የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከሜሪስቶፕስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለተቋሙ ሰራተኞች የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ፡፡
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከወረቀት የጸዳ አሰራርን ለመዘርጋት በዲጂታላይዜሽን ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ ይገኛል፡፡ ከማሪ ስቶፕስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ጋር በመተባበርም የመዝገብ አስተዳደር ስርዓት (Document management system) ለመዘርጋት የሚያስችል አስፈላጊ ግብዓቶችንና ቅድመ ዝግጅቶችን አሟልቶ በቀጣዩ አንድ ወር ውስጥ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ይገኛል፡፡
የዚሁ አካል የሆነውና የተቋሙን የሚመለከታቸውን የስራ ክፍሎችና ባለሙያዎችን ተደራሽ ያደረገ የአቅም ግንባታና የግብዓት ማሰባሰቢያ ስልጠና ለተከታታይ አምስት ቀናት ተሰጥቷል፡፡
ስልጠናውን በሚመለከት ማብራሪያ የጠየቅናቸው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ስራ አስፈጻሚ አቶ ጌትየ ዝግአለ እንደገለጹልን ስልጠናው ትኩረት ያደረገው በባለስልጣኑና በሜሪስቶፕስ ኢንተርናሽናል ኢትየጵያ ትብብር እየለማ የሚገኘው የመዝገብ አስተዳደር ስርዓት (Document management system) ምንነትና አጠቃቀም ስርዓት ላይ መሆኑን ጠቁመው የስራ ክፍሎች ሲስተሙን ሲጠቀሙ በምን መልኩ መጠቀም እንዲሚችሉ የሚጠቁም ተግባር ተኮር ስልጠና መሆኑን ጠቁመዋል፡፡


Tagline
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ለሲስተሙ አስፈላጊ የሆኑ መሰረተ ልማቶችን እና ግብዓቶችን ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር እንዲሟሉ ያደረገ ሲሆን በወረቀት የሚገኙ ሰነዶችን መደ ዲጂታል ስርዓት የመቀየሩን ሂደት ለማጠናቀቅ በመስራት ላይ እንደሚገኝም ጠቁመዋል፡፡
የዲጂታል ስርዓቱ ሙሉ በሙሉ ተሰርቶ ሲጠናቀቅ በባለስልጣኑ የሚገኙ መዝገቦች ሙሉ በሙሉ ዲጂታይዝድ የሚሆኑ ሲሆን ይህም በባለስልጣኑ የመዝገብ ቤት ውስጥ የሚገኙ መዝገቦችን ብልሽት የሚቀርፍ እንዲሁም የባለስልጣን መስሪያ ቤቱን የአሰራር ስርዓት የሚያዘምን መሆኑንም አክለው ገልጸዋል፡፡

