የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ፒፕል ኢን ኒድ (People In Need) ከተባለ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችል ሰነድ ተፈራረመ፡፡

የሥምምነት ሰነዱን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ እና የፒፕል ኢን ኒድ (People In Need) የኢትዮጵያ ዳይሬክተር Bharat Man Shrestha የፈረሙ ሲሆን በፊርማ ስነስርዓቱ ላይ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችን ጨምሮ የድርጅቱ ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡

ለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከድርጅቱ ጋር በጋራ ለመስራት የተስማሙባቸው ዋና ዋና ጉዳዮች ሀገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን ማጠናከር፣ በሎካላይዜሽን፣ በጥናትና ምርምር እና በአቅም ግንባታ ስራዎች ላይ ትኩረት ያደረጉ ሲሆን ይህንን የሚያስተባበር የጋራ ጥምር ተወካይ እንደሚሰየም ተጠቁሟል፡፡

የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በትብብርና በቅንጅት ለመስራት የሚያስችል ውይይት ከፒፕል ኢን ኒድ (People In Need) ተካዮች ጋር ያደረገ ሲሆን የድርጅቱ ተወካይ Bharat Man Shrestha ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጋር በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውንም ጠቁመዋል፡፡

ፒፕል ኢን ኒድ (People in Need) በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ተመዝግበው ከሚንቀሳቀሱ የውጭ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አንዱ ሲሆን በሰብዓዊ ድጋፍና በልማት ትብብሮች ላይ በኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች እየሰራ ይገኛል፡፡