይዝ ጥናቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ ያለውን የፖሊሲ ክፍተት ለመሙላት እገዛ የሚያደርግ ሲሆን ተጨማሪ የፓሊሲ ጥናቶችን ለማድረግ እንደመነሻ እንደሚሆን ተጠቁሟል።
የመግባቢያ ሰነዱን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ እና የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ፍቃዱ ፀጋዬ የተፈራረሙ ሲሆን የመግባቢያ ሰነዱ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ጋር በምርምር፣ በፖሊሲ ጥናት ትንተና፣ በፖሊሲ ውይይት፣ በአቅም ግንባታ፣ በእውቀት ማጋራት እና በተቋማዊ ትብብር ላይ በጋራ ለመስራት ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር ነው።
የመግባቢያ ሰነዱ ለጠንካራ የሲቪል ማህበረሰብ ዘርፍ እድገት፣ የተሻለ የፖሊሲ ግብዓት ለማግኘት እና ለጠንካራ የመንግስት እና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ቅንጅት አስተዋፅዖ የሚያደርግ ሲሆን ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ እና ኢንስቲትዩቱ በሌሎች ጉዳዮችም ላይ በትብብርና በቅንጅት ለመስራት ከመግባባት ላይ ደርሰዋል።





