Tagline
የፍትሕ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት 22ኛውን የፀረ- ሙስና ቀን አከበሩ::
የፍትሕ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት ”ትውልድን በሥነ- ምግባር ፤ ተቋምን በአሰራር ”በሚል መሪ ቃል 22ኛውን የፀረ- ሙስና ቀን የተቋማቱ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች እንዲሁም ሰራተኞች በተገኙበት በፓናል ውይይት ተከብሯል፡፡
ይህንን ቀን “ትውልድን በሥነ -ምግባር ፤ ተቋምን በአሰራር” በሚል መሪ ቃል ስናከብር ትውልድን በሥነ -ምግባር ሲባል እያዳንዳችን በተሰጠን ኃላፊነት ስነ-ምግባራዊ አገልግሎት እየሰጠን መሆናችንን ለማስታወስ ሲሆን፤ ተቋምን በአሰራር ስንል ደግሞ ሙስናን የመዋጋት ስራዎቻችን ፍሬ እንዲኖራቸው የተቋሞቻችንን አሰራር መፈተሸ ስንችል እንደሆነ ማሳያ መሆኑ ተገልጿል ፡፡
በመድረኩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣንን ጨምሮ የፍትሕ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ጠቋማት ከፍተኛ አመራሮች የሀብት ምዝገባ ርክክብ ያካሄዱ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ በፌደራል ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የተዘጋጀ የንቅናቄ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
በውይይቱም የፀረ ሙስና ቀን ሲከበር በዓመት አንዴ ከሚደረግ መርሃ-ግብር ባለፈ በቤታችን ሙስናን የሚፀየፍና በስነ-ምግባር የታነፀ ትውልድ ማፍራት ላይ እንዲሁም በየተቋሞቻችን ግልፅ የሆኑ ስርዓቶችን መዘርጋት እና ተጠያቂነትን በማረጋገጥ በኩል ኃላፊነትን መወጣት እንደሚገባም ተጠቁሟል፡፡





