የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከኮሪያ በጎ ፈቃደኞች ድርጅት (Korean Volunteers Organization- KVO) ጋር በመተባበር ለበጎ ፍቃደኞች አገልግሎት የሚሰጥ የተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያ ( Mobile App) ተዘጋጀ።

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በአዋጅ ቁጥር 1113/2011 ከተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት በጎ ፈቃደኝነትንና በጎ አድራጊነት በማህበረሰቡ ዘንድ ባህል እንዲሆንና እንዲዳብር ማድረግ አንዱ ነው።

ይህንን ተግባርና ኃላፊነት ለመወጣት ከኮሪያ በጎ ፈቃደኞች ድርጅት (Korean volunteers organization-KVO) ጋር በመተባበር ለበጎ ፍቃደኞች አገልግሎት የሚውል የተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያ (Mobile phone App) በማበልፀግ ወደተግባር ለመግባት በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛል።

ይህንኑ አስመልክቶ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና የድርጅቱ ተወካዮች በተገኙበት የግማሽ ቀን የትውውቅና የውይይት መድረክ ተካሂዷል።

በመድረኩ ላይ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች አቶ ፋሲካው ሞላ እና አቶ መስፍን ሙሉነህ እንዲሁም የኮሪያ በጎፈቃደኞች ድርጅት Korean volunteers organization KVO የኢትዮጵያ ተወካይ አቶ ሚኪያስ ግርማ የተገኙ ሲሆን በመድረኩ መተግበሪያውን በሚመለከት፣ የመተግበሪያውን አገልግሎት፣ መለያ ሎጎ እና የዳሰሳ ጥናት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ መድረኩን ባስጀመሩበት ወቅት እንዳሉት ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ እንደአውሮፓውያኑ አቆጣጠር December 5 በሚከበረው የዓለም ዓቀፉ የበጎ ፈቃደኞች ቀን ላይ መተግበሪያውን ለማስተዋወቅ እቅድ የተያዘ መሆኑን በመግለጽ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ እያደረገ ያለው የዲጂታይዜሽን ሪፎርም አካል መሆኑንም አክለው ጠቁመዋል።

የኮሪያ በጎ ፈቃደኞች ድርጅት Korean Volunteers Organization-KVO የኢትዮጵያ ዳይሬክተር አቶ ሚኪያስ ግርማ ባስተላለፉት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ላይ ድርጅታቸው መተግበሪያውን ሰርቶ ማስረከብ ብቻ ሳይሆን በትብብርና በቅንጅት በመስራት ውጤታማ እንዲሆን ጥረት እንደሚያደርጉ በመግለጽ መተግበሪያው በጎ ፈቃደኞችን ከመመዝገብና ከማገናኘት ባለፈ የተደራጀ መረጃ በመቀመር የበጎ ፈቃደኞችን አስተዋጽኦ ይበልጥ ያጎለብታል ብለዋል።
መተግበሪያው December 5/2025 በይፋ ተመርቆ ስራ ይጀምራል።